Wednesday, May 29, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ጦቢያን በታሪክ- ስለ አፄ ቴዎድሮስ

ትኩስ ፅሁፎች

«የካሳ ጀግንነት በ1845 ዓ.ም. ሀገር ያረጋገጠው ሀቅ እየሆነ ሲመጣ ሣልሳዊ አፄ ዮሐንስን ከሥልጣን ለማስወገድ ፍላጎት እንዳለው በዘራፍ ግጥም ሐሳቡን አሳወቀ። መሳፍንቱ ወዲያውኑ መልስ ሰጡ፡ እቴጌ መነን
«ይሄ ቅዋርኛ፤
የፍየል እረኛ።»
ሲሉ ገጠሙ።
በደጃዝማች ወንድይራድ ግቢ የነበረ አንድ አዝማሪ ደግሞ እንዲህ ሲል ገጠመ፡
«ሽህ ብረት ከህዋላው ሽህ ብረት ከፊቱ
ሽህ ነፍጥ ከህዋላው ሽህ ነፍጥ ከፊቱ
ይሄን ሳታይ ሞተች ኮሶ ሻጭ እናቱ
በሸዋ በትግሬ የተቀመጣችሁ
በጎጃም በላስታ የተቀመጣችሁ
አንድ ዛላ በርበሬ መንቀል አቅትዋችሁ
ቆጥቁጦ አንገብግቦ ለብልቦ ይፍጃችሁ።»
እናት፣ ልጅ፣ እና የቤተመንግሥት ባለሟሎች በሙሉ ካሳን በአይሻል ጦርነት ገጠሙት። ድል አደረጋቸው፤ አጼ ዮሐንስም ውጤቱን ተቀብለው ጀግንነቱን አመኑ። በየፉከራቸው የሰደቡትን በሙሉ ታድያ ካሳ ተራ በተራ ቀጣቸው። እቴጌ መነንን እህል እንዲፈጩ፣ ደጃች ወንድይራድን ብዙ ኮሶ እንዲጠጣ ቀጣቸው። የሰደበውንም አዝማሪ አስጠርቶ ምንድን ነው ያልከኝ ብሎ ጠየቀው፡
«አፍ ወዳጁን ያማል የሚሰራው ሲያጣ
ሽመል ይገባዋል ያዝማሪ ቀልብ አጣ» ሲል መለሰ።
የካሳ ጭካኔ በዚህ ጊዜ ታወቀ። አዝማሪው ተስፋ ያደረገው ቀድሞ ስለሚተዋወቁ ይቅርታ የሚደረግለት መስሎት ነበር ነገር ግን እራሱ እንደገጠመው በሽመል ተደብድቦ እንዲሞት ተፈረደበት።
አንዲት ሴት አዝማሪ ግን ይቅር ተብላ ወደሀገሯ እንድትሄድ ተፈቅዶላታል። እንዲህ ስላለች፡
«እርሱ አይሰማም ብየ እንደት በጉድ ወጣሁ
መንጠልጠያ ባገኝ እሰማይ በወጣሁ
መውረጃ ባገኝም እምድር በገባሁ።»
– ፀሐይ ብርሃነሥላሴ፡ ‹‹ኢትዮጵያዊ ጦረኝነት››
****

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች