Sunday, April 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናአሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር...

አሜሪካ የኢትዮጵያ የባህር በር ጥያቄ ተገቢነት ቢኖረውም ከጎረቤት አገሮች ጋር በሚደረግ ንግግር መሆን አለበት አለች

ቀን:

  • መንግሥትን ከፋኖና ከኦነግ ሸኔ ጋር ለማነጋገር ፍላጎቷን ገልጻለች

የኢትዮጵያ የባህር በር የማግኘት ፍላጎት ቅቡልነት ያለው ጥያቄ ቢሆንም ከሶማሊያ ፌዴራል መንግሥትና ከአጎራባች አገሮች ጋር በመነጋገር፣ ወይም በትብብር ቀጣናዊ የኢኮኖሚና የፀጥታ ውህደት ላይ በተመሠረተ አካሄድ ሊሆን እንደሚገባ አንድ የአሜሪካ ከፍተኛ ባለሥልጣን አስታወቁ፡፡

በቅርቡ በአዲስ አበባ ከተካሄደው የአፍሪካ ኅብረት የመሪዎች ጉባዔ ተሳትፎ ጎን ለጎን ከጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ (ዶ/ር) እና ከሶማሊያ ፕሬዚዳንት ሀሰን ሼክ መሐመድ ጋር ቆይታ የነበራቸው የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ ሞሊ ፊ፣ ለሁለቱ መሪዎች የሶማሊያን ሉዓላዊነትና የግዛት አንድነትን በማክበር ላይ በመመሥረት ችግሩ እንዲፈታና ውጥረቱ እንዳይባባስ ማሳሰባቸውን ተናግረዋል፡፡

የሶማሌላንድ ጉዳይ መፈታት ያለበት በሶማሊያና በሶማሌላንድ ሕዝብ እንጂ በውጭ ተዋናዮች አይደለም ያሉት ሞሊ ፊ፣ ቀጣናው ውስጥ ካለው በተጨማሪ ግጭትን ማስተናገድ አይቻልም ብለዋል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በኦሮሚያ ክልል ከሚንቀሳቀሰውና በፓርላማው አሸባሪ ተብሎ ከተሰየመው የኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ሸኔ)ም ጋርም ሆነ በአማራ ክልል ከሚንቀሳቀሰው የፋኖ ኃይል ጋር ያሉትን ግጭቶች ለመፍታትና ለማደራደር አሜሪካ ዝግጁ መሆኗን የገለጹት ደግሞ፣ የአሜሪካ መንግሥት የአፍሪካ ቀንድ ልዩ መልዕክተኛ ማይክ ሐመር ናቸው፡፡ ወታደራዊ አማራጭ ሰላማዊ መፍትሔ አያመጣም ያሉት ልዩ መልዕክተኛው፣ ‹‹የኢትዮጵያ መንግሥት ለመነጋገር ያለውን ዝግጁነት እናደንቃለን፤›› ብለዋል፡፡

በተጨማሪም በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እየታየ ነው ያሉትን የሰብዓዊ መብት ጥሰት በመጥቀስ፣ መንግሥት ለዜጎች ከለላ እንዲያደርግና ወንጀለኞችን ተጠያቂ እንዲያደርግ አሳስበዋል፡፡

የአሜሪካ የአፍሪካ ጉዳዮች ረዳት ኃላፊ በበኩላቸው፣ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ (ዶ/ር) በአማራና በኦሮሚያ ክልሎች እያጋጠሙ ያሉትን ችግሮች በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት ቁርጠኛ መሆናቸውን እንደገለጹላቸው ተናግረዋል፡፡

ከዚህ በፊት መንግሥት በታንዛኒያ ዳሬሰላም ከኦሮሞ ነፃነት ሠራዊት (ሸኔ) ጋር ባደረገው ንግግር መሳተፋቸውን የገለጹት ሐመር፣ ግጭቱን በሰላማዊ መንገድ ለመፍታት የሚያግዝ ሰላማዊ መፍትሔ ለማመቻቸት አሜሪካ ዝግጁ መሆኗን አዲስ አበባ በሚገኘው የአሜሪካ አምባሳደር ኧርቪን ማሲንጋ በኩል ጥያቄው ስለመቅረቡ አስረድተዋል፡፡

ሞሊ ፊ ለጋዜጠኞች በሰጡት የበይነ መረብ መግለጫ፣ በኢትዮጵያ ሰብዓዊ መብቶች እንዲከበሩና ሰላም ለማስፈን ከከፍተኛ የመንግሥት ባለሥልጣናት ጋር መምከራቸውን አስታውቀዋል፡፡

በሶማሊያ የአልሸባብን የሽብር ጥቃት ለመዋጋት የአሜሪካ መንግሥት ቁርጠኛ መሆኑንና የሶማሊያን መከላከያ ኃይል እንደሚደግፍ ገልጸው፣ የሶማሊያ የፀጥታ ኃይሎች ሙሉ በሙሉ የአገሪቱን የፀጥታ ሁኔታ ማስከበር እስኪችሉ ድረስ በተገቢው ሁኔታ የተጠና የአገሮች ወታደራዊ ኃይል በሶማሊያ ይቆያል ብለዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ (ክፍል አንድ)

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...