Wednesday, May 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበግጭት ለተጎዱ ልጆች 80 ሺሕ መጻሕፍት ማሠራጨት መጀመሩን ኢትዮጵያ ሪድስ አስታወቀ

በግጭት ለተጎዱ ልጆች 80 ሺሕ መጻሕፍት ማሠራጨት መጀመሩን ኢትዮጵያ ሪድስ አስታወቀ

ቀን:

በኢትዮጵያ በግጭት ምክንያት ከትምህርት ቤት ለተስተጓጐሉ፣ በሥነ ልቦናና በሌሎች ግጭት በሚፈጥራቸው ችግሮች ለተጎዱ ልጆች የተለያዩ ይዘት ያላቸው 80 ሺሕ የልጆች መጻሕፍትን በየቋንቋው አሳትሞ እያሠራጨ እንደሚገኝ ኢትዮጵያ ሪድስ አስታወቀ፡፡

ድርጅቱ በግጭት ምክንያት ለተፈናቀሉና ትምህርት ላቋረጡ ሕፃናት መጻሕፍት ለማቅረብ ሥራውን ሲጀምር፣ ይህ ቅድሚያ አይደለም በሚል እክል ገጥሞት እንደነበር ሆኖም በተደረጉ ውይይቶች ሊሳካ መቻሉን የኢትዮጵያ ሪድስ ፕሮግራም ዳይሬክተር አቶ ብርሃኑ ግርማ ተናግረዋል፡፡ 

የመጻሕፍት ሥርጭቱ መከናወን ልጆችን ከድብርት በማውጣት ተስፋ እንዲኖራቸውና ከትምህርት ቤት መቋረጥ ጋር ተያይዞ የቀረባቸውን መሠረታዊ ትምህርት ቤታቸው ሆነው እንዲማሩ እንደሚያስችል፣ ከሰብዓዊ ድጋፍና ከሌሎች የዕርዳታ ሥራዎች እኩል እንዲታይና እንዲካተት እንደሚያስገነዝብም አክለዋል፡፡

- Advertisement -

በአማራ፣ በትግራይ፣ በአፋር፣ በኦሮሚያና በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ክልሎች ለሚገኙ ልጆች የተዘጋጁት መጻሕፍት፣ በየክልሎቹ ትምህርት ቢሮዎች ተገምግመው የጸደቁ መሆኑን፣ በቤኒሻንጉል ጉሙዝ ባለው የመንገድ ችግር ምክንያት መሠራጨት እንዳልጀመረ ጠቁመዋል፡፡

የድርጅቱ አብዛኛው የፕሮጀክት ትኩረት ሕፃናት ላይ ሲሆን፣ ከተቋቋመበት ጊዜ አንስቶም በመቶ ሺዎች የሚቆጠሩ የአገር ውስጥና የውጭ አገር መጻሕፍትን ለሕፃናትና ለተማሪዎች ተደራሽ ማድረጉን ተናግረዋል፡፡

ከመጽሐፍ ህትመት ጋር ተያይዞ ድርጅቱ ከዚህ በፊት ካሳተማቸው መጻሕፍት በተጨማሪ ከኦፕን ኸርትስ ቢግ ድሪምስ ፋውንዴሽን ጋር በመሆን ከ200 ሺሕ በላይ የሕጻናት መጽሐፍትን በአማርኛ፣ በኦሮምኛ፣ በሲዳምኛ፣ በአፋሪኛ፣ በትግርኛ፣ በጉሙዝ፣ በሺናሻ፣ በዲዚኛና በጠምባሪሳ፣ 45 በሚደርሱ ርዕሶች በማዘጋጀትና በማሳተም በተለያዩ የአገሪቱ ክልል ከተሞች በሚገኙ ትምህርት ቤቶችና የንባብ ማዕከላት ውስጥ በነፃ አሠራጭቷል ብለዋል፡፡ 

ኢትዮጵያ ሪድስ ንባብ በኢትዮጵያ ውስጥ እንዲስፋፋና እንዲጎለብት ዋና መቀመጫውን በአሜሪካ አድርጎ የሚሠራ የበጎ አድራጎት ድርጅት ነው፡፡ ካለፉት 22 ዓመታት ወዲህ፣ በኢትዮጵያ ትምህርትን ለማስፋፋት ቤተ መጻሐፍትን መገንባት፣ በመንግሥት የመጀመሪያ ደረጃ ትምህርት ቤቶች ውስጥ ቤተ መጻሕፍትን  ማቋቋም፣ ለቤተ መጻሕፍት ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ሥልጠና መስጠት ከሚሠራቸው ሥራዎች ይጠቀሳሉ፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን...

የኢትዮ ኤርትራ ሰሞነኛ ሁኔታና ቀጣናዊ ሥጋቱ

“ግንቡን እናፍርስ ድልድዩን እንገንባ” የሚል ፖለቲካዊ መፈክር ጎልቶ በሚሰማበት፣...

ኦሮሚያ ባንክ ከተበዳሪ ደንበኞቼ ውስጥ 92 በመቶ የሚሆኑት አነስተኛና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች ናቸው አለ

ኦሮሚያ ባንክ ለደንበኞቹ ከሰጠው ብድር ውስጥ ለአነስተኛና ለመካከለኛ ኢንተርፕራይዞች...

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...