Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምየብሊንከን የምዕራብ አፍሪካ ጉብኝት

የብሊንከን የምዕራብ አፍሪካ ጉብኝት

ቀን:

ከአፍሪካ ጋር ያላትን ግንኙነት ይበልጥ አጠናክራ ለመቀጠል እየሠራች መሆኑን ያስታወቀችው አሜሪካ፣ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሯን ወደ አራት የሳህል ቀጣና የአፍሪካ አገሮች ልካለች፡፡

በመካከለኛው ምሥራቅና በዩክሬን ያሉት ጦርነቶች አሜሪካን ጨምሮ የኃያላን አገሮቹ አጀንዳ ቢሆንም፣ የአሜሪካ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር አንቶኒ ብሊንከን የአሁኑ የአፍሪካ ጉብኝት፣ አሜሪካ ከአፍሪካ አገሮች ጋር ያላት ግንኙነት እየተጠናከረና ትኩረት እንዳልተነፈገው ለማሳየት ያለመ ነው፡፡

የደኅንነት ሥራዎችን ማጠናከር፣ የጤና ዘርፉን መደገፍና ኢኮኖሚያዊ ዕድገትን ማፋጠንም በብሊንከን ጉብኝት ከሚካተቱ ዋና አጀንዳዎች ቀዳሚዎቹ ናቸው፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

የብሊንከን የምዕራብ አፍሪካ ጉብኝት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የአይቮሪኮስት ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ካቹ ሀውጃ ሊኦን አዶም የአሜሪካ አቻቸው አንቶኒ ብሊንከንን ተቀብለዋል
(አሶሺየትድ ፕሬስ)

በኬፕቨርዴ፣ ኮትዲቫር፣ ናይጄሪያና አንጎላ የሚያደርጉትን ጉብኝት ሰኞ ጥር 13 ቀን 2016 ዓ.ም. በኬፕቨርዴ የጀመሩት ብሊንከን፣ የአገሮችን ኢኮኖሚያዊ ዕድገት ለማፋጠን ከአሜሪካ የሚሊኒየም ቻሌንጅ ኮኦፖሬሽን ፈንድ ተጠቃሚ የሆነችው ኬፕቨርዴ ውጤታማ መሆኗን ገልጸዋል፡፡

 ከዚህ ቀደም ሁለት ጊዜ ባገኘችው ፈንድ የጀመረችውን ፕሮጀክት በማጠናቀቅ ቀዳሚ አገርም ሆናለች፡፡ ሦስተኛውን ድጋፍ ተግባራዊ ለማድረግ እየተንቀሳቀሰች መሆኗም በአሜሪካ ይሁንታን ያገኘ ነው፡፡

ከአሜሪካ ሚሊኒየም ቻሌንጅ ኮኦፖሬሽን ባገኘቸው ድጋፍ የወደብ ከተማዋን ፖርቶ ዳ ፕራያ እያዘመነች የምትገኘው አገሪቱ፣ ከዓለም ጤና ድርጅት ከወባ ነፃ ሰርተፍኬት አግኝታለች፡፡

የደሴት አገሯ ኬፕቨርዴ በርካታ ዳያስፖራዎች በአሜሪካ የሚገኙ ሲሆን፣ እ.ኤ.አ. ከ1990 ወዲህ የተረጋጋ ፖለቲካ ያላት፣ ከአፍሪካ አገሮችም የበለፀገችና ዴሞክራሲን ያሠፈነች እንደሆነች ይታወቃል፡፡

አሜሪካም ካቻምና ከኬፕቨርዴ ጋር በወታደራዊ ትብብር በተለይም በባህር ደኅንነት ዙሪያ አብሮ ለመሥራት የስምምነት ሰነድ መፈራረሟ ይታወሳል፡፡

ከኬፕቨርዴ ጉብኝታቸው በኋላ የኮትዴቮር ወይም (አይቮሪኮስት) የኢኮኖሚና ትልቋ ከተማ ወደሆነችው አቢጃን ያቀኑት ብሊንከን፣ በኮትዲቮር ዋና አጀንዳቸውን በምግብ ዋስትና ዙሪያ ማድረጋቸውን ቪኦኤ ዘግቧል፡፡

