Saturday, June 22, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ዝንቅየመስቀሉ መንገዶች

የመስቀሉ መንገዶች

ቀን:

ኢየሩሳሌም የምድር ማዕከል እንደመሆኗ መጠን ወደ እርሷ የመጣ ሁሉ የተለያየ ስም ሰጥቷታል፡፡ ከመንገዶቿ አብዛኛው ሕዝብ የሚያውቀውን ‹‹ቪያ ዶሎሮዛ››ን መጥቀሱ ብቻ ይበቃል፡፡ የዚህ ቃል መሠረቱ ላቲን ሆኖ ‹‹ቪያ›› መንገድ ‹‹ዶሎሮዛ›› የመከራ፣ የስቃይ፣ የሕመም፣ የጻዕር፣ የጋዕር፣ የጭንቅ መንገድ እንደማለት ሲሆን፣ ወደ ግእዙ ሲለወጥ ደግሞ ደግሞ እግረ መስቀል፣ ፍኖተ መስቀል፣ ሕማማተ መስቀል ማለት ነው፡፡

እግዚእ ኢየሱስ ክርስቶስ በእግረ መስቀሉ ጉዞ በመንገዱ ላይ 14 ድርጊቶች ስለተፈጸሙበት 14ቱ የመስቀል መንገዶች በመባል ይታወቃሉ፡፡ ከእነርሱም ጋር ተያይዘው በጌታ ላይ የደረሱት ስቃዮችና እንግልቶች 14ቱ ሕማማተ መስቀል ይባላሉ፡፡

የቪያ ዶሎሮዛ መንገድ የሚጀምረው በምሥራቅ ኢየሩሳሌም ከጌቴሴማኒ ፊት ለፊት የበጎች፣ የአንበሶች የማርያም፣ ወይም የእስጢፋኖስ በር ተብሎ በሚጠራው በኩል ነው፡፡ የሊቀ ካህናቱ ወታደሮች ጌታን ይዘውት በሄዱበት መንገድ በቀኝ በኩል የእመቤታችን የትውልድ ቦታ የቅዱስ ሐና ቤተ ክርስቲያንና ጌታችን የ38 ዓመት በሽተኛውን የፈወሰበት የቤተ ሳይዳ መጠመቂያ ይገኛሉ፡፡

እግረ መስቀል ጉዞ መቼ? እንዴት እንደተጀመረ መናገር አይቻልም፡፡ ሆኖም የክርስትና ሃይማኖት የመንግሥት ሃይማኖት መሆን በጀመረበት በንጉሥ ቆስጠንጢኖስና በንግሥት እሌኒ ጊዜ ሳይሆን አይቀርም ተብሎ ይገመታል፡፡ ከዚያን ጊዜ ጀምሮ እንደተጀመረ፣ እየተቋረጠ ከዘመናችን ደርሷል፡፡ በአሁኑ ጊዜ በየሳምንቱ ዓርብ በ9 (15) ሰዓት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን መነኮሳት በፍራንሲስካውያን መሪነት ከዚህ ቦታ ተነስቶ መስቀሉን በመሸከም በቪያ ዶሎሮዛ መንገድ እስከ ጎልጎታ ድረስ የእግር ጉዞ ይደረጋል፡፡ በየቦታውም ከወንጌላውያኑ ቦታውን የሚመለከተው ክፍል ይነበባል፡፡ ይተረጐማል፣ ይብበራራል፣ ይዘመራል፣ ጸሎትም ይደረጋል፡፡

በየዓመቱ የስቅለት ዓርብ የቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም ተሳላሚዎች ኢትዮጵያውያንና የዓለም ክርስቲያኖች የእግረ መስቀል ጉዞውን የሚጀምሩት በካቶሊክ ቤተ ክርስቲያን ሥር ባለው ምድር ቤት ነው፡፡ ገበታ፣ ጸፍጸት፣ ሊቶስጥራ ተብሎ የሚጠራው አስደናቂው ንጥፍ ድንጋይ እስካሁን አለ፡፡ ጉዞው ከመንግሥት በተፈቀደ ሰዓት ቢሆንም ረፈድ ካለ ምንም መፈናፈኛ ቦታ አይገኝም፡፡ መራመድ የሚቻለው አንዱ የአንዱን እግር እየረገጠ ነው፡፡ ለኢትዮጵያ ተሳላሚዎች የተመደበው ሰዓት ከሁሉ በፊት ቢሆም ኢትዮጵያውያን ተሳላሚዎች ከዓመት ወደ ዓመት ቁጥራቸው እየጨመረ በመሄዱ ያለው ግፊ በቀላሉ የሚገመት አይደለም፡፡ አልፎ አልፎም የመሰበር አደጋ የሚደርስበት ጊዜ አለ፡፡ ከዚህም የተነሳ አባቶች እንዳስጠነቀቁ ነው፡፡ አሁን ደግሞ ወደ ሦስተኛው ጣቢያ እናመራለን፡፡ ጉዞው ምንጊዜም ለበረከት ያህል የእንጨት መስቀሉን በመሸከም ነው፡፡

ከስምንተኛው ምዕራፍ ተነስቶ ወደ ዘጠነኛው ምዕራፍ የእግረ መስቀል ጉዞ ለማድረግ እንደገና ሱቆች ወደአሉበት ቦታ ወደ ደቡብ አቅጣጫ መመለስ ያስፈልጋል፡፡ ከዚያም ወደ ቀኝ ታጥፎ በመግባት ደረጃውን እንደ ወጡና ጥቂት እንደተራመዱ በግብፅና በኢትዮጵያ አብያተ ክርስቲያናት አጠገብ በስተግራ በኩል አንድ የድንጋይ ተክል/ምሰሶ ይገኛል፡፡ የዘጠነኛው ምዕራፍ ምልክት ነው፡፡

በኢትዮጵያ ኦርቶዶክስ ተዋሕዶ ቤተ ክርስቲያን የዴር ሡልጣን ገዳም ከትንሣኤው ቤተ ክርስቲያን ጋር የተያያዘ ነው፡፡

ይህ የትንሣኤ ቤተ ክርስቲያን ‹‹የቤተ ክርስቲያን ሁሉ እናት›› ተብሎ ይጠራል፡፡ ስለምን ቢባል የመጀመሪያው ቤተ ክርስቲያን ይህ ብቸቻ ነውና፡፡ የእኛም የዴር ሡልጣን ቤተ ክርስቲያን አብሮ የተሠራ ስለሆነ እናት ቤተ ክርስቲያን የሚለው ይመለከተዋል፡፡ በእኛ ቤተ ክርስቲያን የስም አሠራር ዘይቤ የትንሣኤ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ስም አዲስ ስልሆነ ግር ማለቱ አይቀርም፡፡ የትንሣኤ ቤተ ክርስቲያን ከሚለው ስም ይልቅ የቀራንዮ ወይም የጎልጎታ ቤተ ክርስቲያን የሚለው ጎልቶ ይታወቃል፡፡ የኦርቶዶክስ እምነት ተከታዮች የሆኑ ምሥራቃውያን ክርስቲያኖች ‹‹የትንሣኤ ቤተ ክርስቲያን›› ብለው ሲጠሩት፣ የካቶሊክና የፕሮቴስታንት እምነት ተከታዮች ምዕራባውያን ክርስቲያኖች ደግሞ ‹‹የቅዱስ መቃብር ቤተ ክርስቲያን›› ብለው ይጠሩታል፡፡

  • ሊቀ ካህናት መርዓዊ ተበጀ (ዶ/ር) ‹‹ቅድስት ሀገር ኢየሩሳሌም›› (2015)
spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...