Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትበዶፒንግ ምክንያት ድሏን ለኢትዮጵያዊቷ ያሳለፈችው ኬንያዊት

በዶፒንግ ምክንያት ድሏን ለኢትዮጵያዊቷ ያሳለፈችው ኬንያዊት

ቀን:

  • በሮተርዳምና በቦስተን ማራቶን ያሸነፉት ኢትዮጵያውያን

ከቅርብ ዓመታት ወዲህ አንዳንዶች አትሌቶች ተፈጥሮ በለገሰቻቸው ፀጋ አልያም ጠንክሮ በመሥራት አሸናፊ ከመሆን ይልቅ፣ በመድኃኒት መልክ ተቀምመው በሚዘጋጁ አበረታች ቅመሞች በመጠቀም በአቋራጭ ውጤት ለመጨበጥ ከጀመሩ ውለው አድረዋል፡፡

በዶፒንግ ምክንያት ድሏን ለኢትዮጵያዊቷ ያሳለፈችው ኬንያዊት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ሲሳይ ለማ

የዓለም አቀፉ የፀረ አበረታች ቅመሞች ኤጀንሲን ጨምሮ፣ አገሮች የየራሳቸው የውስጥ ሕግጋትን በማውጣት ችግሩን ለመቆጣጠር ቢጥሩም፣ በሚፈለገው ልክና መጠን ውጤት ሊያስገኝላቸው አለመቻሉ፣ በየጊዜው ሰለባ ከሚሆኑ አትሌቶች መረዳት ይቻላል፡፡

ኢትዮጵያን ጨምሮ አገሮች አትሌቶቻቸው አበረታች ቅመሞችን መጠቀም እንደሌለባቸው፣ ተጠቅመው ከተገኙ በወንጀል ጭምር እንደሚያስጠይቃቸው ቢያስጠነቅቁም፣ መፍትሔ ሊሆን አልቻለም፡፡ ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ባለሙያዎች እንደሚሉት፣ ጠንካራ የፋይናንስ አቅም ያላቸው ዓለም አቀፍ ካምፓኒዎች፣ ድርጅቶችና  አገሮች የምርመራውን ምስጢራዊነት በሚፃረር መልኩ ጣልቃ እየገቡ መሆኑ ትልቅ ችግር ነው፡፡

ለዚህም በማሳያነት የሚያቀርቡት፣ የታላላቅ ካምፓኒዎችንና ድርጅቶችን ምርትና አገልግሎት የሚያስተዋውቁ ታላላቅ አትሌቶች፣ ብዙ ጊዜ ከችግሩ ጋር ተያይዞ ስማቸው ሲጠቀስ ቢደመጥም፣ ዕርምጃው ያን ያህል ሲሆን የማይስተዋለው በጣልቃ ገቦች ይቀለበሳልና፡፡

ኢትዮጵያ ‹‹ንፁህ ውጤት በንፁህ አትሌቶች›› የሚለውን መርህ ተከትላ፣  ችግሩን ማስወገድና መከላከል ይቻል ዘንድ ብሔራዊ ተቋም በባለሥልጣን ደረጃ ማቋቋም መቻሏ ይጠቀሳል፡፡

የኢትዮጵያ ፀረ አበረታች ቅመሞች ባለሥልጣን፣ ችግሩን መከላከልና መቆጣጠር ይቻል ዘንድ አሁን ላይ ጠንካራ መሠረት አለው የሚሉት የባለሥልጣኑ ዋና ዳይሬክተር አቶ መኰንን ይደርሳል ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ በተለይም በአሁኑ ጊዜ በዓለም አቀፉ ቻርተር መሠረት ቅጣት የሚባለው በግለሰብ ደረጃ ካልሆነ እንደ አገር አንዳች የሚያሰጋ ነገር እንደሌለም ያስረዳሉ፡፡      

አሸናፊነቷን የተጠነቀችው ኬንያዊት

ዓለም አቀፉ የስፖርት ግልግል ፍርድ ቤት እ.ኤ.አ. በ2014 በተካሄደው የቦስተን ማራቶን አሸናፊ የነበረችው ኬንያዊቷ ሪታ ጀብቶ ውጤት ያመጣችው አበረታች ቅመም ተጠቅማ ነው በሚል ክብሯን እንድትነጠቅ ውሳኔ ማሳለፉን ይፋ አድርጓል፡፡

