Wednesday, June 19, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዝንቅስብሐት ገብረእግዚአብሔር ስለ ደራስያን ምን ይላል?

ስብሐት ገብረእግዚአብሔር ስለ ደራስያን ምን ይላል?

ቀን:

ማስተርፒስ ወደ አማርኛ ሥነ ጽሑፍ እየመጣች ነው

 • የዘነበ ወላን “ልጅነት” ካነበበ በኋላ

ዶስቶቭስኪ ሲጽፍ ዝርክርክ ነበር። በቴክኒክ ረገድ ያልተዝረከረከው ‘ወንጀልና ቅጣት’ ብቻ ነበር። ታድያ ማንበቡ ሲጥምህ እንኳንም ተዝረከረከ ነው የምትለው።

 • ስለ ዶስቶቭስኪ

ካፒታልን ያነበብኩት በደርግ ዘመን መፅሀፉን ወደ አማርኛ እንዲመልስ በተዋቀረው ኮሚቴ አባል ሆኜ ነው። ሰዎች ማርክስ ቤተሰቡን አስርቦ ነው የፃፈው ይላሉ። ፍልስፍናው ሲገባህ አውራጃም በተራበ ነው የምትለው።

- Advertisement -

– ስለ ካርል ማርክስ

አደፍርስን ሳነበው “ሌቱም አይነጋልኝ”ን በእንግሊዝኛ የተተየበ 65 ገጽ ላይ ደርሼ ነበር። ከዛ በፊት አማርኛ ለሥነ ጽሑፍ ብቁ አይደለም የሚል እምነት ነበረኝ። ዳኛቸው በአማርኛ መፃፍ እንደሚቻል ከሰተልኝ።

 • ስለ ዳኛቸው ወርቁ

ፍሩይድ ተአምረኛ ነበር። ወደ ራሱ ውስጥ ገብቶ የመረመረ ጂኒየስ ነው። ራሱ በርቶለት የኔንም ውስጤን አበራልኝ።

 • ስለ ፍሩይድ

በዓሉ ጎበዝ አለቃ ነው። ከዛ ቀጥሎ ነው ደራሲነቱን የማደንቀው። በዓሉ ባህሪውም መልኩም የሥነጽሑፍ ችሎታውም ያማረ ሰው ነበር። ‘አይገኝም እንጂ እንዳማሩ መሞት’ የሚለውን የአንዳንድ ጊዘ ሕግ ጥሶታል።

 • ስለ በአሉ ግርማ

ጸጋዬ የኛ ዎሌ ሾይንካ ነው። ኦክስፎርድ ድረስ ሄዶ ሥነጽሑፋችንን ዓለማቀፋዊ ያደረገ ደራሲ ነው።

– ስለ ጸጋዬ ገብረ መድኅን

ዲክንስ የታችኛውን ማኅበረሰብ ሕይወት ነው የጻፈው። እንደ ሩስያ ሥነ ጽሑፍ እንባ በእንባ ነው የሚያደርግህ። የእንግሊዝ ነገሥታትና ልዑላን ዲክንሰን አነበቡት። ከዛ በኋላ ነው ድሆችን የሚረዳ ድርጅት በእንግሊዝ መቋቋም የጀመረው። ዲክንስ በሥነጽሑፉ ጉልበት በሃገር ደረጃ ማኅበራዊ ተፅዕኖ መፍጠር የቻለ ታላቅ ደራሲ ነው።

 • ስለ ቻርልስ ዲክንስ

ኃይለመለኮት መዋዕል ‘ጉንጉን’ ውስጥ አማርኛን ከነለዛዋ ከነማዕረጓ ጽፎ አስደነቀኝ። ደግሞም ኃይለመለኮት ብዕሩ ብቻ ሳይሆን አንደበቱም ርቱዕ ነው።

 • ስለ ኃይለመለኮት መዋዕል

ፕሩስት አይሁድ ነው። የፈረንሳይ አይሁድ። ጂንየስ ነው። አይሁድ መሆን ጂኒየስ ያደርጋል መሰለኝ። ሰባት ልብወለድ ጽፏል። ስለ ራሱ ነው የጻፈው። በልብወለዱ ውስጥ ያሉት ሁለት መቶውም ገጸ ባህሪያት ፈረንሳይ ውስጥ በሕይወት ያሉ ሰዎች ናቸው። በፈረንሳይኛ ነው ያነበብኩት። ፈረንሳይኛን እንደሱ የሚያውቅበት ደራሲ የለም።

 • ስለ ማርሴል ፕሩስት

ጋሽ ሐዲስ ዓለማየሁ ቆንጆ ስታይል ነው ያላቸው። ተረታዊ አቀራረባቸውን እወደዋለሁ። በአማርኛ የሚጽፉ ቶልስቶይ ልትላቸው ትችላለህ።

– ስለ ሐዲስ ዓለማየሁ

ኒቼ ከዘመናዊ ታላላቅ ፈላስፎች አንዱ ነው። ግማሽ ጎኑ ፖላንድ ነው። በጣም ብሪሊያንት ነበር። ከኤግዚስቴንሽያሊዝም አያቶች አንዱ ነው። ፍልስፍናው በጣም ተፅዕኖ ፈጣሪ ነው አሁን ድረስ። ኒቼ የቂጥኝ በሽታ ነበረበት። በዚሁ ጦስ አብዶ ነው የሞተው።

 • ስለ ፍሬድሪክ ኒቼ

ከበደ ሚካኤል በዘመናቸው ለነበረ ትውልድ ትክክለኛ ደራሲ ናቸው። ለአሁኑ ትውልድ ግን እንጃ። ምክንያቱም ሥራቸው ግብረገብ ይበዛበታል። ቢሆንም መደነቅ ይገባቸዋል።

 • ስለ ከበደ ሚካኤል

አልቤር ካሙ ጋዜጠኛም ፈላስፋም ደራሲም ነበር። ደግሞም ሰው ነው። ላመነበት ነው የሚኖረው። በእኛ ዘመን ካሙን እና ሳርትርን ያላነበበ ኢንተሌክችዋል ወጣት አልነበረም። ሥራቸው ፍልስፍናም ምርምርም ነበር።

 • ስለ አልቤር ካሙ
 • ቴዎድሮስ ሸዋንግዛው በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደከተበው
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የምግብ ዋጋ ንረት አጣዳፊ ዕርምጃ ያስፈልገዋል!

መንግሥት የሚቀጥለውን ዓመት በጀት ይዞ ሲቀርብ በአንገብጋቢነት ከሚነሱ ጉዳዮች...

ከባለአንድ ዋልታ ወደ ባለብዙ ዋልታ የዓለም ሥርዓት የመሸጋገራችን እውነታ

በአብዱ ሻሎ አንገት ማስገቢያ እ.ኤ.አ. በፌብሩዋሪ 2022 የሩሲያ መንግሥት በዩክሬን ‹‹ልዩ...

የኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የውጭ ግንኙነት የሺሕ ዘመናት ታሪኳና እሴቶቿን የሚመጥን መሆን ይኖርበታል

(ክፍል አንድ) በተረፈ ወርቁ (ዲ/ን) እንደ መንደርደሪያ ለዛሬው የግል ትዝብቴንና ታሪክን ላዛነቀው...

ከአገር ግንባታ ጋር የተያያዙ ወሳኝ የቅርብ ታሪካችን አንጓዎች

በታደሰ ሻንቆ በአያሌው የተመረጡና ልጥ የሌላቸው ነጥቦች የተደራጁበት ይህ ታሪክ...