በአቢጃን ከሚገኘው የአፍሪካ ልማት ባንክ ጋርም በምግብ ዋስትና ላይ የሚመክሩ ሲሆን፣ በአይቮሪኮስት እ.ኤ.አ. በ2025 የሚካሄደው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ ዝግጅትም መወያያ ነው፡፡

በአሜሪካም ሆነ በዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ ዘንድ፣ በሳህል ቀጣና በምዕራብ አፍሪካ አገሮች በተደጋጋሚ የሚፈጸመው መፈንቅለ መንግሥት ውግዘት ሲገጥመው ተስተውሏል፡፡

ምንም እንኳን የየአገሮቹ ሕዝቦች በአብዛኛው መፈንቅለ መንግሥቶቹን ደግፈው ጎዳና የወጡ ቢሆንም፣ ይህ በኃያላን አገሮች ዘንድ ተቀባይነት አላገኘም፣ ለቀጣናውም አለመረጋጋት ፈጥሯል፡፡ አሜሪካም በቀጣናው ደኅንነት ለማስጠበቅ እየሠራች ትገኛለች፡፡

 እ.ኤ.አ. በተለይ ከ2020 ጀምሮ በማሊ፣ በቡርኪና ፋሶ በጊኒና ኒጀር የተደረጉት መፈንቅለ መንግሥቶች፣ የምዕራብ አፍሪካ የኢኮኖሚ ማኅረበሰብ (ኢኮዋስ)ን ጭምር የፈተኑ ናቸው፡፡ አይቮሪኮስት ደግሞ መፈንቅ መንግሥት ከተከናወነባቸው አራቱ አገሮች በሦስቱ ማለትም ጊኒ፣ ማሊና ቡርኪናፋሶ ጋር የምትዋሰን መሆኗ የፀጥታ ስጋት ሆኖባታል፡፡

አሜሪካም አይቮሪኮስትና አጎራባች አገሮች ግጭትን እንዲቆጣጠሩና የቀጣናውን የሽብር ሥጋት እንዲያስወግዱ የ45 ሚሊዮን ዶላር አዲስ ድጋፍ ለማድረግ ማቀዷም ተሰምቷል፡፡

አሁን አሜሪካ ያቀደችው የ45 ሚሊዮን ዶላር ድጋፍ ሲታከል፣ አሜሪካ ከ2022 ወዲህ በምዕራብ አፍሪካ በአትላንቲክ ደሴቶች ለሚገኙ አገሮች  ያደረገችው ድጋፍ 300 ሚሊዮን ዶላር ይደርሳል፡፡

የአሜሪካ ተቀናቃኞች ተደርገው የሚቆጠሩት ቻይናና ሩሲያ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ በአፍሪካ ያላቸው ተፅዕኖ እየጎላ መጥቷል፡፡

ቻይና ለመሠረተ ልማት ፕሮጀክቶች ብድርና ድጋፍ ስታመቻች፣ ሩሲያም ወታደራዊ ትብብር ታደርጋለች፡፡

አሜሪካ በቀጣናው ሽብርን ለመከላከል ከአገሮቹ ጋር እየሠራች ሲሆን፣ ኒጀርም 1,000 ያህል የአሜሪካ ወታደሮች በአገሯ እንዲቀመጡ ፈቅዳለች፡፡

አንቶኒ ብሊንከን በአራቱ የምዕራብ አፍሪካ አገሮች ጉብኝታቸውን ሲጀምሩ፣ በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የአሜሪካ አምባሳደር ሊንዳ ቶማስግሪን ፊልድ በፊናቸው፣ ሦስት ተጨማሪ የምዕራብ አፍሪካ አገሮችን እየጎበኙ ነው፡፡

አምባሳደሯ ሊንዳ፣ በጊኒ ቢሳዋ፣ በሴራሊዮንና በላይቤሪያ በሚኖራቸው ቆይታ፣ የአፍሪካ ዴሞክራሲ እየገጠመው ስላለው ፈተና፣ በደኅንነትና በተያያዥ ጉዳዮች ዙሪያ እንደሚመክሩ በተመድ የአሜሪካ ሚሽን አስታውቋል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...