Tuesday, February 27, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበጥበብ የታጀበ በጎ ሥራ

በጥበብ የታጀበ በጎ ሥራ

ቀን:

ከዘፈን ይልቅ ልቧን የሚያስደስተው ሰዎች ተረድተውና ታግዘው ማየት ነው፡፡ የወደቁ፣ ጨለማ ውስጥ ያሉና መሄጃ መንገድ የጠፋባቸውን መርዳት ያስደስተኛል ትላለች፡፡

በተለይ ወጣት ሴቶችን ሳይወድቁ መምራት፣ መንገድ ማሳየትና የተሻለ ቦታ እንዲደርሱ ሥልጠና መስጠት ከምትከውናቸው በጎ ሥራዎች አንዱ ነው፡፡

በጥበብ የታጀበ በጎ ሥራ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በፖፕ፣ በሂፕ ሆፕ፣ በጃዝና በሬጌ ሥልት ዘፈኖቿ ለምትታወቀው ቻቺ ታደሰ፣ ከዚህ ቀደም በኢትዮጵያ ታሪክ ተፅዕኖ የፈጠሩ የብርቱ ሴቶችን ስም በ90 ቅርንጫፎቹ የሰየመው እናት ባንክ፣ 172ኛ ቅርጫፉን በስሟ ሰይሞላታል፡፡

እናት ባንክ ጥር 25 ቀን 2016 ዓ.ም.፣ በለሚ ኩራ ክፍለ ከተማ ሐያት ዞን ሦስት አካባቢ የሚገኘውን 172ኛ ቅርንጫፉን በቻቺ ስም መሰየሙን አስመልክቶ አስተያየት የሰጠችው አርቲስት ቻቺ፣ ከሁሉም በላይ ለሰዎች በተለይም ለወጣት ተማሪዎች ድጋፍ በማድረግ ለውጤት ማብቃት እንደሚያስፈልግና ለዚህም እናት ባንክ እንዲተባበራት ጥሪ አቅርባለች፡፡

አርቲስት ቻቺ ‹‹ሦር ቱ ሰክሰሰ›› መንግሥታዊ ያልሆነ የሥልጠና ተቋም የመሠረተችውም ወጣቶችን ለማገዝ ስትል ነው፡፡ ማርገሬት ሆፈር ከተባሉ አሜሪካዊትና ከቅድስተ ማርያም ዩኒቨርሲቲ ጋር በሚተገበረው ሥልጠና፣ በስኮላር ሺፕ ውጭ ለመሄድ ፍላጎትና ጥሩ ውጤታቸው ያላቸው የሁለተኛ ደረጃ ተማሪዎች የሚሳተፉበት ነው፡፡

ለውጭ ትምህርት የሚያበቃ ዓለም አቀፍ የእንግሊዝኛ ቋንቋ ክህሎት ሥልጠና መስጠት፣ ነፃ የትምህርት ዕድል እንዲያገኙ ማገዝና የቅድመ ዝግጅት ሥልጠና መስጠትም የሶር ቱ ሰክሰስ ዓላማ ነው፡፡

በቅርቡ በተጀመረው ሥልጠናም በመጀመሪያው ዙር 15 በሁለተኛው 55 ተማሪዎች በሥልጠናው ተሳትፈዋል፡፡

በሥልጠናው አሁን ላይ እየተሳተፉ ከሚገኙ ተማሪዎች ደግሞ በአዲስ አበባ ከመንግሥት ሁለተኛ ደረጃ ትምህርት ቤቶች የተውጣጡ ከ15 በላይ ሴት ተማሪዎች ይገኙበታል፡፡

ከእቴጌ መነን የልጃገረዶች አዳሪ ትምህርት ቤት የተውጣጡ ተማሪዎችም የዕድሉ ተጠቃሚዎች ናቸው፡፡ ቻቺ ‹‹ተማሪዎቹን ትንሽ ድጋፍ ካገኙ ኢትዮጵያን በዓለም የሚያስጠሩ ይሆናሉ፡፡ እነሱ ዕውቀት አላቸው፡፡ ከእኛ የሚያስፈልገው መንገዱን ማሳየት ብቻ ነው፤›› ስትል ትገልጻለች፡፡

‹‹ኧረ ሸጋው ስምህ ማነው››፣ ‹‹አፍሪካዊ ነኝ››፣ ‹‹ካከበርከኝ›› በሚል ሙዚቃዎቿ በተለይ ከ1980ዎቹ ወዲህ በኢትዮጵያ ዕውቅና ያገኘችው ቻቺ፣ ‹‹ሆያ ሆዬ›› የተሰኘ አልበም በማዘጋጀትም ከሬጌ አቀንቃኞቹ ቡጂ ባንቶንና ሲዝለር ጋር በመተባበር በተለያዩ አገሮች ሥራዎቿን በመድረክ አቅርባለች፡፡

በተለያዩ የዓለም አገሮች እየተዘዋወረች ሥራዎቿን የማቅረቧ ምክንያት ደግሞ፣ ኢትዮጵን ማስተዋወቅና በበጎ ማስጠራት መሆኑን ትናገራለች፡፡ ለዚህ ታዲያ በሙዚቃው ብቻ አልተወሰነችም፡፡ ኢትዮጵያን ያስተዋውቁልኛ ብላ ላሰበቻቸው ሥራዎች ‹‹የእኔ ኢትዮጵያ››ን በማቋቋም ኢትዮጵያን ለማስተዋወቅ ሠርታለች፡፡

