Wednesday, May 29, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

ባለ ሀብቱ ወርቁ አይተነው የዘይት ፋብሪካቸውን አስይዘው የገዙት መኖሪያ ቤት ለጨረታ ቀረበ

spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

ዘመን ባንክ ባለሀብቱ አቶ ወርቂ አይተናው በአምስት ቢሊዮን ብር የገነቡትን የዘይት ፋብሪካ አስይዘው የገዙትን የመኖሪያ ቤት በጨረታ ሊሸጥ መሆኑን አስታወቀ፡፡

ባለቤትነቱ የታዋቂው ባለሀብት ወርቁ አይተነው የሆነው ደብሊው ኤ የምግብ ዘይት ማጣሪያ ፋብሪካ ስም ብድር የተወሰደው መኖሪያ ቤት፣ በአዲስ አበባ የካ ክፍለ ከተማ ባለ ሦስት ፎቅ ሕንፃ ሲሆን 1,403 ካሬ ሜትር ስፋት ያለው ነው።

የጨረታው መነሻ ዋጋ 62.7 ሚሊዮን ብር ሲሆን፣ ጨረታው የሚከፈተው  ግንቦት 2 ቀን 2016 ዓ.ም. በዘመን ባንክ ዋና መሥሪያ ቤት መሆኑን የወጣው የሐራጅ ማስታወቂያ ይገልጻል።

የጨረታ ሰነዱን በበላይነት የሚቆጣጠረው ዘመን ባንክ፣ አሸናፊ የሆኑ ተጫራቾች የግዥውን ዋጋ ግማሽ የሚደርስ ብድር ከባንኩ ሊያገኙ ይችላሉ ብሏል።

በአማራ ክልል ደብረ ማርቆስ የሚገኘው ደብሊው ኤ የዘይት ፋብሪካ፣ በአምስት ቢሊዮን ብር ኢንቨስትመንት ተገንብቶ በ2013 ዓ.ም. መከፈቱ ይታወሳል።

ይሁን እንጂ ከአንድ ዓመት በፊት በውጭ ምንዛሪ በግብዓት እጥረትና የግብር ጫናዎች ምክንያት ምርቱ መቆሙን ሪፖርተር መዘገቡ ይታወሳል።

የዘይት ፋብሪካው ዓመታዊ በጀት 203.6 ሚሊዮን ዶላር ሲሆን፣ ከዚህ ገንዘብ ውስጥ 131 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋው ድፍድፍ ዘይት ከውጭ ለማስገባት፣ 53 ሚሊዮን ዶላር ለሌሎች ኬሚካሎችና 19 ሚሊዮን ዶላር የሚጠጋው የማሸጊያ ዕቃዎች ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት መሆኑን ሪፖርተር የደረሰው መረጃ ያሳያል።

በቀን 1.3 ሚሊዮን ሊትር የምግብ ዘይት የማምረት አቅም ያለው ደብሊው ኤ  ዘይት ማቀነባበሪያ ፋብሪካ፣ የምርት ግብዓቶችን ከውጭ ማስመጣት የቻለው አንድ ጊዜ ብቻ ሲሆን፣ ፋብሪካው ከተመረቀበት ጊዜ አንስቶ ያመረተው አንድ ጊዜ ብቻ መሆኑን ሪፖርተር መዘገቡ ይታወሳል።

ከወራት በፊት አቢሲኒያ ባንክ በቂርቆስ ክፍለ ከተማ አዲስ አበባ የሚገኘውን መኖሪያ ቤት በ40.3 ሚሊዮን ብር መነሻ ዋጋ ለጨረታ ማቅረቡ ይታወሳል። ባለሀብቱ አቶ ወርቁ አይተነው ለምንና በምን ምክንያት እንደሆነ ባይታወቅም ከአገር መውጣታቸው ይታወቃል፡፡

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች