Friday, April 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዓለምምዕራባውያኑ በተቃርኖ የተሠለፉበት የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ

ምዕራባውያኑ በተቃርኖ የተሠለፉበት የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ

ቀን:

‹‹ሩሲያ በአስቸጋሪ ጊዜ ውስጥ እያለፈች እንደሆነ ትገነዘባላችሁ ብዬ አምናለሁ፡፡ በሁሉም አቅጣጫ አስቸጋሪ ፈተናዎች ገጥመውናል፡፡ እነዚህን ችግሮች በውጤትና አንድ ሆነን ለመወጣት አንድ መሆንና በራሳችን ተማምነን መቀጠል አለብን››

የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ በሚካሄድበት ዋዜማ ይህንን ንግግር ያደረጉት ፕሬዚዳንት ቭላድሚር ፑቲን፣ ‹‹የሩሲያ ሕዝብ አንድ ትልቅ ቤተሰብ ነው›› ሲሉም ተደምጠዋል፡፡

ምዕራባውያኑ በተቃርኖ የተሠለፉበት የሩሲያ ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ሩሲያውያን አንድ ቤተሰብ መሆናቸውን ፑቲን ተናግረዋል
(አሶሺየትድ ፕሬስ)

ከሶቪየት ኅብረት መበታተን በኋላ ከተካሄዱ ምርጫዎች እሑድ መጋቢት 8 ቀን 2016 ዓ.ም. በተጠናቀቀው ፕሬዚዳንታዊ ምርጫ፣ 87 በመቶ ድምፅ በማግኘት ትልቁን የመራጭ ድምፅ ያስመዘገቡት ፑቲን፣ ለቀጣዮቹ ስድስት ዓመታት አገራቸውን የሚመሩ ይሆናል፡፡

- Advertisement -

Video from Enat Bank Youtube Channel.

በአምስተኛ የፕሬዚዳንትነት ዘመናቸው ሩሲያን ለቀጣይ ስድስት ዓመታት የሚመሩት የ71 ዓመቱ ፑቲን፣ መንበሩ የእሳቸው ሆኖ የሚቀጥል መሆኑን ተከትሎ ምዕራባውያን በተቃርኖ ሲሠለፉ ቻይና፣ ቬንዙዌላ፣ ቦስኒያ ሄርዞጐቪና፣ ለፑቲን ድጋፋቸውን ገልጸዋል፡፡

አሜሪካ፣ የአውሮፓ ኅብረት፣ ዩክሬንና እንግሊዝ ነፃና ፍትሐዊ ያልሆነ የምርጫ አካሄድ ነው ሲሉ የፑቲንን ማሸነፍ አጣጥለውታል፡፡

ከምዕራባውያን ወታደራዊና ሰብዓዊ ድጋፍ በምታገኘው ዩክሬንና ጉልህ ልዩነት ባላት ሩሲያ መካከል ከሁለት ዓመታት በላይ የዘለቀው ጦርነት መቋጫ አለማግኘቱና ሩሲያውያን አንድነታቸውን ለማስጠበቅ ያላቸው ኃላፊነት፣ ለፑቲን ማሸነፍ የጀርባ አጥንት ቢሆኑም፣ ምዕራባውያን ለፑቲን ማሸነፍ የእሳቸውን ጫና ፈጣሪነት ያጎሉታል፡፡

ሮይተርስ እንደሚለውም፣ በሩሲያ ውስጥ ፑቲን በጣም ዝነኛ ናቸው፡፡ በዩክሬን ጦርነት ምክንያት ከምዕራባውያን ጋር የገቡበት ፍጥጫም፣ ይበልጥ አገሬው እንዲፈልጋቸው አድርጓል፡፡ ጠንካራ ተፎካካሪ የሌለ በመሆኑም አጠቃላይ ሩሲያን እንዲቆጣጠሩ አስችሏል፡፡  

ከ114 ሚሊዮን መራጮች የ76 ሚሊዮኑን ድምፅ ያገኙት ፑቲን፣ በምዕራባውያኑ ዘንድ ይኮነኑ እንጂ፣ ለአገራቸው ጥንካሬ፣ ነፃነትና ሉዓላዊነት እንደሚያልሙ ተናግረዋል፡፡ ‹‹የተገኘው ውጤት ሁላችንም፣ ከሁሉም የሩሲያ ሕዝብ ጋር ሆነን ግባችንን እንድንመታ ያደርገናል፤›› ብለዋል፡፡

ከፑቲን ጋር የተወዳደሩት ሦስት ተፎካካሪዎች፣ ኮሙዩኒስቱ ኒኮላ ካሪቶኖቭ 4.3 በመቶ፣ የኒው ፒፕል ፓርቲ ቭላድስላቭ ዲቫንኮብ 3.9 በመቶ፣ የናሽናሊስት ሊበራል ዴሞክቲክ ፓርቲ ለአኒድ ስታስኮ 3.2 በመቶ ድምፅ አግኝተዋል፡፡

ፕሬዚዳንት ፑቲን ለመጀመሪያ ጊዜ ተወካይ ፕሬዚዳንት ሆነው የተመረጡት እ.ኤ.አ. በ1999 የቀድሞ የሩሲያ ፕሬዚዳንት ቦሪስ የልሲን ከሥልጣን ሲለቁ ነበር፡፡ በ2000 የመጀመሪያ የፕሬዚዳንትነት ሥልጣናቸውን በምርጫ አሸንፈው ሥልጣን የያዙት ፑቲን፣ ሁለተኛ ዙራቸውንም በ2004 አሸንፈዋል፡፡

በ2008 ጠቅላይ ሚኒስትር፣ በኋላ በ2012 ፕሬዚዳንት የሆኑት እኚህ ሰው፣ በ2018 ለአራተኛ ዙር ፕሬዚዳንት ሆነው መመረጣቸው ይታወሳል፡፡

ለሦስት ቀናት የዘለቀው ምርጫ በሚጠናቀቅበት ዕለት ቀድሞ ከነበሩት በተለየ በርካታ መራጮች ሰላማዊ ተቃውሞን በምርጫ ቦታዎች መራጭ ሆነው በመሠለፍ አሳይተዋል፡፡ 

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሰላማዊ የፖለቲካ ትግልና ፈተናው

የኦሮሞ ነፃነት ግንባር (ኦነግ) የፖለቲካ ኦፊሰር የአቶ በቴ ኡርጌሳን...

አበጀህ ማንዴላ! አበጀሽ ደቡብ አፍሪካ!

በአየለ ት. የፍልስጤም ጉዳይ የዓለም አቀፍ ፖለቲካንም ሆነ የተባበሩት መንግሥታትን...

የውጭ ባለሀብቶች ለኢትዮጵያውያን ብቻ በተፈቀዱ የንግድ ዘርፎች እንዲገቡ የመወሰኑ ፋይዳና ሥጋቶች

ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አዓመድ (ዶ/ር) የውጭ ኩባንያዎች በጅምላና ችርቻሮ...