Thursday, February 29, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን ከአውሮፓ የመጡ የረዥም ጊዜ ወዳጃቸውን እያዘዋወሩ በአዲስ አበባ የተገነቡ ፓርኮችንና በግንባታ ሒደት ላይ የሚገኘውን ሳተላይት ከተማ ካስጎበኙ በኋላ በአንድ ሬስቶራንት ውስጥ አረፍ ብለው እየተጨዋወቱ ነው]

 • እሺ እንዴት አገኘኸው?
 • ጥሩ ነው።
 • ጥሩ ነው ብቻ? እስኪ ደግሞ እነዚህን ፎቶዎች ተመልከት።
 • እነዚህ ደግሞ ምንድናቸው?
 • በተለያዩ አካባቢዎች የገነባናቸው የቱሪስት መዳረሻ ሪዞርቶች ናቸው።
 • ኦ… በጣም ድንቅ ናቸው።
 • በተቻለን አቅም አገር ለመለወጥ እየሞከርን ነው።
 • ጥሩ ጅማሮ ነው።
 • ወደድከው አይደል።
 • እኔማ ወድጄዋለሁ፣ ግን…
 • ግን ምን?
 • ከመጣሁ ጀምሮ ያገኘዋቸው ወዳጆቼ እንዲሁም ስዘዋወር የምሰማው ግን ምሬት ነው።
 • የምን ምሬት?
 • ብዙዎቹ ከአዲስ አበባ ወጣ ብሎ በሰላም መመለስ አስቸገሪ እንደሆነና በኑሮ ውድነት መቸገራቸውን ነው የሚያወሩት።
 • ሲያጋንኑ ነው፡፡
 • ብቻ በምሬት ነው የሚያወሩት።
 • ሲያጋንኑ ነው እያልኩህ?
 • ከመጣሁ ጀምሮ የምሰማው መንግሥት የማኅበረሰቡን አንገብጋቢ ችግሮች ቅድሚያ ሰጥቶ ከመፍታት ይልቅ የፓርኮች ግንባታን መርጧል የሚሉ በምሬት የተሞሉ ትችቶችን ነው።
 • አሱን እኛም እንሰማለን፡፡ አዲስ ቤተ መንግሥትና ፓርኮችን መገንባት ምን ትርጉም አለው የሚሉ ድምጾች መኖራቸውን እናውቃለን። ነገር ግን ግን…
 • እ…?
 • ያው ማኅበረሰባችንን ታውቀዋለህ አይደል?
 • ማለት?
 • ነገሮችን በቶሎ አይረዳም ማለቴ ነው።
 • አለመረዳት ነው ብለህ ነው?
 • ሌላ ምን ሊሆን ይችላል?
 • የማኅበረሰቡ ቅሬታ መንግሥት ፍላጎቴን አልተረደም። ቅደሚያ የሚሰጣቸው ነገሮች በሙሉ የማኅበረሰብን ችግር የሚፈቱ አይደሉም የሚል ነው። ይህ ደግሞ ተገቢ ቅሬታ እንጂ ተቃውሞ ወይም አለመረዳት አልመሰለኝም።
 • አይ… አለመረዳት ነው። ምን አለ በለኝ ትንሽ ቆይቶ ሲያመሠግን ትሰማለህ።
 • አንድ ነገር አስታወስከኝ።
 • ምን?
 • The Mouse Land የሚባለውን ተረት።
 • ሰምቼ አላውቅም። የምን ተረት ነው?
 • ፍልስፍና አዘል ተረት ነው። የአማርኛ ፍቺው ‹‹የአይጦች አገር›› ይመስለኛል።
 • እሺ…?
 • አይጦች ናቸው አሉ… የጋራ ችግራቸውን የሚፈታላቸውና የሚያስተዳድራቸው መንግሥት መመሥረት አለብን ብለው ምርጫ ያካሂዳሉ።
 • እሺ…
 • ድምፅ ሲቆጠር ያሸነፈው ግን ድመት ሆኖ ተገኘ።
 • እሺ…
 • ሥልጣን ላይ የወጣው ድመት በራሱ ዕይታ ጥሩ ናቸው የሚላቸውን ሕጎችና ፖሊሲዎችን ማውጣት ጀመረ።
 • እሺ፡፡
 • አይጦች ግን አልወደዱትም።
 • ለምን?
 • ምክንያቱም የሚያወጣቸው ሕጎችና ፖሊሲዎች ለአይጦች የሚመቹ አልነበሩም።
 • ባይመቻቸውም መቀበል አለባቸው!
 • ለምን?
 • በምርጫ የመጣ መንግሥት ነዋ!
 • ቢሆንም የሚያወጣቸው ፖሊሲዎችና ሕጎች የአይጦችን ሁኔታ ያገናዘበ አይደለማ።
