- Advertisement -

‹‹ሰው ሲራብ ቆሞ መመልከት የሞራልና የፖለቲካ ኪሳራ ነው›› ኦክስፋም ኢንተርናሽናል

ኦክስፋም ኢንተርናሽናል በትግራይ ክልል ጦርነትና የዝናብ እጥረት ያስከተለውን የከፋ የሰብዓዊ ቀውስ ጠቅሶ፣ ‹‹ሰው ሲራብ ቆሞ መመልከት የሞራልና የፖለቲካ ኪሳራ ነው፤›› ሲል አስታወቀ፡፡

ኦክስፋም ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው መግለጫ፣ በረሃብ የተጠቁ ቤተሰቦች ችግሩን ለማምለጥና በሕይወት ለመትረፍ ሲሉ የመጨረሻ ተስፋ አስቆራጭ ዕርምጃዎችን እየወሰዱ መሆናቸውን አስታውቋል፡፡

በአንድ ትምህርት ቤት ከተጠለሉ ቤተሰቦች መካከል አናገርኳቸው ብሎ ኦክስፋም  በመግለጫው ያሠፈራቸው እናቶች፣ ልጆቻቸው ተርበው ቀኑን በሙሉ የሚያበሏቸው ነገር ማጣታቸውን፣ ልጆቻቸው ረሃቡን ሊቋቋሙ ባለመቻላቸው የረሃብ ሕመምን ለማስታገስ ለረጅም ሰዓታት እንዲተኙ እንደሚያስገድዷቸውና ለእንስሳት የሚሆኑ ሥራ ሥሮችን ለመመገብ መገደዳቸውን መናገራቸውን ገልጿል፡፡ ነፍሰ ጡርና የሚያጠቡ እናቶች በረሃብ እየተሰቃዩ መሆናቸውንም አክሏል፡፡

የሕዝብ ዕንባ ጠባቂ ተቋም ከአንድ ሳምንት በፊት ባወጣው መግለጫ፣ በፌዴራል ተቋማትና በአማራና በትግራይ ክልሎች የሚመጣው የዕርዳታ ጠባቂዎች መረጃ የተዛባ መሆኑን የሚያመለክት የዳሰሳ ጥናት ይፋ ማድረጉ ይታወሳል፡፡

በተቋሙ በወጣው ጥናት በትግራይ ክልል 355 ሰዎች፣ እንዲሁም በአማራ ክልል 23 ሕፃናት በምግብ እጥረት ተገቢውን ዕድገት ባለማግኘታቸው ሞተው ሲወለዱ፣ 21 ሰዎች ድርቁ ባስከተለው ረሃብ መሞታቸውን ገልጾ ነበር፡፡

ይሁን እንጂ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ባለፈው ሳምንት በሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ማብራሪያ ሲሰጡ ‹‹ድርቅ ለኢትዮጵያውያን ልክ እንደ ባህላችንና እንደ ዓድዋ ድል ለ100 ዓመታት ሲጎበኘን የቆየ ጉዳይ በመሆኑ፣ እንደ አዲስ ሊወራ የሚችል ነገር አይደለም፤›› ብለው ነበር፡፡

- Advertisement -

‹‹ድርቁን መንግሥት አላመጣውም፣ እንደ ፖለቲካ ማየት የለብንም፡፡ የአየር ንብረት ለውጥ ችግር አለ፣ ችግኝ እንትከል ሲባል ችግኝ ምን ያደርጋል? ድርቅና ረሃብ አለ ስንዴ እናምርት ሲባል ስንዴ ምን ያደርጋል? ካልን በኋላ ድርቅ መጣ ብለን ብንጮኸ ትርጉም የለውም፤›› ሲሉም አስረድተዋል፡፡

‹‹ድርቁን ለፖለቲካ መጠቀም ጥፋት ነው፤›› ያሉት ጠቅላይ ሚኒስትሩ፣ ባለፉት አራት ወራት 500 ሺሕ ኩንታል ያህል በመንግሥትና በተራድኦ ድርጅቶች ትብብር ለተረጂዎች መላኩን ተናግረዋል፡፡

‹‹ይህ ሀብት በቂ ካልሆነ ደግሞ የኢትዮጵያ መንግሥት አቅም እያለው በረሃብ የሚሞት ሰው ዓይተን ዝም አንልም፤›› ብለዋል፡፡

‹‹እስካሁን ባለኝ መረጃ በረሃብ ምክንያት የሚሞት ሰው የለም፤›› ብለው፣ መንግሥት ትናንት እንዳደረገው ዛሬም የሚራብ ሰው ካለ ፕሮጀክት አቁሞ በረሃብ እንዳይሞት ከሕዝቡ፣ ከባለሀብቶችና ከክልል መንግሥት ጋር በመሆን የሚችለውን ሁሉ እንደሚሠራ ገልጸው ነበር፡፡