ውሳኔውን ተከትሎ በወቅቱ ሁለተኛ በመሆን ውድድሯን ያጠናቀቀችው ኢትዮጵያዊቷ ብዙነሽ ዳባ፣ ከወርቅ ሜዳሊያው በተጨማሪ ለሪታ ጀብቶ የተበረከተው የገንዘብ ሽልማት ይገባታል በሚል ባለቤቷ ወርቁ ባዬ ከሰሞኑ ለቦስተን ማራቶን አዘጋጅ ጥያቄ አቅርቧል፡፡

እንደነዚህ የመሰሉ ችግሮች ከዚህ በፊት ተደጋግመው እንደተከሰቱ፣ ውሳኔውም ከገንዘብ ሽልማቱ ውጪ ያለው ሜዳሊያና ክብሩ ግን ጥፋተኛ የተባለውን አትሌት ተከትሎ ውድድሩን ለሚያጠናቅቀው ተወዳዳሪ ተላልፎ የሚሰጥበት አሠራር መኖሩን ባለሙያዎች ያስረዳሉ፡፡ የሚመለከታቸው የቦስተን ማራቶን አዘጋጆች ያሉት ነገር ባይኖርም፣ የብዙነሽ ዳባ ባለቤት አቶ ወርቁ ባዬ ግን ይህን ጉዳይ አዘጋጆቹ ተመልክተው ለባለቤቱ ብዙነሽ ደባ እስከ 100 ሺሕ ዶላር የገንዘብ ሽልማት ሊሰጧት እንደሚገባ ተናግሯል፡፡

የዘንድሮው የቦስተን እና የሮተርዳም ማራቶን

በሌላ በኩል ዘንድሮ ሲጠበቅ የነበረው የቦስተን ማራቶን  ሚያዝያ 7 ቀን 2016 ዓ.ም. ለ128ኛ ጊዜ ሲከናወን፣ በወንዶች ኢትዮጵያ፣ በሴቶች ደግሞ ኬንያውያን በበላይነት አጠናቀዋል፡፡ ከአራት ወራት በፊት በስፔን ቫሌንሽያ በተካሄደው ማራቶን ርቀቱን 2፡01.48 የቦታውን ፈጣን ሰዓት በማስመዝገብ ያሸነፈው ሲሳይ ለማ፣ ሰኞ በተካሄደው የቦስተን ማራቶንን 2፡06.17 በሆነ ጊዜ አጠናቆ ነው አሸናፊ መሆኑን ያረጋገጠው፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ በመሆን ውድድሩን ያጠናቀቁት ደግሞ ኬንያውያን ናቸው፡፡

በሴቶች መካከል በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር ከአንደኛ እስከ ሦስተኛ ያለው ደረጃ በመያዝ ያጠናቀቁት ኬንያውያን ሲሆኑ፣ ያሸነፈችው በዓለም አትሌቲክስ ሻምፒዮናና በኦሊምፒክ በተለይም በአምስት ሺሕ ሜትር በድንቅ የአጨራረስ ብቃቷ የምትታወቀው ሔለን ኦብሪ ናት፡፡

በተመሳሳይ ሚያዝያ 6 ቀን በተደረገው የሮተርዳም ማራቶን ውድድር ኔዘርላንዳዊው አብዲ ናግዬ ርቀቱን 2፡04.41 በማጠናቀቅ አሸናፊ ሲሆን፣ ኢትዮጵያውያኑ ዓምደወርቅ ዋለልኝና ብርሃኑ ለገሠ በ2፡04.50 እና በ2፡05.16 በሆነ ጊዜ ሁለተኛና ሦስተኛ ሆነው አጠናቀዋል፡፡ በሴቶች መካከል በተደረገው ተመሳሳይ ውድድር አሸቴ በከሪ 2፡19.30 በመግባት አሸናፊ ሆናለች፡፡ ሁለተኛና ሦስተኛ ኬንያውያን መሆናቸው የዎርልድ አትሌቲክስ ድረ ገጽ ዘግቧል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...