Thursday, February 29, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ  የኢትዮጵያ ዲያስፖራ አባላትን በአዲስ አበባ የተለያዩ አካባቢዎች እያዞሩ እያስጎበኙ ከአንድ ዲያስፖራ ጋር እየተወያዩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር የዛሬ ሁለት ዓመታት ገደማ ወደ አዲስ አበባ መጥቼ ከተማዋን ጎብኝቼ ነበር።
 • እውነት?
 • አዎ።
 • ታዲያ ልዩነቱን እንዴት አዩት?
 • በጣም ይደንቃል። ሌላ ከተማ እኮ ነው የመሰለችው።
 • አይደል?
 • አዎ። እንዴት ነው ግን ይህንን ሁሉ በአጭር ጊዜ ልትሠሩ የቻላችሁት?
 • ቁርጠኛ አመራር ካለ የማይቻል ነገር የለም።
 • ወጪውስ?
 • የምን ወጪ?
 • የሠራችሁት ሥራ ቁርጠኛ አመራር ብቻ ሳይሆን ትልቅ ወጪ የሚጠይቅ መሰለኝ።
 • ይህንን የመሰለ ለውጥማ ያለ ወጪ አይመጣም። ትልቅ ሀብት ነው የፈሰሰበት።
 • እሱን እኮ ነው የምለው።
 • ምኑን?
 • ከፍተኛ የውጭ ዕዳ እንዳለባችሁና በቅርቡም በዩሮ ቦንድ የተበደራችሁትን መክፈል እንዳልቻላችሁ ተወርቷል።
 • ተዋቸው ባክህ። ሆነ ብለው ስማችንን ለማጠልሸት የነዙት መረጃ ነው።
 • እንጂ ችግር የለባችሁም?
 • የለብንም።
 • ለነገሩ አዲስ አበባ ከተማን በዚህ መልኩ ቀይራችሁ ችግር ውስጥ ናችሁ ለማለት ይከብዳል። የሆነ ያገኛችሁት ነገር ሳይኖር ግን አይቀርም።
 • ምን እናገኛለን ብለህ ነው?
 • ነዳጅ?
 • ገና ወደ ሥልጣን እንደመጣን ሶማሌ ክልል ይኖራል ብለን ገምተን ነበር።
 • ምን?
 • ነዳጅ።
 • እና?
 • እስካሁን ግን አላገኘነውም።
 • ነዳጅ ሳታገኙ አዲስ አበባን በዚህ ደረጃ መቀየራችሁ ድንቅ ነው። ግን…
 • ግን ምን?
 • የከተማዋ ነዋሪ ሕይወትና አኗኗር ግን ብዙም አልተለወጠም።
 • ልክ ነው፡፡ እሱ ላይ ብዙ ሥራ መሥራት ይኖርብናል።
 • ታዲያ ቅድሚያ በፓርክና በመናፈሻ ልማት ማተኮራችሁ ትክክል ነው።
 • ይህንንም ያደረግነው ለሕዝቡ ስንል ነው።
 • እንዴት?
 • የኢትዮጵያ ሕዝብ አማኝ እንደሆነ ታውቃለህ አይደለም።
 • አዎ በሚገባ።
 • አብዛኛው የኢትዮጵያ ሕዝብ ደሃ መሆኑንም ታውቃለህ አይደለም።
 • አዎ!
 • ታዲያ የኢትዮጵያ ሕዝብ የሚጾመውና የሚጸልየው ለምን ይመስልሃል?
 • ያው ፈሪሃ እግዚያብሔር ያለው ሕዝብ በመሆኑ ይመስለኛል።
 • እሱ ብቻ አይደለም?
 • ሌላ ሊሆን የሚችለው ፈጣሪ ኑሮውን እንዲያሻሽልለት፣ ልጆቹን እንዲባርክለትና ጤና እንዲሰጠው ይመስለኛል።
 • እሱ ብቻ አይደለም።
 • ታዲያ ለምንድነው?
 • ገነትን ለመግባት ነው።
 • ታዲያ እናንተ ፓርክና መናፈሻ መገንባት ላይ መጠመዳችሁ ከዚህ ጋር ምን ያገናኛዋል?
 • ገነት ማለት እኮ ጥሩ ዛፍ፣ ጥሩ ሽታና ጥሩ አበባ ማለት ነው።
 • ነው እንዴ?
 • እናሳ?
 • ስለዚህ ፓርክና መናፈሻ የምታለሙት ለምንድነው ማለት ነው?
 • ለሕዝባችን እዚሁ ማውረስ ስለምንፈልግ ነው።
 • ምን?
 • ገነትን።
 • እንደዛ ከሆነማ ሕዝቡም ከዚህ በኋላ ለመንግሥት ነው ማድረስ ያለበት።
 • ምኑን?
 • ጾምና ፀሎቱን።
 • በል ጉብኝቱ እዚህ ላይ ይበቃናል።
 • ምነው ክቡር ሚኒስትሩ?
 • ይጠብቁኛል።
 • ማን?
 • ሌሎች ጎብኚዎች።

