Wednesday, May 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊየወጣቶችን ፈጠራ የሚያስቃኘው የስታርት አፕ ዓውደ ርዕይ

የወጣቶችን ፈጠራ የሚያስቃኘው የስታርት አፕ ዓውደ ርዕይ

ቀን:

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ያዘጋጀው ‹‹ስታርት አፕ ኢትዮጵያ›› ዓውደ ርዕይ ከመጋቢት 30 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ በመካሄድ ላይ ነው፡፡

ለሦስት ሳምንት በሚዘልቀው ዓውደ ርዕይ በኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ፣ በግብርና፣ በጤና፣ በትምህርት፣ በኢንዱስትሪ፣ በፋይናንስና በሌሎች ዘርፍ የተሰማሩ ጀማሪ ሥራ ፈጣሪዎች ‹‹ስታርት አፖች›› ሥራዎቻቸውን በማስተዋወቅ ላይ ናቸው።

በዓውደ ርዕዩ የመጀመርያ ደረጃ ላይ የሚገኙ፣ የመጀመርያ ደረጃውን የተሻገሩ፣ ወደ ገበያ መቀላቀል ደረጃ ላይ የደረሱ በሚል የተከፈሉ ስታርት አፖች በዙር እየተሳተፉ ይገኛሉ።

- Advertisement -

ሥራዎቻቸውን ካቀረቡ በርካታ ተሳታፊዎች መካከል የኤድ ቴክ ድርጅት መሥራችና ሥራ አስኪያጅ አቶ አብዲ ጀማል አንዱ ናቸው፡፡

ድንገተኛ አደጋ አጋጥሟቸው ወይም የቴክኒክ ችግር ገጥሟቸው ለቀናት ወይም ለሳምንታትና ከዚያም በላይ ለሆኑ ቀናት መንገድ ዘግተው የሚቆሙ ተሽከርካሪዎች በፍጥነት እንዲነሱና ጥገና እንዲደረግላቸው የሚያግዝ ቀልጣፋ አሠራርን ለመዘርጋት ያለመ ሥራን ለመሠራት ጅማሮ ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡

አደጋ የደረሰባቸው አሽከርካሪዎች ወደ ጥሪ ማዕከላቸው በመደወል ወይም በተዘጋጀ የሞባይል መተግበሪያ (አፕልኬሽን) አማራጭን በመጠቀም በፍጥነት ሳይውል ሳያድር አገልግሎቱን ማግኘት የሚችሉበትን አሠራር ለመዘርጋት እየሠሩ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

 ፈጠራው የትራፊሪክ መጨናነቅን ከማቃለሉም በላይ፣ ባለንብረቶች ንብረታቸውን ወደሚፈልጉት ጋራዥ ወስደው እንዲሠሩ የሚረዳ ነው ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል በቅርቡ ገበያውን እየተቀላቀሉ ያሉ በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎችን ቻርጀ ማድረጊያ ማሽኖችን በተመረጡ ቦታዎች መትከልና ቀልጣፋ አገልግሎትን እንዲያገኙ ለማስቻል እየሠሩ መሆኑን ሥራ አስኪያጁ ተናግረዋል፡፡

የቻርጀ ማሽኖቹ ‹‹ኢትዮ ቻርጅ›› የሚል ስያሜ የተሰጣቸው ሲሆን፣ በተለይ ብዛት ያላቸው ተሸከርካሪዎች በሚቆሙበት እንደሚከተሉ፣ ትንንሽ ማሽኖች ደግሞ በቤት ውስጥም ማስገጠም እንደሚቻል አቶ አብዲ ገልጸዋል፡፡

ቴክኖሎጂው በተለይ ለኢትዮጵያ አዲስ ከመሆኑም አንፃር አሽከርካሪዎች ቻርጅ ማድረጊያ ማሽን የት እንደሚገኝ በቀላሉ ለማወቅ መቸገራቸው የማይቀር ነው፡፡ ችግሩን ከወዲሁ ለመፍታት ኤድ ቴክ ቻርጅ ማድረግያ ማሽኖችን ከመትከል ባሻገር፣ የት እንደሚገኙና በሌሎች ተሽከርካሪዎች መያዝ አለመያዙን (ወረፋ) ለማወቅ የሚረዳ መተግበሪያ ማበልፀጋቸውን አቶ አብዱ ተናግረዋል፡፡

ለጀማሪ ወጣቶች ስታርት አፖች ላይ በዋናነት መሥራት የተፈለገው መሬት ላይ ካለው ችግር ጋር በቀጥታ ስለሚገናኙና ለችግሮችም መፍትሔን ከማፍለቅ አንፃር ቀልጣፋ በመሆናቸው እንደሆነ የተናገሩት በኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር የኢኖቬሽን ልማትና ምርምር ሥራ አስፈጻሚ አቶ ሰላምይሁን አደፍርስ ናቸው፡፡

