Thursday, February 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የዱሮው መምህር ተግባርና እጣፋንታ በተመስገን ገብሬ ዓይን

ትኩስ ፅሁፎች

‹‹ኑሬ እውር ነው። ግን ለተማሪዎች ሁሉ የሚያስደንቅ ብርሃን ነበር፡፡ እኛ ጭቃማ በሆነው በጠባቡ መንገድ መራነው፡፡ እርሱ ግን በተሻለው በእውቀት መንገድ መራን፡፡ ምሽት የለውም። ግን የሁላችን አባት ነበር፡፡ ወላጆቻችን ገንዘብ ስላልከፈሉት ይርበው ነበር። እና ግን ብዙ በሆነ ጊዜ ረሃብን ይረሳው ነበር፡፡ በፈቃዱ ነውና የሚያስተምራቸው ብለው አባቶቻችን ገንዘብ መክፈል ሲከለክሉት እርሱ እንደወላጆቻችን ጨካኝ አይደለምና ትምሕርት አልከለከለንም፡፡ እርሱ እጅግ አጭር እጅግ ደግሞ ቀጭን ነው፡፡ ግን የታላቂቱን ቤተ ክርስቲያን የደብረ ማርቆስ ጠንካራው ምሰሶ እርሱ ነበር፡፡ ሰውን ሁሉ ለመውደድ ይፈቅዳል፤ ግን ያልታደለ ነውና በሁሉ ዘንድ የተናቀና የተጠላ ዕውር ነበር፡፡ ከተማሮቹ በቀር ወዳጅ አልነበረውም፡፡››

ይህ አጭር ጽሑፍ የተወሰደው ከተመስገን ገብሬ ግለታሪክ (ሕይወቴ ገጽ 21) ነው፡፡ በወቅቱ የነበረውን የመምህር ሚናና መስዋእትነት፣ የኅብረተሰቡን ግዴለሽነትና ጭካኔ፣ የተማሪዎቹን ትዝብት ቁልጭ አድርጎ የሚያሳይ፣ ዛሬ ላለንውም መምህራን፣ ኅብረተሰብና ተማሪዎች ራሳችንን እንድናይ ጥሩ ማነጻጸሪያ ሆነናል ብዬ አምናለሁ፡፡

መምህሩ አካላዊ ብርሃን የለውም፤ ግን ውስጣዊና መንፈሳዊ፣ እንዲሁም ኅሊናዊ ሚዛኑ በከፍታ ቦታ ላይ የተቀመጠ እጅግ ሥሙር (በተማሪዎቹ የተወደደ) ነበረ፡፡ ለመምህርስ በተማሪዎቹ የመከበርና የመወደድ ቀለብ በላይ ምን አለ? ለዚህ ዓይነቱ ፀጋና መስዋእትነት ስንቶቻን እንተጋ ይሆን? ኅብረተሰብስ መቼ ይሆን ወደ ቅን ልቦናው ተመልሶ ለመምህር፣ ለትምህርትና ለተማሪዎች (ለልጆቹ) ማኅበራዊ ትኩረቱንና ኃላፊነቱን የሚወጣው? እነዚህን ወገኖች በወግ በወጉ የሚያስተዳድረው መንግሥትስ መቼ ነው የሁለሙ የአገር ጉዳይ መሠረት ስለሆነው መምህርና ትምህርት ከተመስገን ዘመን ጨካኝነት ወጥቶ በርኅራኄና በቅን ልቦና ማሰብና ማተኮር የሚጀምረው? መቼስ ነው የትምህርት ጉዳይ፣ የመምህር ጉዳይ ሲነሳበት አፍአዊ ከሆነ ማማለል የሚወጣውና ሺ ምንተሺ የሆነ ምክንያት ከመዘርዘር የሚቆጠበው?

  • ደረጀ ገብሬ
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች