Sunday, April 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
Uncategorizedየ ጃሲሪ ታለንት ኢንቬስተር ፕሮግራም 6ኛ ዙር ማመልከቻ | ጋዜጣዊ መግለጫ | ጥር 6, 2016 ዓ.ም

የ ጃሲሪ ታለንት ኢንቬስተር ፕሮግራም 6ኛ ዙር ማመልከቻ | ጋዜጣዊ መግለጫ | ጥር 6, 2016 ዓ.ም

ቀን:

ጋዜጣዊ መግለጫ |  6, 2016 .

ማስታወቂያ

የ ጃሲሪ ታለንት ኢንቬስተር ፕሮግራም 6ኛ ዙር ማመልከቻ

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

6ኛው ዙር የ ጃሲሪ ታለንት ኢንቬስተር ፕሮግራም ማመልከቻ አሁን ተጀምሯል። ጃሲሪ ከኬንያ፣ ከሩዋንዳ እና ከኢትዮጵያ የሚመጡ ሥራ ፈጣሪዎች እንዲያመለክቱ ጥሪ ያቀርባል፡፡ ፕሮግራሙ ጠንካራ ብቃትን መሰረት ያደረገ

የአመራረጥ ሂደትን በመከተል፤ በጣም ተስፋ ሰጭ እና ብቁ ስራ ፈጣሪዎችን ለፕሮግራሙ ይመለምላል፡፡

አሁን ባለው ተለዋዋጭ የንግድ ዓለም ውስጥ አዲስ ሥራ መጀመር በጣም ከባድ ሊሆን ይችላል። ጀማሪ ሥራ

ፈጣሪዎች የሚያጋጥሟቸውን ተግዳሮቶች በመገንዘብ፣ ጃሲሪ ታለንት ኢንቬስተር በአለን እና ጊል ግሬይ ፊላንትሮፒስ

ስር የሚንቀሳቀስ ልዩ ፕሮግራም ሲሆን፤ ከፍተኛ ተፅእኖ ያላቸውን፣ ግብይትን የሚፈጥሩ እና የጋራ እሴትን መሰረት ያደረጉ ሥራዎችን ለማዳበር እና ሥራ ፈጣሪዎችን ለመደገፍ ጽኑ እና ቁርጠኛ አቋም ያለው ፕሮግራም ነው።  ጃሲሪ

ታለንት  ኢንቬስተር ለአዳዲስ  ንግዶች  ስኬት  ማነቆ  የሆኑ እንቅፋቶችን  ለማስወገድ ይጥራል። ፕሮግራሙ ፈንድ

በመስጠት፣ በማሰልጠን፣ በስትራቴጂካዊ ምክር እና በፈጠራ ሃሳብ ውስጥ የተወሳሰቡ ሂደቶችን እንዲፈቱ በማገዝ የፕሮግራሙን ተሳታፊዎችን ከንግድ ሃሳብ እስከ ቬንቸር ፈጠራ እገዛ ያደርጋል፡፡

“ጃሲሪ በሦስት የሥራ ፈጠራ አስፈላጊ ቅድመ-ሁኔታዎች ላይ መሰረት ያደረገ ሲሆን፤ እነርሱም፡- አልኬሚ፣ ምኞት እና

አመለካከት ናቸው። ከአልኬሚ ጋር ተመሳሳይነት ያለው ሥራችን፤ ሥራ ፈጣሪዎችን ከመነሻው ጀምሮ መምራት መቻላችን ነው፡፡ እንዲሁም ለወደፊት የአፍሪካን ብልጽግና ለመቅረጽ የገበያ ፈጠራን እናስተዋውቃለን። ታቅዶበት የተሰየመው የፕሮግራማችን ስም ጃሲሪ፤ የስዋሂሊ ትርጓሜው ጀግንነት ማለት ሲሆን ይህም ያለንን ቁርጠኛ አቋም እና መሰጠታችንን ያሳያል። ትልቅ  ማሰብ፣ የወደፊቱን  ግምት  ውስጥ በማስገባት ለረጅም ጊዜ ማሰብ እና ኃላፊነት የተሞላበት ስነምግባር ያለው ስራ ፈጠራ ድፍረትን ይጠይቃል።” (አንቶኒ ፋር፤ የአላን እና ጊል ግሬይ ፊላንትሮፒስ ዋና ሥራ አስፈፃሚ)