አርቲስት ቻቺ እንደምትለው፣ የእኔ ኢትዮጵያ የተመሠረተው የዳያስፖራ ልጆች ኢትዮጵያን አላወቋትም፣ ማሳወቅ አለብኝ ከሚል ዕሳቤም ጭምር ነው፡፡ የእኔ ኢትዮጵያ ዋና ሐሳቡ ኢትዮጵያን ማስተዋወቅ ሲሆን፣ በዚህም ቡድን በማደራት ደጀን ተራራ ድረስ በመሄድ በቀጥታ ሥርጭት እንዲሁም በሜጋዚን የኢትዮጵያን መልክዓ ምድር ለማስተዋወቅ ሞክራለች፡፡

ወንጪና አርባ ምንጭንም እንዲሁ ለማስተዋወቅ የሠራችው አርቲስቷ፣ አሁን ላይ የፀጥታ ችግር በመኖሩ ለጊዜው እየተሠራ ባይሆንም፣ ሁኔታዎች ሲስተካከሉ የማስተዋወቅ ሥራው የሚቀጥል መሆኑን ጠቁማለች፡፡

ባገኘችው መድረክ ሁሉ ሳግ እየተናነቃት የኢትዮጵያን ስም በማንሳትና በማስተዋወቅ የምትታወቀው አርቲስት ቻቺ፣ የአፍሪካም ድል ነው የምትለውን የዓድዋን ድል ለአፍሪካውያን ይበልጥ ለማስተዋወቅ፣ የዓድዋ ፕሮጀክትን ከሦስት ዓመታት በፊት ዕውን አድርጋለች፡፡

ካቻምና በኢትዮጵያ ወጣቶች የዓድዋ ድልን አስመልክቶ ውይይት እንዲያደርጉና ግንዛቤ እንዲያገኙ በፕሮጀክቱ ሲሠራ፣ በወቅቱ ጥሩ የሠሩ ሰዎችም ተሸልመዋል፡፡

ዓምና በአዲስ አበባ ከተካሄደው መድረክ በተጨማሪ፣ በደቡብ አፍሪካ ኬፕታውን የተለያዩ መድረኮችና የጎዳና ትርዒቶች በማዘጋጀት የዓድዋ በዓል እንዲከበር አድርጋለች፡፡  

ዘንድሮ በኬንያና በአዲስ አበባ እንዲከበር ዝግጅት መደረጉን የገለጸችው ቻቺ፣ ፕሮግራሙ የሚካሄደው የኬንያና የኢትዮጵያ ፍሬንድሺፕ ከሚባል አካል ጋር በትብብር መሆኑን ጠቁማለች፡፡ ጥሩ አበርክቶ ላላቸው አራት ግለሰቦችም ሁለት ከኬንያ፣ ሁለት ከኢትዮጵያ የሚሸለሙ ይሆናል፡፡

ቻቺ ከበጎ ፈቃድ ሥራዎቿ የዱር እንስሳትንና ቱሪዝሙን ማስተዋወቅም ይገኝበታል፡፡ እሷ እንደምትለው፣ ዋና ሥራዋ አምባሳደር ሆኖ ኢትዮጵያ ያላትን የቱሪዝምና የዱር እንስሳት ሀብት ማስተዋወቅና ዘርፉን ማራኪ ለማድረግ መሥራት ነው፡፡

‹‹ኤሮቢክስ ሕይወቴ ነው›› የምትለው ቻቺ፣  እናቶች ቤት ሲውሉ አሊያም ከሥራ ሲመለሱ ጤንነታቸው መጠበቅ አለበት በማለት በተለይ ሴቶች ኤሮቢክስን እንዲሠሩ የግንዛቤ ማስጨበጥ ሥራን ሠርታለች፡፡

ባቋቋመችው የጂምና ኤሮቢክስ ሥልጠና ማዕከል በርካታ ሴቶች ኤሮቢክስ እንዲሠሩ ማስቻሏንና የአካል ብቃት እንቅስቃሴ እንዲዳብር መሥራቷን ትገልጻለች፡፡

ቻቺ በጥበብና በበጎ ሥራዎቿ  ላደረገችው ጉልህ አበርክቶዎች ሴቭ ዘ ችልድረንና ዩኒሴፍ የበጎ ፈቃድ አምባሳደርነት ዕውቅና ሰጥተዋታል፡፡

የኢትዮጵያ ቱሪዝምና እንስሳት ጥበቃ አምባሳደር የሆነችው ቻቺ፣ ለሰላምና ዕርቅ እንዲሁም ኤችአይቪን በመከላከል ላበረከተችው አስተዋጽኦ በጠቅላይ ሚኒስቴር ቢሮ የሰላም አምባሳደርነት ማዕረግ ተሰጥቷታል፡፡

በአዲስ አበባ ዙሪያ ለሚገኙ የትምህርት ቤት ሕፃናት የምገባ ሥራዎችን በመሥራቷም ከአፍሪካ ኅብረት የዕውቅና ሰርተፊኬት አግኝታለች፡፡  

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የመጣንበትና አብረን የምንዘልቅበት የጋራ እሴታችን ለመሆኑ ነጋሪ ያስፈልጋል ወይ?

በኑረዲን አብራር በአገራችን ለለውጥ የተደረጉ ትግሎች ከመብዛታቸው የተነሳ ሰላም የነበረበት...

አልባሌ ልሂቃንና ፖለቲከኞች

በበቀለ ሹሜ በ2016 ዓ.ም. ኅዳር ማክተሚያ ላይ ፊልድ ማርሻል ብርሃኑ...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች የኢትዮጵያ የባህር...