[ክቡር ሚኒስትሩ  ከተለያዩ ክልሎች የተውጣጡ የወጣት ሊግ አባላትን እያዘዋወሩ ካስጎበኙ በኋላ የጉብኝቱን ማሳረጊያ በረዥሙ የንግድ ባንክ ሕንፃ ሰገነት ላይ አድርገዋል]

 • አሁን የምንገኘው ረዥሙ የከተማችን ሕንፃ ላይ ነው።
 • እንዴ ክቡር ሚኒስትሩ እዘያ ወዲያ የሚታየው ቤተ መንግሥቱ ነው አይደል?
 • አዎ። ልክ ነው።
 • በምዕራብ በኩል እዚያ ጋር የምትመለከቱት መናገሻ ተራራ ነው።
 • ኦ! ልክ ነው።
 • እዚያ ጋር የምትመለከቱት ደግሞ ወጨጫ ተራራ ነው።
 • ብቻ ምን አለፋችሁ ከዚህ ሕንፃ ላይ ሙሉ አዲስ አበባን መመልከት ትችላላችሁ።
 • አዲስ አበባ ነው ያሉት ክቡር ሚኒስትር?
 • እ…?
 • ከዚህ ላይ
 • እ…?
 • ምን የማይታይ ነገር አለ ክቡር ሚኒስትሩ?
 • ሌላ ምን ይታያል?
 • ከዚህ ላይ ክቡር ሚኒስትሩ?
 • እ…
 • ያገኘነው ወደብ ይታያል!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ...

በኦሮሚያ የሚፈጸሙ ግድያዎችና የተጠያቂነት መጥፋት

የካቲት 11 ቀን 2016 ዓ.ም. ቢሾፍቱ አቅራቢያ በሚገኘው የዝቋላ...

የኢትዮጵያ መዋዕለ ንዋይ ገበያ ከሚያስፈልገው ካፒታል ውስጥ 90 በመቶውን ሰበሰበ

እስካሁን 15 ባንኮች የመዋዕለ ንዋይ ገበያው ባለድርሻ ሆነዋል የኢትዮጵያ መዋዕለ...

አዲሱ የንብ ባንክ ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር ቢሊዮን ብር ለማሳደግ ማቀዱ ተሰማ

አዲሱ የንብ ኢንተርናሽናል ባንክ የዳይሬክተሮች ቦርድ የባንኩን ካፒታል በአሥር...

የጋራ ድላችን!

ከፒያሳ ወደ ቄራ ልንጓዝ ነው። ለበርካታ ደቂቃዎች ሠልፍ ይዘን...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ። ምኑ? ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡ ምኑ ነው የሚደንቀው? የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ? በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን...

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት። ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው? ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት ሞባይል ስልካቸው ላይ አተኩረው ሲመለከቱ ቆይተው፣ በድንገት ካቀረቀሩበት ቀና ብለው ባቤታቸውን ጠየቁ]

ምን ጉድ ነው የማየው? ምን ገጠመሽ? የመንግሥት ሚዲያዎች የሚያሠራጩት ምንድነው? ምን አሠራጩ? አልሰማህም? አልሰማሁም፣ ምንድነው? ዳግማዊ አፄ ምኒልክ መልዕከት አስተላለፉ እያሉ ነው እኮ። እ... እሱን ነው እንዴ? አዎ። የምታውቀው ነገር አለ? አዎ። የዓድዋ...