Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊየወጣቶች አሻራ ያረፈበት የፐርፐዝ ብላክ ከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን

የወጣቶች አሻራ ያረፈበት የፐርፐዝ ብላክ ከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን

ቀን:

ቴክኖሎጂን መሠረት በማድረግ በኢትዮጵያ የተሻለ ኢኮኖሚ ለመገንባትና ድህነትን ለመቅረፍ እየሠራ እንደሚገኝ የገለጸው ፐርፐዝ ብላክ ኢትዮጵያ፣ በኢትዮጵያ የአሠራር ሥርዓት ላማቀላጠፍ አስተዋጽኦ ያበረክታሉ ያላቸውን የከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ይፋ አድርጓል፡፡

ቴክኖሎጂው ጥር 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ይፋ መደረጉን አስመልክቶ በተዘጋጀው መድረክ፣ በቀጣዮቹ ወራት ፐርፐዝ ብላክ ወደ ሆልዲንግ ካምፓኒ ተቀይሮ በሥሩ 16 ተመጋጋቢ (ሰብሲደሪ) ኩባንያዎች እንደሚያቋቁም የፐርፐዝ ብላክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍስሐ እሸቱ (ዶ/ር) ገልጸዋል፡፡

ወደ ሆልዲንግ ለመሸጋገር የሰብሲደሪ ካምፓኒ እንደሚያስፈልግ በመጠቆም፣  የከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን አንድ ብሎ ይፋ ሆኗል ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በዚህ ሶሉሽን ሥር ስድስት ፕላትፎርሞች ያሉ ሲሆን፣ የኢትዮጵያን የዲጂታል ቴክኖሎጂ እንደሚያፋጥኑ ተስፋ ተጥሎባቸዋል፡፡

ዓለም ስለግብርናና ስለኢንዱስትሪ ማውራት ትቶ ወደ አርቴፊል ኢንተለጀንስ (ሰው ሠራሽ አስተውሎት) ገብቷል፣ ዓለም ጥሎን ሄዷል፣ ለዚህም ብዙ መሥራት ይጠበቅብናል ብለዋል፡፡

ፐርፐዝ ብላክ ብዙ ዕቅድና ራዕይ ይዞ መነሳቱን በመጠቆምም፣ የጥቁሩ ዓለምና የሌላው ዓለም የኢኮኖሚና የዲጂታል ቴክኖሎጂ ልዩነት ሰፊ መሆኑን ይህንን ለማጥበብም መሥራት እንደሚጠበቅ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ የወጣቱን ኃይል፣ ዕውቀትና አቅም ተጠቅሞ ከኢትዮጵያ ቴክኖሎጂን ኤክስፖርት ማድረግ እንደሚቻልና ከዚህ አኳያ ብዙ ዕድል እንዳለ ፐርፐዝ ብላክ እንደሚያምን ፍስሐ (ዶ/ር) ገልጸው፣ ለዚህ የሚያበረታቱ ሁኔታዎች በኢትዮጵያም በአፍሪካም እንዳሉ ጠቁመዋል፡፡

በአፍሪካ ኬንያና ሩዋንዳ በቴክኖሎጂ ኢኮኖሚያቸውን ማበልፀጋቸውን በማስታወስ፣ ቴክኖሎጂን ወደ ኢትዮጵያ አምጥተን ኢትዮጵያን የብላክ ኢኮኖሚ ኤክሰለንሲ እናደርጋለን ብለዋል፡፡

እንደ ፍሰሐ (ዶ/ር)፣ ፐርፐዝ ብላክ ቴክኖሎጂ ላይ መሠረት ያደረገ የኢኮኖሚ ዕድገት መምጣት አለበት ብሎ ያምናል፡፡ ለዚህም እንቅስቃሴውን ከቴክሎጂ ጋር አያይዟል፡፡ በሚመሠርታቸው የፐርፐዝ ብላክ ተመጋጋቢ ድርጅቶች (ሰብሲደሪስ) በቴኖሎጂው ላይ የሚሠራ ይሆናል፡፡

የፐርበዝ ብላክ ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ይፋ ሲደረግም እህት ኩባንያ ለማቋቋም ብቻ ሳይሆን፣ ቴክኖሎጂው ፕላትፎርም ሆኖ መንግሥትን ጨምሮ መላ ኢትዮጵያውያንና ኩባንያዎች የሚጠቀሙበት መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

