Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበአፍሪካ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ይካፈላል

በአፍሪካ ጨዋታዎች የኢትዮጵያ ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድን ይካፈላል

ቀን:

  • 18 ተጫዋቾች ጥሪ ተደርጓል

በአፍሪካ ከሚከናወኑ ስፖርታዊ ውድድሮች ግንባር ቀደሙ በየአራት ዓመቱ የሚካሄደው የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች ነው። ኦሊምፒካዊ ይዘት ያለው ጨዋታው በስድስት አሠርታት ግድም ጉዞው  በተለያዩ አገሮች 12 ጊዜ ተካሂዷል። 13ኛው የአፍሪካ ጨዋታዎች ከመጪው የካቲት 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ ለሁለት ሳምንታት በጋና ከተሞች፣ አክራ፣ ኩማሲና ኬፕ ኮስት ይከናወናል።

ጨዋታዎቹ ቀደም ብሎ ነሐሴ 2023 መካሄድ የነበረበት ቢሆንም፣ በኢኮኖሚ ችግር፣ በዝግጅቱ መጓተትና ውድድሮቹን በሚመሩት መካከል ባሉ ጉዳዮች ምክንያት ነው ወደ 2024 የተሸጋገረው። ለ15 ቀናት የሚቆየው ዝግጅቱ መጋቢት 15 ቀን  የሚያበቃ ሲሆን፣ በሺዎች የሚቆጠሩ አትሌቶች  ይሳተፉበታል ተብሎ ይጠበቃል።

ከመጀመሪያው የብራዛቪል ጨዋታዎች ጀምሮ መካፈል የጀመረችው ኢትዮጵያ፣ ከአትሌቲክሱ ባሻገር ከ20 ዓመት በታች ሴቶች ብሔራዊ ቡድኗ ይካፈላል። በቅርቡ የብሔራዊ ቡድን ዋና አሠልጣኝ ሆነው የተሾሙት አሠልጣኝ ዮሴፍ ገብረ ወልድ ለ18 ተጫዋቾች ጥሪ ያደረጉ ሲሆን፣ ለጨዋታው ዝግጅት መጀመራቸው ተገልጿል፡፡

ውድድሩን የሚመራው አኅጉራዊው ኮንፌዴሬሽን ካፍ በወንዶች ዘጠኝ፣ በሴቶች ደግሞ ስምንት አገሮች በሁለት ምድብ ተከፍለው እንደሚፎካከሩ ገልጿል።

የኢትዮጵያ ብሔራዊ ቡድን በምድብ አንድ ከአዘጋጇ ጋና፣ ዑጋንዳና ታንዛኒያ ጋር የተደለደለ ሲሆን፣ የመጀመሪያ ግጥሚያውን የካቲት 30 ቀን ከጋና ሲያደርግ፣  መጋቢት 3 ቀን ከዑጋንዳ፣ እንዲሁም መጋቢት 6 ቀን  ከታንዛኒያ ጋር ይጫወታል፡፡

የአፍሪካ ኅብረት በበላይነት የሚመራው  የመላው አፍሪካ ጨዋታዎች በአኅጉሪቱ የሚገኙ በርካታ አትሌቶች ክህሎታቸውን እንዲያሳድጉ ዕድል እንደሚከፍት ታምኖበታል፡፡ በ2023 በኢትዮጵያ በተደረገው ስምምነት መሠረት የአፍሪካ ጨዋታዎችን  የአፍሪካ ስፖርት ምክር ቤትና  የአፍሪካ ኢሊምፒክ ኮሚቴዎች ማኅበር (አኖካ) በጋራ እንዲያዘጋጁት መወሰኑ ይታወሳል፡፡

ውድድሩ ከኦሊምፒክ አንድ ዓመት ቀደም ብሎ በየአራት ዓመቱ የሚዘጋጅ ቢሆንም፣ ቀደም ሲል እንደተገለጸው በአንዳንድ ጉዳዮች ምክንያት ወደ ዘንድሮ ተላልፏል።

የአፍሪካ ጨዋታዎች ለ2024 የፓሪስ ኦሊምፒክ ይፋዊ ማጣሪያ በመሆናቸው ለአፍሪካ አትሌቶች አስፈላጊነት አለው። በየውድድሩ የሚያገኙት ውጤት ካማረም በፓሪስ ኦሊምፒክ ይወዳደራሉ።

የአፍሪካ ጨዋታዎች ከስፖርታዊ ክንውኖች ባሻገር አፍሪካውያን ባህላቸውን የሚያሳዩበትና የሚያንፀባርቁበት መድረክ ነው፡፡

ጋና አማራጭ የመወዳደሪያ ሥፍራዎችን ለማቅረብ በከፍተኛ በጀት የገነባችው አዲስ የኦሊምፒክ ስታዲየም  ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ መሆኑ  ተጠቁሟል፡፡

23 ስፖርቶች የሚኖሩት የመላው አፍሪካ ጨዋታው የመዝጊያና የመክፈቻ መርሐ ግብር በአክራ ስፖርት ስታዲየም ይከናወናል፡፡ ክሪኬት ለመጀመሪያ ጊዜ በዘንድሮ ውድድር ይካተታል ተብሏል፡፡

በብስክሌት፣ ትራይትሎን፣ ባድሜንተን፣ ቴኒስ፣ ሪሲሊንግና ጠረጴዛ ቴኒስ የሚያሸንፉ በቀጥታ ለፓሪስ ኦሊምፒክ ያልፋሉ፡፡ ኢትዮጵያ ከአትሌቲክስና እግር ኳስ በተጨማሪ በውኃ ስፖርት ትካፈላለች።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...