ጉልህ የሆነ ተጽእኖ ማድረጋችንን የምንቀጥል ሲሆን፤ ከፕሮግራሙ ጅማሮ እስከ አሁን ድረስ 144 የፕሮግራሙ

ተጠቃሚዎችን በ4 ዙር ውስጥ በማፍራት ከ 61 ቬንቸር 24 ኢንዱስትሪዎችን አሳድገናል፤ በተጨማሪም ድርጅቶቻችን

በአጠቃላይ ለ 613 ሰዎች የስራ እድል ፈጥረዋል።

 

 

የስድስተኛው ዙር ማመልከቻ በጥር 15, 2016 ዓ.ም ተከፍቶ መጋቢት 27, 2016 ዓ.ም የሚያበቃ ይሆናል፡፡ ጃሲሪ

ፍላጎት ያላቸው አመልካቾች የማመልከቻውን ሂደት በተመለከተ ሊያነሱ የሚችሉትን ጥያቄዎች ለመመለስ የሚረዳቸውን መረጃ በተለያዩ ጊዜያት በ ኦንላይን የሚያደርግ ሲሆን፤   ዝርዝር መረጃውም በጃሲሪ ማህበራዊ ሚዲያ መድረኮች ላይ ይገኛል።

ለማመልከት  https: //jasiri.org/application/ ይጎብኙ።

ስለ ጃሲሪ

ጃሲሪ በአፍሪካ አህጉር ላይ አዳዲስ ገበያዎችን በመፍጠር፤ ማህበረሰቡን የሚጠቅሙ እና ድህነትን በሚያጠፉ የስራ

ፈጣሪዎች ላይ ኢንቨስት ያደርጋል፣ ያሳድጋል፤ እንዲሁም ያበረታታል። ጃሲሪ ሥራ ፈጣሪዎች ለአዳዲስ የፈጠራ ሥራዎች ቁልፍ ናቸው ብሎ በማመን፤ ሥራ ፈጣሪዎችን ተባባሪ መስራቾች ሊሆኑ ከሚችሉ ከፍተኛ ራዕይ የሰነቁ ሌሎች ሥራ ፈጣሪዎች ጋር እንዲገናኙ ዕድል ያመቻቻል። ፕሮግራሙ ከሀሳብ ማመንጨት እስከ ፈጠራ ድረስ አዳዲስ ስራዎችን በመደገፍ፤ በአፍሪካ ልዩ እና ኃላፊነት የሚሰማቸው ስራ ፈጣሪዎችን ለማፍራት የረጅም ጊዜ ዕቅድ ይዞ ይንቀሳቀሳል።

ተጨማሪ መረጃ jasiri.org. ላይ ያግኙ ፕሮግራሙ ሙሉ በሙሉ በእንግሊዘኛ ቋንቋ ስለሆነ የቋንቋው ክህሎት ሊኖሮት ይገባል፡፡

የሚ ያቄዎች

ስለ ጃሲሪ ለሚኖሮት ጥያቄዎች እና ለበለጠ መረጃ [email protected] ይጠቀሙ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ያልተቃናው የልጆች የንባብ ክህሎት

አንብቦና አዳምጦ መረዳት፣ የተረዱትን ከሕይወት ጋር አዋህዶ የተቃና ሕይወት...

እንስተካከል!

ሰላም! ሰላም! ውድ ኢትዮጵያውያን ወገኖቼ እንዲሁም የሰው ዘር በሙሉ፣...

የሙዚቃ ምልክቱ ሙሉቀን መለሰ ስንብት

የኢትዮጵያ ዘመናዊ ሙዚቃ በ1950ዎቹ እና በ1960ዎቹ በኪነ ጥበባትም ሆነ...

‹‹ደስታ›› የተባለችው አማርኛ ተናጋሪ ሮቦት በሳይንስ ሙዚየም

‹‹እንደ ሮቦት ዋነኛው አገልግሎቴ ውስብስብ የሆኑ የቴክኖሎጂ ውጤቶችንና አሠራሮችን...