ገበሬዎችን ደሃ አድርጎ ካስቀራቸው ምክንያቶች አንዱ ምርቶቻቸውን ቀጥታ ለሸማቹ ማቅረብ አለመቻላቸው መሆኑንና ይህ ችግር በተደጋጋሚ እንደሚነሳ በማስታወም፣ ፐርፐዝ ብላክ ይህንን ችግር ለመቅረፍ በቴክኖሎጂው ታግዞ ጀምሮታል ብለዋል፡፡

‹‹ብዙ የለፋንባቸውና ለአገርና ለዓለም ይተርፋሉ›› ያላቸውን የከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ላይ ገለጻ የሰጠው ወጣት አማኑኤል መለሰ፣ ከዚህ በላቀ ዛሬ ከገበሬው ቴክኖሎጂ ሶሉሽን ብለው የጀመሩትን፣ በቀጣይ ከገበሬው ቴክኖሎጂ ሲቲ ለማድረግ ብሎም እንደ ግዙፍ የቴክኖሎጂ ማዕከል ሲልከን ቫሊ ከገበሬው ቫሊ ብለው አሳድገው ፣ከኢትዮጵያውያን የወጣ ቴክኖሎጂ ለዓለም ይዘው እንደሚቀርቡ ገልጿል፡፡

በወጣትና ልምድ ባላቸው ሠራተኞች ተዋቅረው ኢኮሜርስን ጨምሮ ሌሎች ፕላትፎርሞችንም እንደሚሠሩም አክሏል፡፡      

ፐርፐዝ ብላክ በአሁን ሰዓት አጠቃላይ 24 የሚደርሱ የዲጂታል ቴከኖሎጂ ፕላትፎርሞችን በመሥራት ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ ከ24ቱ ስድስቱ የቴከኖሎጂ ውጤቶች ይፋ ሆነዋል፡፡

ይፋ ከሆኑት የቴክኖሎጂ ውጤቶች ውስጥ የከገበሬው የግብርና ምርቶች አቅርቦት መተግበሪያ (Kegeberew Agricultural Products Sourcing, KAPS) አንዱ ነው፡፡

ይህ አምራች ገበሬው ባለበት ሆኖ ያመረተውን የግብርና ምርት ለሽያጭ ማቅረብ የሚችልበት መተግበሪያ ሲሆን፣ ሸማቹም የሚፈልገውን የግብርና ምርት ማግኘት የሚችልበትና ጊዜን መቆጠብ የሚያስችል የአቅርቦት መተግበሪያ አማራጭ ነው፡፡

የከገበሬው ኮንስዩመር ብድር ማኔጀመንት (Kegeberew Consumer Credit Management, KCCM) ለመንግሥታዊና የግል አገልግሎት ሰጪ ተቋማት የብድር አገልግሎት ማቅረብ የሚቻልበት ሲሆን፣ የከገበሬው የኦንላይን መማርያ አስተዳደር ሥርዓት (Kegeberew Learning Management System, KLMS) ደግሞ በተለያዩ የትምህርት መስኮችና ከ77 በላይ የሚሆኑ ልዩ ልዩ የክህሎት ማበልፀጊያ ሥልጠናዎችን በበይነ መረብ አማካይነት የሚሰጥበት ነው፡፡ ይህ በተለያየ መስክ ዕውቀትና ችሎታ ያላቸው ሰዎች ዕውቀታቸውን ለመጋራት የሚችሉበትም ነው፡፡

ከገበሬው ቴሌቪዥን መረጃ ማሠራጫ (Kegeberew Television Streaming) መተግበሪያ በተጨማሪ፣ የከገበሬው ኦርደርና ዲሊቨሪ መቆጣጠሪያ (Kegeberew Order and delivery Tracking, KOT) ከፕላትፎርሞቹ ይገኝበታል፡፡

ይህ በከገበሬው የበይነ መረብ ግብይት መድረክ አማካይነት የተላኩ ትዕዛዞች ወደ ምርት መጋዘን መድረሳቸውንና የተጠየቀው ምርትና አገልግሎት በትክክል መላኩንና ሸማቾች ያዘዙት ምርት በትክክል ከምርት መጋዘን ወጥቶ እጃቸው መግባቱን ክትትል የሚያደርግ ፕላትፎርም ነው፡፡

ከቻይና ወደ አፍሪካ (China to Africa) ሌላው ሲሆን፣ በቻይና የሚመረቱ የኢንዱስትሪ ውጤቶችን በከገበሬው የበይነ መረብ ግብይት መድረክ (E-commerce) አማካይነት ለመላው አፍሪካ ገበያ ማቅረብ የሚቻልበት መጠነ ሰፊ የበይነ መረብ ግብይት አማራጭ መሆኑን ወጣት አማኑኤል በማብራሪያው ጠቁሟል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...