የትግራይ ክልል ጊዜያዊ አስተዳደር ፕሬዚዳንት አቶ ጌታቸው ረዳ ከቀናት በፊት ስለጉዳዩ በሰጡት ማብራሪያ፣ በክልል የከፋ ረሃብ መከሰቱንና ሞትን በዓይናቸው የሚያዩ ዜጎች ቁጥር እየጨመረ መምጣቱን ጠቅሰው፣ ለዓለም አቀፉ ማኅበረሰብ የዕርዳታ ጥሪ አቅርበው ነበር፡፡

የኦክስፋም የኢትዮጵያ ዋና ዳይሬክተር አቶ ገዛኸኝ ‹‹አሁን የሚታየው የችግሩ ጫፍ እንደሆነ፣ በሚሊዮኖች የሚቆጠሩ ዜጎች አስከፊ የሆነ ረሃብ ውስጥ ሊገቡ እንደሚችሉና ዜጎች ቀጣዩን ምግባቸውን ማግኘት ከባድ የሆኑ መንገዶችን እያለፉ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዓለም አቀፍ ደረጃ አስከፊ ከሆኑ የሰብዓዊ ቀውስ ክስተቶች አንዱ ለሆነው የሰሜን ኢትዮጵያ የዕርዳታ አቅርቦት፣ ይጠበቅ ከነበረው አራት ቢሊዮን ዶላር ማግኘት የተቻለው 34 በመቶ ብቻ መሆኑን ኦክስፋም በመግለጫው ጠቁሟል፡፡

አፋጣኝ የሰብዓዊ ዕርዳታ አቅርቦት ካልተደረገ የበርካታ ዜጎች ሕይወት አደጋ ውስጥ መሆኑን ዋና ዳይሬክተሩ ተናግረዋል፡፡ በተመሳሳይ ኮንሰርን ወርልድ ዋይድ የተሰኘው ዓለም አቀፍ ድርጅት ዓርብ የካቲት 1 ቀን 2016 ዓ.ም. ባወጣው ሪፖርት፣ በኢትዮጵያ የተከሰተው ረሃብ አሳሳቢ ደረጃ ላይ መድረሱን አስታውቋል፡፡

በአፋር፣ በአማራና በትግራይ ክልሎች የተከሰተው የተመጣጠነ ምግብ እጥረት በዓለም አቀፍ ደረጃ ዕውቅና ከተሰጣቸው መሰል ክስተቶች እጅግ የላቀ መሆኑን ድርጅቱ በሪፖርቱ አመላክቷል፡፡

- Advertisement -

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን

ከ ተመሳሳይ አምዶች

በተያዘው ወር መጨረሻ  አዲስ ፖስፖርትና ቪዛ  ይፋ ይደረጋል ተባለ

በውጭ አገር የሚታተመውን ፓስፖርትና አገሪቱ ለውጭ ዜጎች የምትሰጠውን ቪዛ በአዲስ ይዘትና ኅትመት በአገር ውስጥ ታትሞ በተያዘው ወር የካቲት 2017 ዓ.ም. ይፋ እንደሚደረግ የኢሚግሬሽንና ዜግነት...

በውጭ አገር ለሚሰጥ ሕክምና የአገር ውስጥ ተወካይ ኃላፊነት እንዲወስድ የሚያስገድድ ረቂቅ መመርያ ተዘጋጀ

የጤና ሚኒስቴርን ፈቃድ አግኝተው በውጭ አገሮች የሕክምና አገልግሎት ተቋማት የሚታከሙ ኢትዮጵያውያን፣ የሕክምና አገልግሎት ጥራት ደረጃ ጉድለት፣ የሕክምና ስህተት ወይም የሙያ ግድፈት ቢፈጸምባቸው፣ የውጭ ሕክምና...

በአማራ ክልል የአሽከርካሪዎች ዕገታን መደበኛ የሥራ ቦታ አድርጎ የሚንቀሳቀሰው መበራከቱ ተገለጸ

በአማራ ክልል ከጊዜ ወደ ጊዜ እየጨመረ የመጣው የአሽከርካሪዎች ዕገታ በአሁኑ ወቅት ክፍት የሥራ ቦታ እየሆነ መምጣቱ ተነገረ፡፡ አሽከርካሪዎችን በማገት ከፍተኛ ገንዘብ የሚጠይቁና ሲያዙም በአግባቡ በሕግ...