ጅማሮው ሥራ ጀማሪዎች ችግሮችን በመፍታት ረገድ በስፋት እንዲሳተፉ ዕድል የሚሰጥ የቢዝነስ ዓይነት ነው ሲሉ አብራርተዋል፡፡

ውጤታማነቱንም በተሞክሮ ማየታቸውን የተናገሩት አቶ ሰላምይሁን፣ ከዚህ ቀደም በኢኖቬሽን ቴክኖሎጂ ተደግፈው ወደ ሥራ የገቡ ስታርት አፖች በተሰማሩበት መስክ ጥሩ ውጤትን ማስመዝገባቸውን አስታውሰዋል፡፡

ስታርት አፕ ከተለመደው ጥቃቅንና መካከለኛ ኢንተርፕራይዞች የተለየ ሲሆን፣ ለራሱ ስታርት አፕ ተብሉ ዕውቅና እንዲሰጠው ለማድረግ እየተሠራ መሆኑን ሥራ አስፈጻሚው ተናግረዋል፡፡

‹‹ስታርት አፖች ፈጠራ መር ናቸው›› ያሉት አቶ ሰላምይሁን፣ የኢትዮጵያ የስታርት አፕ ሥነ ምኅዳር በዓለም አቀፍ መለኪያ ሲታይ ከኬንያና ከሌሎች የአፍሪካ አገሮች ጋር ሲወዳደር ገና ወደ ኋላ የቀረ ነው ብለዋል፡፡

ጥሩ የቴክኖሎጂ ፈጣሪዎችን ለማስፋፋት የተለያዩ ፖሊሲዎች እየተዘጋጁ እንደሆነ በራሳቸው ጥረት የተለያዩ የፈጠራ ሥራቸውን በማበልፀግ ዘርፉ ውጤታማ እንዲሆንና ሥራ ፈጣሪዎችም ተቀጣሪ ለመሆን ሳይሆን በሥራቸው ለሌሎች የሥራ ዕድል እንዲፈጥሩ እንደሚረዳ ተናግረዋል፡፡

 ለስታርት አፕ ዘርፉ ዕድገት መሠረት የሚጥሉ የተለያዩ የሕግና የፋይናንስ አሠራር ማሻሻያዎች መደረጋቸውን የሥራና ክህሎት ሚኒስቴር መናገራቸው ይታወሳል።

የስታርት አፕ ኢትዮጵያ ዓውደ ጥናት በተዘጋጀበት ወቅት ቴክኖሎጂን ማዕከል አድርገው በሚከናወኑ ችግር ፈቺ የፈጠራ ሥራዎችን ለማበረታታት የሚረዱ የተለያዩ ማዕቀፎች ላይ ማሻሻያ ተደርጓል።

ከተደረጉ ማሻሻያዎች መካከል አንዱ የፈጠራ ሐሳብ ያላቸው ወጣቶች ሐሳባቸውን ወደ ተግባር ለማዋል በሚፈልጉበት ወቅት ያለምንም የንግድ ቤት ኪራይ ውል ሥራ መጀመር የሚችሉበትን አዲስ አሠራር መዘርጋት፣ ማንኛውም የውጭ አገር ፈንድ ያገኘ ስታርት አፕ ሙሉ በሙሉ የውጭ ምንዛሪውን ለሚፈልገው ሥራ ማዋል የሚችልበት አሠራር ተግባራዊ መደረጉ ተመላክቶ ነበር።

አዲስ ፈጠራ ያላቸውና ሥራቸው ወደ ገቢ መቀየር የሚችሉ ወጣቶች በውጭ አገሮች ለተለያዩ አገልግሎቶች ክፍያ በሚጠየቁበት ወቅት በባንኮች በኩል መንግሥት በሚያመቻቸው አሠራር ክፍያ መፈጸም የሚችሉበት አማራጭ ይመቻችላቸዋል የተባለ ሲሆን፣ አሠራሩም ዓለም አቀፋዊ ለሆነው የስታርት አፕ ዘርፍ ምቹ ምኅዳር የሚፈጥር መሆኑን መነገሩ ይታወሳል።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሽቅብና ቁልቁል!

ጉዞ ከመገናኛ ወደ ሲኤምሲ ጀምረናል። ተሳፋሪዎች የዕለት ጉርሳቸውን መሸፈን...

እኛ ኢትዮጵያውያን ከየት መጥተን ወዴት እየሄድን ነው?

በአሰፋ አደፍርስ ኢትዮጵያውያን ከየትም እንምጣ ከየት እስከ 1445 ዓ.ም. እስላማዊና...

የሳባ መንደር

ሼባ ግሩፕ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር በሼባ/ሳባ የጉዞ ወኪል...

የበጀት እጥረት የፈተነው የአኅጉሩ የባህል ዘርፍ

የአፍሪካ አገሮች ቢያንስ ከበጀታቸው አንድ ፐርሰንቱን ለባህል ዘርፍ መዋል...