Wednesday, May 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜና‹‹በሌሎች ክልሎች ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከትግራይ አንፃር አነስተኛ ነው ብዬ ለመግለጽ...

‹‹በሌሎች ክልሎች ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከትግራይ አንፃር አነስተኛ ነው ብዬ ለመግለጽ አልችልም›› ራሚዝ አላክባሮቭ (ዶ/ር)፣ የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት የኢትዮጵያ ተወካይና የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ 

ቀን:

…በኢትዮጵያ የተመድ ጽሕፈት ቤት ኃላፊና የሰብዓዊ ዕርዳታ አስተባባሪ እንደ መሆኔ ሁሉንም ክልሎች ጎብኝቻለሁ። በእርግጥ ትግራይ የጦርነቱ ማዕከል ነበረች። ነገር ግን በሌሎች ክልሎች ያለው የሰብዓዊ ዕርዳታ ፍላጎት ከትግራይ አንፃር አነስተኛ ነው ብዬ መግለጽ አልችልም። እንዲያውም በአንዳንድ ቦታዎች ከትግራይም የበለጠ ሰብዓዊ ቀውስ ሊኖር እንደሚችል አስባለሁ። የተወሰኑ የአፋር አካባቢዎችን፣ የአማራና የጋምቤላ አካባቢዎችን ጎበኝቻለሁ፡፡

በእነዚህ አካባቢዎችም ብዙ ችግሮችን አይቻለሁ። አንዳንዶቹም በከፋ ሁኔታ ሊገለጹ የሚችሉ ናቸው። ስለዚህ አንዱን አካባቢ ከሌላው ማወዳደር አልፈልግም። የተመድና ሌሎች የረድኤት ድርጅቶች ባለሥልጣናት ለምን ትግራይ ክልል ደጋግመው ለመጎብኘት መረጡ ለሚለው፣ በጦርነቱ ምክንያት የተለየ ትኩረት ወደ ትግራይ አመዝኗል። በተጨማሪም በጣም ንቁ የሆኑ በውጭ የሚኖሩ የትግራይ ተወላጆች የፈጠሩት ተፅዕኖ አለ። ነገር ግን እኔ ኢትዮጵያን ለመጎብኘት ለሚመጡ የተመድ ኃላፊዎች በሙሉ የማስተላልፈው መልዕክቴ፣ ለሁሉም ክልሎች እኩል ትኩረት ሰጥተው ሁሉንም ባሳተፈና በተደራጀ መንገድ እንዲሠሩ ነው፡፡… የኢትዮጵያ ዳያስፖራ አባላት ከተለያዩ የኢትዮጵያ አካባቢዎች እንደ መውጣታቸው መጠን፣ በአንዳንዶቹ ችግሮች ላይ የበለጠ ትኩረት ሊሰጡ ይችላሉ። ዞሮ ዞሮ መጨረሻ ላይ ትኩረት የምታገኘው ግን ኢትዮጵያ ነች።… ለሙሉ ዘገባው ሊንኩን ይጫኑ::

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...