Sunday, April 21, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ሲገቡ ባለቤታቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ዜና በመደነቅ እየተመለከቱ አገኟቸው]

 • እንዲያው የሚደንቅ ነው እኮ።
 • ምኑ?
 • ዜና ተብሎ በቴሌቪዥን የሚተላለፈው ነገር ነዋ፡፡
 • ምኑ ነው የሚደንቀው?
 • የልደታ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎች ሕዝባዊ ውይይት ላይ ምን ጉዳዮች ተነሱ?
 • በአስማት ነው የምንኖረው ሲሉ ቅሬታቸውን አቅርበዋል።
 • እንዴት? ምን ማለታቸው ነው?
 • ደመወዛችን ሦስት ሺሕ ብር የመኖሪያ ቤት ኪራይ ዋጋ አሥር ሺሕ ብር ነው። እየኖርን ያለነው በአስማት ነው የሚሉት።
 • በክፍለ ከተማው የተካሄደውን ውይይት የመሩት አመራሮች በቂ ምላሽ ሰጡበት?
 • በቂ ምላሽ እንኳን አልተሰጠም።
 • ለምን?
 • ውይይቱን የመሩት አመራር ስለችግሩና መፍትሔው በቂ ግንዛቤ የላቸውማ።
 • እንዴት አይኖራቸውም?
 • በቃ የላቸውማ።
 • ውይይቱን የመሩት አመራሩ ማን ናቸው?
 • የጋምቤላ ክልል ርዕሰ መስተዳድር።
 • እንዴት?
 • እኔ ምን አውቄ፣ የልደታው ብቻ መሰለህ እንዴ?
 • እ…?
 • ለምሳሌ በጉለሌ ክፍለ ከተማ በተካሄደው ውይይት ላይ ነዋሪዎቹ በመጠጥ ውኃ ችግር እየተሰቃዩ መሆናቸውን ገልጸው መፍትሔ ጠይቀው ነበር።
 • እሺ? ምን ምላሽ ተሰጣቸው?
 • ምላሽ አላገኙም።
 • ለምን?
 • ውይይቱን የመሩት አመራር ችግሩን ለመፍታት ምን እንደታቀደና ምን እየተደረገ እንደሆነ የሚያውቁት ነገር ስለሌ ነዋ።
 • ውይይቱን የመሩት አመራር ማናቸው?
 • የሲዳማ ክልል ርዕሰ መስተዳድር።
 • እሳቸው ብቻ?
 • አይደሉም።
 • ሌላው አመራር ማነው?
 • የትራንስፖርት ሚኒስትሩ።
 • እንዴት?
 • ምን እኔን ትጠይቀኛለህ? አንተው መልስልኝ እንጂ፡፡
 • በቃ ተይው።
 • ለምን?
 • ገብቶኛል።
 • ምኑ?
 • ለምን እንደዚያ እንደተደረገ።
 • ለምንድነው?
 • ለበጎ ነው።

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሾፌራቸው ጋር ሰሞኑን ሲሰጥ ስለነበረው ሥልጠና እያወሩ ወደ ቤታቸው እየተመለሱ ነው]

 • ሁሉም ከፍተኛ አመራር በሥልጠናው ይሳተፋል ማለት ነው ክቡር ሚኒስትር?
 • ከፍተኛ አመራሩ ብቻ ሳይሆን እስከ ታች ያለው በየደረጃው እየተሳተፈ ነው።
 • ሥልጠናው ምን ላይ ያተኮረ ነው?
 • ሰሞኑን ቴሌቪዥን አላየህም ማለት ነው?
 • ኧረ በየዕለቱ ነው ቴሌቪዥን የምከታተለው።
 • ታዲያ ከዕዳ ወደ ምንዳ የሚል ሥልጠና እየተሰጠ እንደሆነ አልማህም?
 • እሱ ነው እንዴ?
 • አዎ።
 • እሱንማ መስማት ብቻ ሳይሆን ሁላችንም ውጤቱን በጉጉት እየጠበቅን ነው።
 • በጉጉት?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር ሁሉም ሠራተኛ የሚያወራው ስለዚህ ሥልጠና እኮ ነው።
 • ለምን?
 • ያው ሁላችንም በኑሮ ውድነቱ እየተሰቃየን ነዋ ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ ከዚህ ሥልጠና ጋር ምን አገናኘው?
 • ሥልጠናው ሲያልቅ ይወሰናል ብለን ነዋ?
 • ምንድነው የሚወሰነው?
 • ምንዳው።
 • እሱ እንኳን አይኖርም።
 • ለምን ክቡር ሚኒስትር?
 • ሌላ ሥልጠና እንዲጀመር ተወስኗል።
 • እንደገና ሌላ ሥልጠና?
 • አዎ።
 • በምን ጉዳይ ላይ ያተኮረ ነው።
 • ሥልጠናው?
 • እ…?
 • ሀብት የመፍጠር ጥረትና ያጋጠሙ ተግዳሮቶች በሚል መሪ ቃል የሚካሄድ ሥልጠና ነው።
 • ቀረ ማለት ነው?
 • ምኑ?
 • ሽግግሩ?
 • የምን ሽግግር? ከምን ወደ ምን?
 • ከዕዳ ወደ ምንዳ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰው መሆን ምንድን ነው? ቅርስና ማኅበራዊ ፍትሕ (ክፍል አንድ)

በሱራፌል ወንድሙ (ዶ/ር) ዳራ ከጎራዎች፣ ከመፈራረጅ፣ ነገሮችን ከማቅለልና ከጊዜያዊ ማለባበስ ወጥተን...

ኢኮኖሚው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሳት ያሠጋል

በጌታቸው አስፋው ኢትዮጵያን እንዳያፈርሱ የሚያሠጉኝ አንድ ሁለት ብዬ ልቆጥራቸው የምችላቸው...

የኢትዮጵያ የፖለቲካ ትግል በሕግ አምላክ ይላል

በገነት ዓለሙ የአገራችንን ሰላም፣ የመላውን ዓለም ሰላም ጭምር የሚፈታተነውና አደጋ...

በሽግግር ፍትሕ እንዲታዩ የታሰቡ የወንጀል ጉዳዮች በልዩ ፍርድ ቤት ሳይሆን በልዩ ችሎት እንዲታዩ ተወሰነ

የኤርትራ ወታደሮች በሌሉበትም ቢሆን ይዳኛሉ ተብሏል በፅዮን ታደሰ የሽግግር ፍትሕ የባለሙያዎች...

የአገሪቱ ባንኮች የመጭበርበር ተጋላጭነት እየጨመረ መሆኑን ብሔራዊ ባንክ አስታወቀ

በአንድ ዓመት ውስጥ ብቻ2 ቢሊዮን ብር መጭበርበሩን ገልጿል ቀሲስ በላይ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...