 • እንዴት?
 • ለምሳሌ መጀመሪያው ያወጣው ሕግ በአይጥ አገር መራመድ እንጂ መሮጥ አይቻልም የሚል ነበር።
 • የትራፊክ አደጋን ለመቀነስ የሚጠቅም ጥሩ ሕግ ይመስለኛል።
 • ነገር ግን ለአይጦች የሚስማማ አይደለም፣ ያጠፋቸዋል።
 • ለምን ያጠፋቸዋል?
 • አይጦች ካልሮጡ ድመትን ማምለጥ አይችሉማ።
 • እህ… እሺ…
 • በዚህም ምክንያት አይጦች በመንግሥት ላይ አመፁ።
 • ማመፅን ምን አመጣው።
 • ታዲያ ምን ማድረግ ይችሉ ነበር?
 • በሰላማዊና ሕጋዊ መንገድ አይፈቱትም?
 • በሰላማዊ መንገድ ነው የፈቱት።
 • እንዴት ፈቱት?
 • አመጽ አካሂደው የነበረውን መንግሥት አወረዱ፣ ከዚያም አዲስ መንግሥት ለመምረጥ ምርጫ አዘጋጁ።
 • ምርጫ ማካሄዳቸው ጥሩ ነው።
 • ምን ዋጋ አለው?!
 • እንዴት?
 • አዲስ ምርጫ አካሂደው ድምፅ ሲቆጠር አሁንም ያሸነፈው ሌላ ድመት ሆኖ ተገኘ።
 • እንከን የለሽ ምርጫ ከነበረ ውጤቱን በፀጋ መቀበል አለባቸው።
 • ምርጫው ዴሞክራሲያዊ ቢሆን ምን ዋጋ አለው።
 • እንዴት?
 • በሁለተኛው ምርጫ ሥልጣን ላይ የወጣው ድመትም ወዲያውኑ ተመሳሳይ ስህተት መሥራት ጀመረ።
 • የምን ስህተት?
 • በድመት ዕይታ ጥሩ የሚባሉ ነገር ግን ለአይጦች የማይመቹ ሕጎችን ማውጣት ጀመረ።
 • ችግሩ ከሕጉ ሳይሆን ከአይጦች ነው የሚመስለው።
 • ለምን እንደዚያ አልክ?
 • በምርጫ የመጣ መንግሥት ነዋ።
 • አይ አንተ…
 • እንዴት?
 • በምርጫ የመጣ መንግሥትም ቢሆን የሕዝብን የቅድሚያ ፍላጎትና መሠረታዊ ችግር ያላጤነ ከሆነ ትርጉም የለውማ?
 • ቆይ፣ ሥልጣን ላይ የወጣው ድመት ያወጣው ሕግ ምንድነው?
 • በመጀመሪያ ያወጣው ሕግ ምን መሰለህ?
 • እ…?
 • የአይጥ ቤት አይጥን ብቻ ሳይሆን ድመትንም የሚያስገባ መሆን አለበት የሚል ነበር።
 • አካታች የሆነ ሕግ ነው።
 • በድመት አይን ካየኸው ነዋ።
 • ለአይጦችስ ቢሆን?
 • አደጋ ነው።
 • ለምን?
 • ድመት የሚያስገባ ቤት ውስጥ መኖር ለአይጥ የህልውና አደጋ ነዋ።
 • እህ… በዚያ መልኩ አላየሁትም ነበር።
 • ገብቶኛል።
 • እንዴት ሊገባክ ቻለ?
 • ከመጣሁ ጀምሮ በአገሪቱ ያስተዋልኩት ይህንኑ ነው።
 • ምንድነው እሱ?
 • ነገሮችን ከአንድ አቅጣጫ፣ ከራስ በኩል ብቻ ማየት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...

የጋራ ድላችን!

ከፒያሳ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ለበርካታ ደቂቃዎች ሠልፍ ይዘን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ ነው የሚደንቀው? የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ? በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን...

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...