Wednesday, May 29, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከፖለቲካ ፓርቲዎች የጋራ ምክር ቤት አባላት ጋር በአገራዊ ጉዳዮች ላይ እየመከሩ ነው]

 • ክቡር ሚኒስትር ባለፈው ሊያወያዩን ሲመጡ ለአገራችን የፖለቲካ ችግር መፍትሔው አንድና አንድ እንደሆነ ነግረንዎት ነበር፣ ያስታውሳሉ?
 • አላስታውስም።
 • ባለፈው የተገናኘን ጊዜ ይህችን አገር ከችግር የሚያወጣው መፍትሔ አንድና አንድ እንደሆነ ብቻ ሳይሆን ምን እንደሆነም ነግረንዎት ነበር።
 • መፍትሔ ያላችሁት ነገር ምን ነበር?
 • የሽግግር መንግሥት ማቋቋም፡፡
 • አዎ፣ እንደዚያ ብላችሁ ሳንግባባ ነበር የተለያየነው።
 • ትክክል።
 • እሺ አሁንም አቋማችሁ ያው ነው?
 • አይደለም ክቡር ሚኒስትር።
 • እና መፍትሔው ምንድነው ትላላችሁ?
 • እርስዎ የሰጡትን አቅጣጫ አስበንና አሰላስለን ተግባብተናል።
 • ምንድነው የተግባባችሁት?
 • ዋናው የዚህ አገር ችግር የፖለቲካ ፓርቲዎች መብዛት መሆኑን ለይተን በመፍትሔው ላይም ተግባብተናል።
 • መፍትሔው ምንድነው አላችሁ?
 • መፍትሔው ሰብሰብ ማለት ነው ብለናል።
 • በዚህ ጉዳይ ላይ ተስማማችሁ?
 • የተቃዋሚ ፓርቲዎች መብዛት ለትግል አመቺ ስላልሆነ ተስማምተናል፣ ግን….
 • ግን ምን?
 • በፍጥነት ለመሰባሰብ ደግሞ ጠቅላላ ጉባዔ ማካሄድና ማስወሰን አለብን።
 • ልክ ነው።
 • ያው እርስዎ እንደሚገነዘቡት ደግሞ ጠቅላላ ጉባዔ ለማካሄድ በትንሹ ሁለት ሚሊዮን ብር ይፈጃል።
 • ስለዚህ?
 • ስለዚህ ገዥው ፓርቲ እንዲመድብልን ለመጠየቅ ነው።
 • ምን?
 • መሰባሰቢያ በጀት!

[ክቡር ሚኒስትሩ በእረፍት ቀናቸው ከባለቤታቸው ጋር እየተጨዋወቱ ሳለ ያልጠበቁት ርዕስ በድንገት ተነስቶ ራሳቸውን ለመከላከል እየሞከሩ ነው]

 • እኔ ምልህ?
 • እ…?
 • የአንተ የሥልጣን ሁኔታ ግን አያሳስብህም?
 • ለምን ያሳስበኛል?
 • አልረጋ ማለቱ ነዋ?
 • እንዴት?
 • ከመሬት ጋር የተገናኘ ኃላፊነት ላይ በነበርክ ጊዜ ኑሯችንም ጥሩ ነበር፣ ግን…
 • ግን ምን?
 • ብዙም ሳትቆይ አነሱህ።
 • ብነሳም ሌላ ትልቅ ኃላፊነት ላይ ነው የተመደብኩት።
 • እሱስ ልክ ነህ፣ ግን…
 • ግን ምን?
 • እዚያም ብዙ ሳትቆይ አነሱህ።
 • ቢሆንም በሚኒስትር ማዕረግ የዴሞክራሲ ጉዳዮች አስተባባሪ ተደርጌ ነው የተሾምኩት፡፡
 • ግን እዚያም ብዙ ሳትቆይ አነሱህ።
 • ቢሆንም አሁንም የምመራው ዘርፍ ቀላል አይደለም።
 • እሱማ ልክ ነው፡፡
 • ታዲያ ምንድነው ያሳሰበሽ?
 • አንድ ቦታ ጥሩ ስትተሠራ ያነሱሃል፣ ወደ ሌላ ቦታ ይመድቡሃል፣ እዚያም ጥሩ መሥራት ስተጀምር ትነሳለህ፣ ለምንድነው አንድ ኃላፊነት ላይ ብዙ የማያቆዩህ?
 • እሱ እንኳን ብዙ የሚያሳስብ አይደለም።
 • ለምን አያሳስብም?
 • ምክንያቱም የኃላፊነት ምደባ ታክቲክ ነው።
 • የምን ታክቲክ?
 • የፓርቲያችን፡፡
 • ከቦታ ቦታ የሚያዘዋውሩህ ለታክቲክ ነው እያልክ እንዳይሆን?
 • አዎ፣ ለፓርቲያችን ታክቲክ እስከጠቀመ ድረስ የትም ቦታ ብመደብ ችግር የለውም፡፡
 • እኔ ግን ታክቲክ አይመስለኝም።
 • ምንድነው የሚመስልሽ?
 • እኔ እንጃ ብቻ…
 • ብቻ ምን?
 • ታክቲክ አይመስለኝም፡፡
 • ምንድነው የሚመስልሽ ታዲያ?
 • ብቻ አንተን ከአንድ ቦታ ሲያነሱህ የሆነ ነገር እየሆንክ ይመስለኛል።
 • ምን የሆንኩ ነው የሚመስልሽ?
 • የልማት ተነሺ፡፡
 • ታስቂያለሽ፡፡
 • ለምን አስቃለሁ? የምሬን ነው፡፡
 • የምርሽን ከሆነ ለምን አትጠይቂም?
 • ምን?
 • የልማት ተነሺ ካሳ፡፡
 • ሰሞኑን ለፓርላማ ስለቀረበው አዋጅ አልሰማህም እንዴ?
 • የምን አዋጅ?
 • ረቂቅ አዋጅ ነዋ?
 • እኮ አዋጁ ስለምንድን ነው?
 • የፌዴራል መንግሥትን ነፃ የሚያደርግ ነው።
 • ከምንድን ነው ነፃ የሚያደርገው?
 • ለልማት ተሺዎችዎች ካሳ ከመክፈል!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...

እኛ ኢትዮጵያውያን ከየት መጥተን ወዴት እየሄድን ነው?

በአሰፋ አደፍርስ ኢትዮጵያውያን ከየትም እንምጣ ከየት እስከ 1445 ዓ.ም. እስላማዊና...

የሳባ መንደር

ሼባ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሼባ/ሳባ የጉዞ ወኪል...

የበጀት እጥረት የፈተነው የአኅጉሩ የባህል ዘርፍ

የአፍሪካ አገሮች ቢያንስ ከበጀታቸው አንድ ፐርሰንቱን ለባህል ዘርፍ መዋል...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እንዲሳተፉ ከተለዩ ባለሀብቶች መካከል እንዱ ጋ ስልክ ደውለው በንቅናቄው ላይ እንዲሳተፉ ግብዣቸውን እያቀረቡ ነው]

መቼም ኢትዮጵያ ታምርት በሚል የተጀመረውን አገር አቀፍ ንቅናቄ ሳትሰማ አትቀርም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ልክ ነው፣ ሰምቻለሁ ክቡር ሚኒስትር። አሁን ደግሞ ንቅናቄውን ለማጠናከር ኢትዮጵያ ታምርት የሚል የታላቁ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...