የባሕር ዳርና ድሬዳዋ ኤርፖርቶች የሲቪል በረራዎች ቁጥጥር ስርዓታቸውን አሳደጉ

በኢትዮጵያ ከሚገኙት አራት ዓለም አቀፍ ኤርፖርቶች መካከል የሆኑት የባህር ዳርና የድሬዳዋ ኤርፖርቶች፣ የአየር በረራዎች ቁጥጥር ክፍሎች ከጥር ወር 2017 ዓ.ም. ጀምሮ ማናቸውንም እስከ 25...

ኢትዮ ቴሌኮም አገልግሎቱን በርካሽ ዋጋ ማቅረቡ ከተወዳዳሪው ኩባንያ ቅሬታ እየቀረበበት መሆኑን አስታወቀ

ኢትዮጵያ ቴሌኮም ጉልህ የገበያ ድርሻ እያለው አገልግሎቱን በርካሽ ዋጋ ማቅረቡ ለተወዳዳሪው ኩባንያው ውድድሩን አስቸጋሪ ስላደረገበት፣ ‹‹መንግሥታዊ ኩባንያው ዋጋ እንዲጨምር መገደድ አለበት የሚል የቅሬታ ጥያቁ...

በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት 39 ምድብ ችሎቶች ከአገልግሎት ውጪ መሆናቸው ተረጋገጠ

በስድስት ወራት 89 ዳኞች ሥራ መልቀቃቸው ተነግሯል የክልሉ ዳኞች ያለመከሰስ መብት ተጠበቀላቸው በአማራ ክልል በፀጥታ ችግር ምክንያት ከ221 ፍርድ ቤቶች 39 የዞንና የወረዳ ምድብ ችሎቶች አገልግሎት...

አዳዲስ ጽሁፎች

የጤናው ዘርፍ ባለፉት ስድሥት ወራት

የወባ በሽታ ከሰሃራ በታች በሚገኙ የአፍሪካ አገሮች ዋነኛ የጤናና የማኅበራዊ ቀውስ መንስዔ ነው፡፡ የዓለም ጤና ድርጅት እ.ኤ.አ. በ2024 ያወጣው መረጃም 263 ሚሊዮን ሰዎች የወባ...

የአዲስ አበባ የኮሪደር ልማት በባለሙያ ዓይን

(በጎ ጎኖችና እርምት የሚፈልጉ ጉዳዮች) በዮሐንስ መኮንን በጥር ወር 2016 ዓ.ም. የአዲስ አበባ ዋና ዋና ኮሪደሮችን በማዘመን ከተማዋን ለነዋሪዎቿና ለጎብኚዎቿ ምቹ ያደርጋታል የተባለ ፕሮጀክት በ43 ቢሊዮን...

በልዩነት ውስጥ ሆነንም እስኪ እንነጋገር

በገነት ዓለሙ ዴሞክራሲ መብቶችና ነፃነቶች የሚሠሩበት የሕዝብ አስተዳደር ነው፡፡ ሰብዓዊ መብቶችንና ነፃነቶችን መኗኗሪ ያደረገ ሥርዓት ነው፡፡ እነዚህ መሠረታዊ መብቶችና ነፃነቶች በተፈጥሮ የተገኙ፣ ሰው በመሆናችን ብቻ...

ለጤናማ የትራፊክ ፍሰትና ለመንገድ ደኅንነት ቅጣት መጣል ብቻውን መፍትሔ አይሆንም!

በአዲስ አበባ ከተማ ለተሽከርካሪዎች ምቹ የሆኑ መንገዶችን እየተመለከትን ነው፡፡ ከአዳዲሶቹ መንገዶች ባሻገር አንዳንድ ነባር መንገዶች የማስፋፊያ ሥራ ታክሎባቸው አገልግሎት ላይ ውለዋል፡፡ ከኮሪደር ልማቱ ጋር...

የግጭት አዙሪት ውስጥ ሆኖ የአፍሪካ ማዕከል መሆን ያዳግታል!

የአፍሪካ ኅብረት 38ኛው የመሪዎች ጉባዔ በአዲስ አበባ ሲካሄድ ብዙ ትዝ የሚሉ ጉዳዮች አሉ፡፡ እጅግ በጣም አሰልቺ፣ ውጣ ውረድ የበዛበትና ታላቅ ተጋድሎ ተደርጎበት ከከፍተኛ ዲፕሎማሲያዊ...

አገሬ ምንተባልሽ – ልብ ያለው ልብ ይበል

በቶማስ በቀለ ይቺ አገራችን ብዙ ተብሎላታልም፣ ብዙ ተወርቶባታልም፣ አገሪቱ በቅኝ ያልተገዛች ብቸኛ አገር (ላይቤሪያን ጨምሮ) ከመሆኗ አኳያ የሚነገርላት ብዙ ጥሩና የሚገርሙ ነገሮች ያሉትን ያህል፣ ከረሃብ...
[the_ad id="124766"]

በማህበራዊ ሚዲያዎች ይከታተሉን