Thursday, April 18, 2024

ኦርቶፔዲክስ

Published on

- Advertisment -

በጡንቻ መገጣጠሚያ እና የአጥንት ህመሞች ላይ የላቀ ጥበብ፡የአጥንት ጉዳትን ችግር ከመመርመርም ያለፈ

የአጥንትና መገጣጠሚያ ህክምና (ኦርቶፔዲክስ) ተያያዥ ህመም በመመርመር፣ በማከም እና በመከላከል ላይ ያተኮረ የህክምና ዘርፍ ነው። እነዚህ ህመሞች በአጥንቶች፣ በመገጣጠሚያዎች፣ በጡንቻዎች፣ በጅማትና በነርቮች ላይ ተጽእኖ ያሳድራሉ። ኦርቶፔዲክስ እንደ ስፖርት ጤና እና የአጥንት ካንሰር ህክምናን የመሳሰሉትን አካትቶ ይዟል፡፡ እያንዳንዱ የህክምና አይነትም በጡንቻ መገጣጠሚያ እና አጥንት ጤና ላይ የተለየ አበርክቶ አለው፡፡

የስፖርት ጤና በኦርቶፔዲክስ

በኦርቶፔዲክስ ውስጥ የሚካተተው የስፖርት ጤና ከአካል ብቃት እንቅስቃሴ ጋር በተያያዙ ጉዳቶች እና ተቀራራቢ ችግሮች ላይ ያተኩራል፡፡የአጥንት ህክምና ባለሙያዎች የተለያዩ ጉዳዮችን ይመረምራሉ እና ያክማሉ:: ከትናንሽ ስንጥቆች እስከ ውስብስብ የጅማት መቆረጥ እና መተርተር ድረስ ያሉ ጉዳቶችን እና ሌሎችንም ችግሮች መፍትሔ ለመስጠት ይችላሉ። የተጎዱ መገጣጠሚያዎችን፣ ጅማቶችን እና የጅማት ክፍሎችን ለመጠገን እንደ አርትሮስኮፒክ ቀዶ ጥገና ያሉ ቴክኒኮችን ይጠቀማሉ። ግባቸውም አትሌቶች እና ሌሎችም ግለሰቦች ወደ ከፍተኛ የብቃታቸው ደረጃ እንዲመለሱ ማድረግ እና ለወደፊቱ ጉዳቶችን መከላከል ነው። ይህንንም ግባቸውን የሚያሳኩት በተቀረፁ የማገገሚያ መርሃ ግብሮች እና የአካል ጉዳት መከላከል ስልቶች ነው።

የአጥንት ካንሠር ህክምና (ኦርቶፔዲክ ኦንኮሎጂ)

ኦርቶፔዲክ ኦንኮሎጂ በጡንቻ መገጣጠሚያ እና አጥንት ስርዓት ላይ ተጽእኖ ያላቸውን እጢዎችን በመመርመር እና በማከም ላይ ያተኩራል፡፡ የእጢው መጠን ቀለል ያለ ወይም ወደ ካንሰርነት ደረጃ የተሸጋገረ እንዲሁም አደገኛ ሊሆን ይችላል፡፡ ካንሠሩ በአይነቱም በአጥንት ውስጥ፣  አጥንትን ከመገጣጠሚያ አካል ጋር የሚያገናኙ ለስላሳ ቲሹዎች ወይም ከ cartilage ውስጥ ሊቀሰቀስ ይችላል፡፡. ኦርቶፔዲክ ኦንኮሎጂ ሀኪሞች ለችግሩ መፍትሄ ለማግኘት ሁለገብ ዘዴዎችን ተግባራዊ ማድረግ ላይ ያተኩራሉ፡፡ ይህ ዕጢዎችን በቀዶ ሕክምና ማስወገድ፣ የተጎዱ አካባቢዎችን እንደገና ማጎልበት፣ የኬሞቴራፒ እና የጨረር ሕክምናን መስጠት እና ችግሩ እንዳይመለስ ክትትል ማድረግን ያካትታል። የህክምናው ዓላማም እንቅስቃሴ ሳይቋረጥ በሂደት ምርጡን ውጤት የሚያመጣ የተሟላ የጤና እንክብካቤ አገልግሎት መስጠት ነው።

በአብላጫው የሚዘወተሩት የኦርቶፔዲክ ቀዶ ጥገናዎች እና መንስኤዎቻቸው?

የተለመዱት የኦርቶፔዲክ ቀዶ ጥገናዎች እየተባባሱ ከሚሄዱ ህመመሞች߹ የህክምና ክትትል ከሚያሻቸው ጉዳቶች߹ ከልክ ያለፈ ህክምና ሂደት የጎንዮሽ ችግሮች ወይም ከአካላዊ አፈጣጠር እክል ጋር የመጡ የተለያዩ ሁኔታዎችን ይመለከታሉ፡፡ አጠቃላይ የጉልበት ወይም የዳሌ መገጣጠሚያ ቅየራ (TKR/THR) በዋናነት በሂደት የሚፈጠርን የመገጣጠሚያ አጥንቶች መፈረካከስን በተጨማሪም ከስፖርት ጋር ተያይዘው የሚመጡ ጉዳቶችን ወይም በአካል ላይ የሚያጋጥሙ ተደጋጋሚ ጫናዎች ላይ ያነጣጠሩ መፍትሄዎችን ይሰጣል።

