Tuesday, May 28, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊበአዲስ አበባ ከ700 ሺሕ በላይ የትራፊክ የደንብ ጥሰቶች መፈጸማቸው ተገለጸ

በአዲስ አበባ ከ700 ሺሕ በላይ የትራፊክ የደንብ ጥሰቶች መፈጸማቸው ተገለጸ

ቀን:

በአዲስ አበባ 716,624 የትራፊክ የደንብ ጥሰቶች መፈጸማቸውን፣ የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር የመንገድ ደኅንነት ምክር ቤት የ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወራት ዕቅድ አፈጻጸም ሪፖርት አመለከተ፡፡

ሚያዚያ 3 ቀን 2016 ዓ.ም. ሪፖርቱን አስመልክቶ በተካሄደው የውይይት መድረክ ከጥሰቶቹ መካከል ከፍጥነት በላይ ማሽከርከር፣ የደኅንነት ቀበቶ ሳያስሩ ማሽከርከር፣ ሄልሜት (ቆብ) ሳያደርጉ ማሽከርከርና ስልክ እያነጋገሩ ማሽከርከር ተጠቃሾች ናቸው፡፡

የአዲስ አበባ ትራፊክ ማኔጅመንት ባለሥልጣን ዋና ዳይሬክተር አቶ ክበበው ሚደቅሳ እንደተናገሩት፣ በ2016 ዓ.ም. በትራፊክ አደጋ 286 ሰዎች ሕይወታቸውን አጥተዋል፡፡ 1408 ሰዎች ከባድ የአካል ጉዳት የደረሰባቸው ሲሆን፣ 1220 የሚሆኑት ደግሞ ቀላል ጉዳት የደረሰባቸው ናቸው፡፡

- Advertisement -

እንደ አቶ ክበበው፣ የዘንድሮው ከዓምናው ጋር ሲነፃፀር፣ የሞት መጠን በ6.23 በመቶ፣ ከባድ አካል ጉዳት ደግሞ በ4.41 በመቶ ቀንሷል፡፡

የአዲስ አበባ ትራንስፖርት ቢሮ ኃላፊና የምክር ቤቱ ምክትል ሰብሳቢ አቶ ምትኩ አስማረ እንደተናገሩት፣ ምክር ቤቱ የመንገድ ደኅንነት ስትራቴጂ በመንደፍ የመንገድ ደኅንነት አስተዳደር ሥርዓት የመገንባት፣ አደጋ በሚበዛባቸው ዋና መንገዶች ላይ በማተኮር ለእግረኞች ቅድሚያ እንዲሰጥ፣ በግንዛቤ ማስጨበጫ ሥራዎች በመታገዝ ቁልፍ የደኅንነት ሕጎችን ማስከበር ላይ ትኩረት አድርጎ በመሥራት ላይ ነው፡፡

የትራፊክ አደጋና የአካል ጉዳት መረጃ አስተዳደር ሥርዓትን መገንባትና የድኅረ አደጋ የሕክምና አገልግሎትን ማጠናከር ላይ አፅንኦት መስጠቱንም አክለዋል፡፡

በከተማ አካባቢ ከሚደርሱ አደጋዎች መካከል ከ85 በመቶ በላይ የሚሆነው ለእግረኛ ቅድሚያ አለመስጠት ነው፡፡ ይህንን ለመከላከል የእግረኛ መብራቶች ጥገና በማካሄድና የእግረኛ መሻገሪያ የትራፊክ መብራቶች ግዥ በመፈጸም የተከላ ሥራ በመከናወን ላይ ነው ተብሏል፡፡

ከ2016 እስከ 2018 ዓ.ም. በመንገድ ደኅንነት ስትራቴጂ በተቀመጠው ግብ መሠረት፣ የሞትና ከባድ ጉዳት አደጋን ዘጠኝ በመቶ ለመቀነስ ታቅዶ እየተሠራ እንደሚገኝ ገልጸዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...