Tuesday, May 28, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[የኢኮኖሚ ጉዳዮች አማካሪው ቅሬታ የቀረበባቸው አንዳንድ ጉዳዮችን ክቡር ሚኒስትሩ ተመልክተው ምላሽና ውሳኔ እንዲሰጡባቸው ለማድረግ ከክቡር ሚኒስትሩ ጋር እየተወያዩ ነው] 

 • ክቡር ሚኒስትር ተቋማችን በሚሰጣቸው አንዳንድ አገልግሎቶች ላይ ጥያቄ እየተነሳ በመሆኑ ነው ዛሬ ከእርስዎ ጋር ለመወያየት የፈለግኩት።
 • የምን ጥያቄ? ማነው ጥያቄውን ያቀረበው?
 • ጥያቄውን ያቀረቡት የተቋማችን ተገልጋዮች ናቸው።
 • እሺ፣ ጥያቄያቸው ምንድነው?
 • በእርግጥ ጥያቄ ብቻ አይደለም።
 • እ…?
 • ቅሬታ ነው፣ ቅሬታቸው እንዲፈታ ነው የሚጠይቁት።
 • ምንድነው ቅሬታቸው?
 • የተወሰኑት ቅሬታ አቅራቢዎች ለኮንስትራክሽን አገልግሎት የሚውሉ ከባድ ተሽከርካሪዎችን ገዝተው ጂቡቲ ወደብ ቢደርሱም ማስገባት አትችሉም ተባልን ነው የሚሉት፡፡
 • ሌሎቹ ቅሬታ አቅራቢዎችስ?
 • ሌሎቹም ተመሳሳይ ቅሬታ ነው ያቀረቡት፡፡
 • ተመሳሳይ ማለት?
 • ለእርሻ አገልግሎት የሚውሉ ትራክተሮች ገዝተው ጂቡቲ ወደብ ከደረሱ በኋላ ወደ አገር ውስጥ ለማስገባት መከልከላቸውን ነው ቅሬታ ያቀረቡት።
 • እንዲህማ ሊሆን አይችልም፡፡
 • ግን ክቡር ሚኒስትር በርካታ ተገልጋዮች ናቸው ቅሬታውን እያቀረቡ ያሉት።
 • እንዴት ሊሆን ይችላል?
 • እኔም ይህንን ለማወቅ ነው ወደ እርስዎ ዘንድ የመጣሁት።
 • ቆይ በእኛ በኩል የተላለፈ ክልከላ አለ እንዴ?
 • እረ በፍፁም።
 • ታዲያ እንዴት ሊሆን ይችላል?
 • እኔም ግራ ገብቶኛል ክቡር ሚኒስትር።
 • እንዲህማ ሊሆን አይችልም፣ በምን ምክንያት እንደተከለከሉ የገለጹት ነገር የለም?
 • እነ ማን?
 • ቅሬታ አቅራቢዎቹ፡፡
 • ከእነሱማ የሰማነው ነገር አለ፡፡
 • በምን ምክንያት ነው አሉ?
 • በነዳጅ ኃይል የሚሠራ ተሽከርካሪ ወደ አገር ማስገባት ተከልክሏል የሚል ምላሽና ምክንያት እንደተሰጣቸው ነው የገለጹልን።
 • አዎ… ትክክል ነው።
 • ምኑ ነው ትክክል?
 • እኔ ዘንግቼው እንጂ ነዳጅ የሚጠቀም ተሽከርካሪ እንዳይገባ ተከልክሏል።
 • እኛ ግን እንደዚያ የሚል መመርያ አላወጣንም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • በእኛ ተቋም እንዳልወጣማ አውቃለሁ።
 • በዚህ ጉዳይ ላይ ደግሞ የመወሰን ሥልጣን በሕግ የተሰጠው ለእኛ ተቋም ብቻ ነው።
 • እንዴት?
