Friday, April 19, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከተለያዩ አካባቢዎች ከመጡ የሕዝብ ተወካዮች ጋር ሕዝባዊ ውይይት እያደረጉ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር በእኛ አካባቢ መንገድ የለም፣ የመንገድ ግንባታ ይጀመራል ቢባልም ተስፋ ከመስጠት የዘለለ ነገር አልተገኘም።
 • ክቡር ሚኒስትር የእኛ አካባቢም መሠረታዊ ችግር መንገድ ነው፣ በተጨማሪም ከፍተኛ የመጠጥ ውኃ ችግር አለ።
 • ክቡር ሚኒስትር ከሌሎች አከባቢዎች የመጡ የሕዝብ ተወካዮች እንደተናገሩት ሁሉ የእኛ አካባቢ ችግርም መንገድ ነው፣ በዚህም ምክንያት እናቶች ወደ ሕክምና ጣቢያ መሄድ አልቻሉም፣ አርሶ አደሩም በመንገድ ችግር ምክንያት ምርቱን አውጥቶ መሸጥ አልቻለም።
 • አብዛኞቻችሁ የመንገድ መሠረተ ልማት ጥያቄ አንስታችኋል።
 • ለምሳሌ እዚያ ጋ ያሉት አባቴ የመጡበት አካባቢ ከፍተኛ ችግር መንገድ ነው ብለዋል።
 • አሁን እርስዎ የመጡበት አካባቢ መንገድ ባይሠራ እንኳ ገነት አይደለም?
 • እውነት ለመናገር በስብከት የምንሰማው ገነት ያለው እርስዎ የመጡበት አካባቢ ነው።
 • እዚያ ጋ ያሉት አባቴም የመንገድ ጥያቄ አንስተዋል።
 • ነገር ግን እርሶ የመጡበት አካባቢ ፓርክ ሠርተናል፣ ፓርክ ብቻ ሳይሆን ወደ ፓርኩ የሚወስድ መንገድም ገንብተናል።
 • ሌሎቻችሁም መንገድ፣ ውኃ፣ ሆስፒታል እንዲገነባላችሁ ጠይቃችኋል።
 • በሁላችሁም የማኅበረሰብ ተወካዮች የተነሱት ጥያቄዎች ሰላማዊና ልማታዊ ናቸው።
 • ነገር ግን ለተነሳው ጥያቄ ሁሉ መልስ አትጠብቁ ጥያቄዎቻችሁን መዝግበናል
 • ስለዚህ ከሌሎች ባልደረቦቼ ጋር እየተወያየን በዕቅድ የምናያቸው ይሆናል።

[ክቡር ሚኒስትሩ በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ሰሞኑን በቴሌቪዥን የተላለፉትን ውይይቶች በተመለከተ እያወጉ ነው]

 • እኔ የምልህ?
 • እ…?
 • እስኪ አንድ ጥያቄ ልጠይቅህ?
 • እሺ፣ ምንድነው?
 • አለቃችሁ ክቡር ሚኒስትር ሰሞኑን ሕዝባዊ ውይይት አድርገዋል ሲባል አልነበር እንዴ?
 • አዎ፣ ምነው?
 • ለማየት ፈልጌ ነበር።
 • ታዲያ ሰሞኑን በቴሌቪዥን ሲተላለፍ አልነበር እንዴ? አላየሽውም?
 • እሱንማ አይቸዋለሁ።
 • ታዲያ ምንድነው የፈለግሸው?
 • ወይይቱ ከሕዝብ ተወካዮች ጋር መስሎኝ ነበር።
 • ከሕዝብ ተወካዮች ጋርማ ነው የተካሄደው።
 • እሱን እንኳ ተወው።
 • እንዴት?
 • አይመስሉማ።
 • ምንድነው የማይመስሉት?
 • የሕዝብ ተወካይ።
 • እና ምንድነው የሚመስሉት?
 • የሊግ ተወካይ።
 • የምን ሊግ?
 • የወጣቶች፣ የሴቶች ምናምን እያላችሁ የምታደራጇቸው ሊጎች አሉ አይደል?
 • ግን እኮ ውይይቱ ላይ የሃይማኖት አባቶችና የአገር ሽማግሌዎችም ተገኝተዋል።
 • የሊግ አባል ሆነው ይሆናላ?
 • የየትኛው ሊግ?
 • የካህናትና የኢማሞች ሊግ ወይም ደግሞ…
 • እ…?
 • የአባ ገዳዎች ሊግ።
 • ኧረ በጭራሽ እንደዚያ ዓይነት አደረጃጀት የለንም።
 • የሚያወሩት ግን እንደዚያ ነው!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...

እጥረትና ውጥረት!

ጉዞ ከስድስት ኪሎ ወደ ቃሊቲ፡፡ ‹‹ይገርማል ቀኑ እንዴት ይሄዳል?››...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት። የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው? ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው። እሺ፣...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ? አላስታውስም። ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ በዕረፍት ቀናቸው በመኖሪያ ቤታቸው ሆነው ከባለቤታቸው ጋር ከውጭ እንዳይገቡ ስለተከለከሉ ምርቶች እያወሩ ነው]

እኔ እምልህ ...ኤል ሲ እንዳይከፈት ተከልክሏል ሲባል አልነበረም እንዴ? ኤል ሲ ደግሞ ምንድነው? ሌተር ኦፍ ክሬዲት ነዋ!? አልገባኝም? አስመጪዎች ከውጭ ለሚያስገቡት ዕቃ የሚያስፈልጋቸውን የውጭ ምንዛሪ ከባንኮች አይደል የሚያገኙት? አዎ። ኤል...