Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናየኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

የኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ ለመሸጥ የሚያስችል ስምምነት ለመፈጸም የመንግሥት ውሳኔ እየተጠበቀ ነው

ቀን:

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለታንዛኒያ የኤሌክትሪክ ኃይል ሽያጭ ለማከናወን የሚያስችለውን ስምምነት ድርድር ካገባደደ በኋላ፣ መንግሥት ይፋዊ የመፈራረሚያ ውሳኔውን እንዲያሳውቀው እየተጠባበቀ መሆኑን አስታወቀ። 

የኢትዮጵያ የኤሌክትሪክ ኃይል ዋና ሥራ አስፈጻሚ አቶ አሸብር ባልቻ ለታንዛኒያ ለማቅረብ ተቋማቸው የተነጋገረውን የኃይል መጠን በተመለከተ ለሪፖርተር፣ ‹‹ከታንዛኒያ ኩባንያ ጋር የተነጋገርነው አሁን ለጊዜው 100 ሜጋ ዋት ለማቅረብ ነው፣ ይህ ግን ሊጨምር ይችላል፤›› ብለዋል።

‹‹በተለይ የሚሸጠው የኤሌክትሪክ ኃይል በኬንያ አልፎ ስለሚሄድ፣ እዚያ ያለውን ኔትወርክ ለማስተካከል ተጨማሪ ኢንቨስትመንት ይፈልጋል፣ እሱ ከተሟላ የበለጠ እናቀርባለን፤›› ሲሉ ተናግረዋል። 

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

እንደ ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገለጻ በአሁኑ ወቅት ኢትዮጵያ ለኬንያ የኤሌክትሪክ ኃይል የምታስተላልፍበት መስመር 2,000 ሜጋ ዋት የመሸከምና የማስተላለፍ አቅም ያለው ሲሆን፣ እስከ ታንዛኒያ ድረስ ቢያንስ 1,500 ሜጋ ዋት ያህል የማስተላለፍ አቅም አለው፡፡

ከታንዛኒያ ጋር የሚደረገውን ስምምነት በተመለከተ አቶ አሸብር፣ ‹‹አሁን ድርድሩ በጣም ትንሽ ነው የቀረው፣ ጨርሰናል ማለት ይቻላል፣ መንግሥት በሚያሳውቀው ቀን ውል ለመፈጸም ነው እያሰብን ያለነው፤›› ብለዋል።

የኃይል ሽያጩን ለማከናወን በኢትዮጵያ በኩል በአሁን ወቅት ተዘርግቶ አገልግሎት እየተሰጠበት ያለውን መሠረተ ልማት እንደምትጠቀም ጠቁመው፣ ከኬንያ ወደ ታንዛኒያ ለማድረስ የሚያስችለው የኃይል ተሸካሚና አስተላላፊ መሠረተ ልማት ግንባታም መጠናቀቁን ገልጸዋል። 

በኬንያ በኩል ለታንዛኒያ ለሚላከው የኤሌክትሪክ ኃይል ሁለቱ አገሮች ውል መፈጸማቸውን፣ በኢትዮጵያ በኩል ግን ለኬንያ የሚከፈል ገንዘብም ሆነ የተጨማሪ የኃይል አቅርቦት ውል እንደሌለ አስረድተዋል።

ታንዛኒያና ኬንያ የፈጸሙትን የስምምነት ይዘት አስመልክተውም፣ ‹‹ወደ ታንዛኒያ ለሚላከው ኃይል ኬንያ ለምትሰጠው ኃይል የማስተላለፍ አፈልግሎት በሰዓት አንድ የአሜሪካ ሳንቲም ታገኛለች፤›› ብለዋል። 

ኢትዮጵያ እ.ኤ.አ በ2022 ከኬንያ ጋር በፈጸመችው የኃይል ሽያጭ ስምምነት መሠረት በአሁኑ ወቅት 200 ሜጋ ዋት የምትልክ ሲሆን፣ ስምምነቱ ሦስተኛ ዓመት ሲሞላው የተገለጸው መጠን ወደ 400 ሜጋ ዋት ከፍ እንዲደረግ ተስማምተው እንደበር ይታወሳል፡፡

ከታንዛኒያ ጋር የተደረገውን ስምምነት አቶ አሸብር፣ ‹‹መንግሥት በይፋ በዚህ ቀን ፈርሙ ሲለን ስምምነቱን በፊርማ አፅድቀን እንፈጽማለን፤›› ብለው፣ ‹‹በምን ያህል ገንዘብ ሽያጩ እንደሚከናወንና ከመቼ ጀምሮ የሚለውን መግለጽ የመንግሥት ኃላፊነት ነው፤›› ብለዋል። 

የኢትዮጵያ ኤሌክትሪክ ኃይል ለአፍሪካ አገሮች በሽያጭ የሚያቀርበውን የኤሌክትሪክ ኃይል ለማሳደግና ተደራሽነቱንም ለማስፋት በያዘው ዕቅድ መሠረት፣ በመጪዎቹ አምስት ዓመታት አቅርቦቱን ደቡብ አፍሪካ ለማድረስ ማለሙን ዋና ሥራ አስፈጻሚው ገልጸዋል። 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ (ክፍል አንድ)

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...