Saturday, April 20, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ የካቤኔ አባል የሆኑት አንድ ከፍተኛ ባለሥልጣን የሚያቀርቡትን ቅሬታ እያዳመጡ ነው] 

 • ክቡር ሚኒስትር እየሆነ ያለው ነገር በእጅጉ ስላሳሰበኝ ነው በአካል አግኝቼ ላነጋግርዎት የፈለግኩት።
 • ጥሩ አደረክ። ምን አሳሳቢ ነገር ገጥሞህ ነው?
 • ክቡር ሚኒስትር ተወያይተንና ተግባብተን ያስቀመጥናቸው አቅጣጫዎች፣ በተለይም ወሳኝ ያልናቸው ጉዳዮች በተቃራኒው ነው የሚፈጸሙት።
 • እህ…
 • በውስጣችን ሌላ መንግሥት አለ ወይ? የሚል ጥያቄ እንዲፈጠርብኝ ጭምር እያደረገ ነው።
 • ምንድነው የተፈጠረው?
 • ክቡር ሚኒስትር እርስዎ እንዲሁም ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናት ባሉበት ኢትዮጵያ ታምርት የሚል ንቅናቄ ይፋ ማድረጋችንን ያስታውሳሉ አይደለም?
 • በትክክል።
 • በዚህ ንቅናቄ ጥሩ የሚባል ውጤት ማየት በጀመርንበት ወቅት ይህንን የሚያዛባ ተቃራኒ ተግባራት ውስጣችን ባሉ ባለሥልጣናት እየተፈጸመ ነው።
 • ለምን የተፈጠረውን ነገር መጀመሪያ አትነግረኝም?
 • ወደዚያ እየመጣሁ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • እሺ …ምን ተፈጠረ?
 • ኢትዮጵያ ታምርት በሚል ንቅናቄ ከውጭ የምናስገባቸውን ዋና ዋና ምርቶች በአገር ውስጥ ለማምረት ጥረት መጀመራችን ይታወቃል።
 • አዎ።
 • ነገር ግን ገና መሠረቱን ሳይዝ የጀመርነው ንቅናቄ በራሳችን በመንግሥት ባለሥልጣናት ደባ ፈተና ውስጥ ገብቷል።
 • እንዴት?
 • አፍዴራን የሚያክል የጨው ክምችት ይዘን የቆዳ ፋብሪካዎቻችን እየተዘጉ ነው።
 • ለምን?
 • ምክንያቱም የኢንዱስትሪ ጨው ሊቀርብ አልቻለም።
 • እንዴት? በምን ምክንያት?
 • ምክንያቱም ክልሉ ካደረጃቸው አምራቾች ውጪ ሌላ ሰው ወደ ክልሉ ገብቶ ጨው ማምረት አይችልም የሚል ክልከላ በመጣሉ ነው።
 • ክልሉ ነው ይህንን ክልከላ የጣለው?
 • አይደለም ክቡር ሚኒስትር።
 • እና ማን ነው?
 • የንግድ ጉዳይ የሚመለከተው የፌዴራል መንግሥት ሚኒስቴር መሥሪያ ቤት ነው።
 • እሺ ማንም ያምርተው፣ የተመረተውን ጨው ግን ለኢንዱስትሪዎቹ ሊቀርብላቸው ያልቻለውም በምን ምክንያት ነው?
 • ስላልተመረተ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ለምን?
 • አንደኛ በክልሉ የተደራጁት አምራቾች አቅም የላቸውም።
 • እሺ ሌላውስ?
 • የግንዛቤ ችግር ነው።
 • እንዴት?
 • የቆዳ ኢንዱስትሪዎች ጨው ምን ያደርግላቸዋል ነው የሚሉት።
 • እህ… እነሱ ጨው ለምግብ ብቻ እንደሆነ ነው የሚያውቁት?
 • ለምግብ የሚሆነውንም ጨው እያመረቱ እኮ አይደለም ክቡር ሚኒስትር?
 • እና ከዬት ነው የሚመጣው?
 • ከውጭ ተገዝቶ ነው።
 • ኢትዮጵያ ታምርት እያልን ጨው ከውጭ ነው የሚገባው?
 • ንቅናቄው በጨው ብቻ አይደለም የተሰናከለው።
 • እ… ሌላ ምን ችግር አለ?
 • የአገር ውስጥ ባለሀብቶችን ወደ አምራች ዘርፍ በማስገባት የውጭ ምርቶችን እንዲተኩ ንቅናቄ ጀምረን ነበር።
 • እሺ…?
 • በዚህ ረገድ ጥሩ ስኬት ያስመዘገብን ቢሆንም ባልታወቀ ምክንያት ተመሳሳይ ምርቶችን ከውጭ በገፍ ለሚያስገቡ ባለሀብቶቸ ከፍተኛ የሆነ መንግሥታዊ ማበረታቻ መሰጠት ጀምሯል።
 • የምን ማበረታቻ ነው የሚሰጣቸው?
 • በማንና እንዴት እንደተወሰነ ሳይታወቅ ተመሳሳይ ምርቶችን በገፍ ለሚያስገቡ ባለሀብቶች የውጭ ምንዛሪ ቅድሚያ እንዲያገኙ ይደረጋል።
 • እሺ…?
 • የውጭ ምንዛሪ እጥረት ቢኖርም እነዚህ ባለሀብቶች በውጭ ባንኮች ያስቀመጡትን ዶላር ተጠቅመው ተመሳሳይ ምርቶችን እንዲያስገቡ ይደረጋል።
 • እንዴት?
 • በፍራንኮ ቫሉታ።
 • ፍራንኮ ቫሉታ የፈቀድነው የተወሰኑ ምርቶችን ብቻ ለማስገባት አይደለም እንዴ?
 • ነው።
 • እና እንዴት ይሆናል?
 • ይኼ ብቻ አይደለም እየሆነ ያለው ክቡር ሚኒስትር?
 • እ… ልላ ምን እየሆነ ነው?
 • በፍራንኮ ቫሉታ የሚያስመጡት ባለሀብቶች ትክክለኛ ቀረጥና ታክስ ጭምር እየከፈሉ አይደለም።
 • እንዴት? በማን ውሳኔ?
 • በውሳኔ አይደለም ክቡር ሚኒስትር?
 • ታዲያ በምንድነው?
 • ባለሀብቶቹ የሚያስገቡትን ምርት በአነስተኛ ዋጋ እንደገዙት የሚገልጽ ሐሰተኛ ሰነድ እያቀረቡ ስለሚስተናገዱ ነው።
 • ምን?
 • ክቡር ሚኒስትር ምርቱን በነፃ ያገኙት እስኪመስል ድረስ በሳንቲም ደረጃ እንደገዙት የሚገልጽ የግዥ ሰነድ አቅርበው ነው የሚስተናገዱት።
 • ሊሆን አይችልም?
 • እየሆነ ነው ክቡር ሚኒስትር። የሚገርመው የምርቱ ዋጋ እየታወቀ ያስቀመጥናቸው ኃላፊዎች የሚቀርብላቸውን ሰነድ ሀሰተኛነት አለመጠራጠራቸውና ውድቅ አለማድረጋቸው ነው።
 • ሰነዱ ሀሰተኛ መሆኑን እንዴት መጠራጠር ተሳናቸው?
 • ተስኗቸው አይደለም።
 • እ…?
 • ተናበውና ተጋሪ ሆነው ስለሚሠሩ ነው።
 • የምን ተጋሪ?
 • የጥቅም ነዋ ክቡር ሚኒስትር።
 • አንተ እንዴት ነው ይህንን ልትደርስበት የቻልከው?
 • ጎትጉተን ያስገባናቸው ባለሀብቶች በማስረጃ አስደግፈው ቅሬታቸውን ለተቋማችን ካቀረቁቡ በኋላ ነው ነገሩን የተረዳሁት።
 • ጥሩ ነው።
 • ምኑ ክቡር ሚኒስትር?
 • ችግሩ እንዲፈታ ያደረግከው ጥረት የሚበረታታ ነው።
 • ክቡር ሚኒስትር ችግሩ እንዲፈታ አቤቱታ እያቀረብኩ እንጂ ችግሩ መቼ ተፈታ?
 • ከማንም ትዕዛዝ ሳትጠብቅ ችግሩን ለመፍታት የሄድከው ርቀት በራሱ የመፍትሔው አካል ነው።
 • አመሠግናለሁ ክቡር ሚኒስትር።
 • እኔም በድጋሚ አመሠግናለሁ። የጀመርከውን ንቅናቄ አጠናክረህ ቀጥልበት።
 • የቱን ንቅናቄ ክቡር ሚኒስትር?
 • ኢትዮጵያ ታምርት የሚለውን።
 • ክቡር ሚኒስትር የእኔ ንቅንቄ ብቻውን ውጤት አያመጣም።
 • አይዞህ ተስፋማ መቁረጥ የለብህም።
 • ተስፋ ቆርጬ አይደለም ክቡር ሚኒስትር።
 • እ…?
 • ውጤት እንዲመጣ ከተፈለገ አንድ ደረጃ ከፍ ማድረግ ያስፈልጋል።
 • ምኑን
 • ንቅናቄውን።
 • ወደ ምን?
 • ወደ ግንባር።
 • እ…?
 • አዎ። ስያሜውም መቀየር አለበት።
 • ምን ተብሎ።
 • ኢትዮጵያ ታምርት ግንባር።

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...