 • ያገለገሉ ተሽከርካሪዎች ወደ አገር ውስጥ እንዳይገቡ ማስቀረት የተቻለው እኛ ባወጣነው የኤክሳይስ ታክስ አዋጅ ነው።
 • አዎ፣ ትክክል ነው።
 • ዝቅተኛ ታክስ በመጣላችን ደግሞ አሁን የምናያቸውን አዳዲስ መኪኖችና በኤሌክትሪክ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዲበራከቱ አድርገናል።
 • ልክ ነህ።
 • ይህንን ሁሉ ያደረገነውም የአየር ብክለትን ለመከላከል ብቻ ሳይሆን ለነዳጅ የምናወጣውን ወጪም ለመቀነስ በማሰብ ነው።
 • ይህንንም፣ ልክ ነህ።
 • ታዲያ አሁን እኛ ሳናውቅ የወሰነው ማነው?
 • ምን የወሰነው?
 • በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ ብሎ የወሰነው።
 • ከላይ የመጣ ነው።
 • ከላይ ማለት?
 • ያው ከላይ ነዋ፣ መቼም ከእግዚአብሔር አልልህ።
 • ገባኝ፣ ምንድነው ከላይ የመጣው?
 • አቅጣጫ፡፡
 • በነዳጅ የሚሠሩ ተሽከርካሪዎች እንዳይገቡ የሚል?
 • አዎ፡፡
 • ግን ክቡር ሚኒስትር…
 • እ…?
 • ከላይም ቢሆን የሕግ አግባብን ተከትሎ መምጣት የለበትም ይላሉ?
 • የሕግ አግባብን ተከትሎ ስትል?
 • አቅጣጫ ምንድነው ማለቴ ነው።
 • እንዴት አንተ?
 • ክቡር ሚኒስትር አቅጣጫ ሕግ አይደለም ማለቴ እኮ ነው።
 • ስለዚህ?
 • ስለዚህ መከልከል ካለበትም ይህንን የሚደነግግ ሕግ ወይም መመርያ መውጣት አለበት ማለቴ ነው።
 • መሆን የነበረበትማ እንደዚያ ነው፣ ግን…?
 • ግን ምን ክቡር ሚኒስትር?
 • እሱን ማን ደፍሮ ይበል?
 • እርስዎ አይጠይቁም እንዴ ክቡር ሚኒስትር?
 • አሁን እየተፈታተንከኝ ነው? ችግርህ ከእኔ ጋር ነው ማለት ነው?
 • መዳፈሬ አይደለም ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ካልሆነ ለምን ትጠይቀኛለህ?
 • ታዲያ ለቀረበልን አቤቱታ ምን ዓይነት ምላሽ እንስጥ?
 • ከላይ የመጣ አቅጣጫ እንደሆነ ንገራቸው።
 • እሱ መፍትሔ አይሆንማ ክቡር ሚኒስትር?
 • እንዴት?
 • ትራክተር እንዳይገባ ከልክለን እንዴት ግብርናን ማሳደግ እንችላለን?
 • እኛ አልከለከልንም፣ ከላይ የመጣ አቅጣጫ ነው በላቸው አልኩህ እኮ?
 • ገባኝ ክቡር ሚኒስትር፣ ግን አርሶ አደሮች በተለይም ሰፋፊ እርሻ ያላቸው ጥያቄ ማቅረባቸው አይቀርም ብዬ ነው።
 • ምንድነው የሚጠይቁት?
 • መሬታችንን በምን እንረስ ብለው?
 • ግድ የለም መልስ እንሰጣቸዋለን።
 • ምን ብለን?
 • ከላይ በወረደው አቅጣጫ መሠረት እረሱ ብለን፣
 • ከላይ የመጣው አቅጣጫ በምን ይረሱ ነው የሚለው?
 • በኤሌክትሪክ ትራክተር!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰማ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እንዲሳተፉ ከተለዩ ባለሀብቶች መካከል እንዱ ጋ ስልክ ደውለው በንቅናቄው ላይ እንዲሳተፉ ግብዣቸውን እያቀረቡ ነው]

መቼም ኢትዮጵያ ታምርት በሚል የተጀመረውን አገር አቀፍ ንቅናቄ ሳትሰማ አትቀርም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ልክ ነው፣ ሰምቻለሁ ክቡር ሚኒስትር። አሁን ደግሞ ንቅናቄውን ለማጠናከር ኢትዮጵያ ታምርት የሚል የታላቁ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...