Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

የዓድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ

ትኩስ ፅሁፎች

‹‹በዚህ የመታሰቢያ ሐውልት በ1888 ዓ.ም. የዓድዋ ጀግኖች የሀገራቸውን ሉዓላዊነት ለማስጠበቅ እና ሕዝቦቻቸውን ከቅኝ ግዛት ለመከላከል፣ በጀግንነት ተዋግተው የሕይወት መስዋዕትነትን ከፍለው በመላው የጥቁር ሕዝብ ልብ ውስጥ ጀግንነትን ከትበዋል፡፡ በዚህ ሐውልት ውስጥ ጀግንነትን ከትበዋል፡፡ በዚህ ሐውልት ውስጥም ዘመን ተሻጋሪው ድላቸው እና የአርበኝነት መንፈሳቸው ለትውልድ ምስክርነት ተቀምጧል፡፡››

ይህ ጽሑፍ የሠፈረው በአዲስ አበባ ከተማ አራዳ/ ፒያሳ ላይ በተሠራው ግዙፉ የዓድዋ ድል መታሰቢያ ዘርፈ ብዙ ሕንፃ ላይ ነው፡፡ ይህን ታሪካዊ ሕንፃና ሐውልት ርዕሰ ብሔሯ  ፕሬዚዳንት ሳህለ ወርቅ ዘውዴ በተገኙበት የካቲት 3 ቀን 2016 ዓ.ም. የመረቁት ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) ናቸው፡፡ የዓድዋ ድል ኢትዮጵያ በንጉሠ ነገሥቷ ዳግማዊ ምኒልክ ጠቅላይ አዝማችነት ከ128 ዓመታት በፊት በወራሪው የጣሊያን ሠራዊት ላይ የካቲት 23 ቀን 1888 ዓ.ም. ያስመዘገበችው እንደነበር ይታወሳል፡፡ ፎቶዎቹ የታሪካዊውን ሕንፃና ሐውልቶች ከፊል ገጽታ ያሳያሉ፡፡

– ፎቶ የአዲስ አበባ ከንቲባ ጽሕፈት ቤት

የዓድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተርየዓድዋ ድል መታሰቢያ በአዲስ አበባ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች