Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ስፖርትከድሬዳዋ ስታዲየም ሳር ተከላ በዘለለ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

ከድሬዳዋ ስታዲየም ሳር ተከላ በዘለለ ትኩረት የሚሹ ጉዳዮች

ቀን:

ዓለም አቀፉ የእግር ኳስ ማኅበር ፊፋ በቅርቡ በድሬዳዋ ስታዲየም የተነጠፈውን ሰው ሠራሸ ሳር ዕውቅና መስጠቱን አስታውቋል፡፡

በታን ኢንጂነሪንግ የተነጠፈው ሰው ሠራሽ ሳር ስድስት ወራት ከፈጀ በኋላ፣ በፊፋ  ተቋም ግምገማ ተደርጎለት  ምላሹ ይጠባበቅ ነበር፡፡

መቀመጫውን በእንግሊዝ ያደረገው ‹‹ስፖርት ላብ ዩኬ›› የተሰኘ የስፖርት ቴክኖሎጂ ጥናትና ምርምር ተቋም ድሬዳዋ ስታዲየምን መገምገሙ ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

በግምገማው ወቅት ሜዳው የተቀመጠበት ልኬት፣ የመሬቱ ጥብቅነት፣ ከተፈጥሮ ሳር ጋር ያለው መቀራረብ፣ ኳስን የማንጠርና የማሽከርከር አቅም፣ የሳሩ ቁመት፣ የራበሩ ምጣኔ፣ እንዲሁም የመጫወቻ ጫማ መሬት ሲረግጥ የሚፈጠረው ሰበቃው እንዴት ነው የሚለውን ገምጋሚ ቡድኑ መመልከቱን ገልጿል።

ባለሙያዎቹ ሜዳውን በገመገሙበት ወቅት ለጋዜጠኞች በሰጡት አስተያየት፣ ሳር ነጠፋው ደረጃውን የጠበቀ እንደሆንና ማንኛውንም ዓለም አቀፍ ጨዋታ ማስተናገድ እንዲችል ተደርጎ መተከሉን አብራርተዋል፡፡

በዚህም መሠረት የድሬዳዋ ስታዲየም ሜዳ በዓለም አቀፍ ደረጃ ከሚገኙ ከተወሰኑ የሻምፒዮንስ ሊግ ሜዳዎች ጋር ተመጣጣኝ እንደሆነ፣ ለጨዋታም ምቹ መሆኑን ባለሙያው መግለጻቸው ይታወሳል፡፡

በዚህም መሠረት የግምገማውን ውጤት ወደ ፊፋ ከተላከ በኋላ፣ የካቲት 21 ቀን 2016 ዓ.ም. የዕውቅና ሰርተፊኬት ማግኘቱ ተገልጿል፡፡

ፊፋ በላከው የማረጋገጫ ደብዳቤ መሠረት  የሜዳው የምርመራ ውጤት ከተገመገመ በኋላ፣ የፊፋን የሰው ሠራሽ ሜዳ ደረጃን እንዳሟላ ማረጋገጡን አስታውቋል፡፡

በዚህም መሠረት የድሬዳዋ ስታዲየም እ.ኤ.አ. ከ25/02/2024 እስከ 24/02/27 ድረስ ዓለም አቀፍ ውድድሮችን ማስተናገድ ይችላል ሲል በይፋ አረጋግጧል፡፡

ስታዲየሙ ሁለት አሳንሰሮች የተገጠሙለት ሲሆን፣ የተቀያሪ ተጫዋቾች የሚቀመጡበት ወንበር ከውጭ እየገባ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡ የስታዲየሙ ዕድሳት መጠናቀቁን ተከትሎ የድሬዳዋ ዋንጫ ጨዋታ  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድንና የዑጋንዳ አቻው ባደረጉት ግጥሚያ ተመርቋል። 

በሌላ ዜና በአዳማ ሳይንስና ቴክኖሎጂ ዩኒቨርሲቲ ሲከናወን የቆየው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ፣ ከየካቲት 21 ቀን ጀምሮ የሁለተኛ ዙር መርሐ ግብሩን  በድሬዳዋ ማከናወኑን ቀጥሏል፡፡

ብሔራዊ ቡድኑ ያሉበትን ጨዋታዎችና የኢትዮጵያ ዋንጫ ቀጣይ ጨዋታዎች ታሳቢ በማድረግ ከ16ኛ እስከ 22ኛ ሳምንት ያሉት መርሐ ግብሮች በድሬዳዋ ስታዲየም ከ23ኛ እስከ 27ኛ ሳምንት ጨዋታዎች በሐዋሳ ዩኒቨርሲቲ ስታዲየም፣ እንዲሁም የመጨረሻዎች ሦስት ሳምንታት በአዲስ አበባ ስታዲየም እንደሚደርጉ ታውቋል፡፡

ምንም እንኳን የድሬዳዋ ስታዲየም የአገር ውስጥ ውድድሮችን የማስተናገድ አቅም ቢኖረውም፣ ፊፋና ካፍ ያስቀመጡትን ሙሉ መሥፈርቶች ማሟላት ይጠበቅበታል፡፡

ከዚህም ጋር ተያይዞ በስታዲየሙ ዙሪያ የሚገኙ የትምህርትና እምነት ተቋማት፣ የፊፋና የካፍን ሙሉ ፈቃድ እንዳያሳጣው ሥጋት ፈጥረዋል፡፡

በፊፋና  በካፍ ሕግ መሠረት ስታዲየሞች ከእምነት ተቋማት፣ ከትምህርት ቤት፣ ከሆስፒታሎች ርቀው መገንባት አለባቸው፡፡

ሆኖም ‹‹በድሬዳዋ ስታዲየም አቅራቢያ የሚገኙት የትምህርና የእምነት ተቋማት ጉዳይ እንዴት ይሆናል?›› የሚለው የቀጣይ የከተማ አስተዳደሩ የቤት ሥራ መሆኑ ተጠቅሷል፡፡

በስታዲየሙ ዙሪያ ያሉት የትምህርትና የእምነት ተቋማት መፍትሔ ካልተበጀላቸው ካፍም ሆነ ፊፋ ዕውቅና ላይሰጡ እንደሚችሉ ይገመታል፡፡ በዚህም መሠረት ስታዲየሙ የፊፋን፣ እንዲሁም የካፍን መሥፈርቶችን አሟልቶ ለብሔራዊ ቡድኑ የስታዲየም አማራጭ ሆኖ መቅረብ ይገባል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...