Rotator Cuff Repairs ዓላማው ከልክ በላይ በሆነ የህክምና ሂደት የተፈጠረን ጉዳት፣ በጉዳት ወይም በእርጅና ምክንያት የተጎዱ የጅማት አካላት መጠገን ሲሆን ስፓይናል ፊውዥን የአከርካሪ አጥንት ግንኙነትን መፋለስ፣ ስብራትን ወይም የተጎዱ የአከርካሪ ህመሞችን ለማስወገድ ጥቅም ላይ ይውላል።

የAnterior Cruciate Ligament (ACL) ሪኮንስትራክሽን ከድንገተኛ እንቅስቃሴዎች ወይም ከስፖርት ጋር በተያያዙ ጉዳቶች ለሚመጡ የጅማት መቀደድ ችግሮች ምላሽ ይሰጣል።

የካርፓል ተነል በእጅ መዳፍ ላይ የሚፈጠርን የነርቭ ስሜት ማጣትን ያስወግዳል። የውስጥ አካል ጥገና በአይነቱ የስብራቶች ጥገና እንዲሁም በአደጋ፣ በመውደቅ ወይም በስፖርት ጉዳቶች ምክንያት የሚመጡ ከባድ ስብራቶችን ያስተካክላሉ። እነዚህ ቀዶ ጥገናዎች የአካልን ሥራን ወደነበረበት ለመመለስ እና ህመምን ለመቀነስ ሲባል በተለየ  መልኩ የአጥንት ጤንነት ሁኔታን እና በመንስኤው ላይ የተመረኮዘ ተገቢ ምርመራዎችን እንዲሁም በተለየ መልኩ ለሁኔታው የታቀዱ ህክምናዎችን ይፈልጋሉ፡፡

የተለመዱት የስፖርት ጉዳቶች እና የቀዶ ጥገና ሕክምናቸው?

ብዙውን ጊዜ የቀዶ ጥገና የሚያስፈልጋቸው የተለመዱ የስፖርት ጉዳቶች የጉልበት ሎሚ አገናኝ ክፍል Anterior Cruciate Ligament (ACL) መጎዳት ወይም መታደስ መፈለግ ወይም ሌሎች ተገቢ የጥገና ወይም መልሶ መገንባት የሚያስፈልጋቸው ናቸው። በትከሻ ወይም በዳሌ ላይ ያሉ መገጣጠሚያዎች የተጎዱትን ሕብረ ሕዋሳት ለመጠገን ወይም ለማስወገድ የህክምና ሂደቶችን ሊጠይቁ ይችላሉ።

የቁርጭምጭሚት አጥንቶች መገጣጠሚያ መጎዳት፣ ከባድ ስብራት፣ የጅማት መሰንጠቅ እና ሌሎች ውስብስብ ጉዳቶች የማስተካከል ወይም የጅማት መጠገን እንዲሁም መልሶ እንደመገንባት ያሉ የቀዶ ጥገና ዘዴዎችን ሊፈልጉ ይችላሉ። ለህክምናው የሚወሰኑት የቀዶ ጥገና ሂደቶች የታማሚውን የጉዳት መጠን፣ የታካሚው አጠቃላይ የጤና ሁኔታ፣ በስፖርታዊ እንቅስቃሴ እና በድህረ ማገገሚያ ግቦች ላይ የተመሰረቱ ናቸው፡፡ ከቀዶ ጥገና በኋላ የሚኖረው የማገገሚያ ሂደት እንቅስቃሴን ወደነበረበት ለመመለስ ወሳኝ ሚና ይጫወታል።

ለተጨማሪ ምክር በዚህ አድራሻ ያግኙን   www.acibademinternational.com

የቅርብ ጊዜ መጣጥፎች

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን አሟሟት በተመለከተ እሑድ ሚያዝያ 6...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን ጠቅላላ ጉባዔና የፀጥታ ምክር ቤቱን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ ንግድ እንዲሁም በገቢና ወጪ ንግድ...

ተመሳሳይ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር የጨረታ ማስታወቂያ

ቪር ጀነራል ትሬዲንግ ኃ/የተ/የግ/ማኀበር በገቢ እና በውጭ ንግድ እንዲሁም በቶነር አሴምብሊንግ ስራ የተሰማራ ድርጅት...

የአየርላንድ እና የኢትዮጵያ የ30 ዓመታት ግንኙነት ስናከብር

ዘንድሮ አየርላንድ ከኢትዮጵያ ጋር የሁለትዮሽ ግንኙነት የጀመረችበት 30ኛ ዓመት ቢሆንም ግንኙነቱ ግን ከዚያም በበለጠ...

የአየርላንድ ብሔራዊ ቀን – የቅዱስ ፓትሪክ ቀን – 2016 (እ.ኤ.አ. 2024)

“የቅዱስ ፓትሪክ ቀን ላይ ሆነን መጪውን ጊዜ ስንቃኝ” በእያንዳንዱ የቅዱስ ፓትሪክ ቀን በአለም ዙሪያ ያሉ...