Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናሰነድ አልባ ተከፋይና ተሰብሳቢ ሒሳቦች እንዲሰረዙለት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረበ

ሰነድ አልባ ተከፋይና ተሰብሳቢ ሒሳቦች እንዲሰረዙለት የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር ጥያቄ አቀረበ

ቀን:

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር በ2012 ዓ.ም. የበጀት ግኝት የሚመረምር ኮሚቴ በማቋቋምና ሒሳቡን በማጥራት፣ ሰነድ አልባ የሆኑ ተከፋይና ተሰብሳቢ ሒሳቦች ከመዝገብ እንዲሰረዙለት፣ ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረቡን አስታወቀ፡፡

ሚኒስቴሩ ይህንን ያስታወቀው የሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ትናንት ማክሰኞ ሚያዝያ 29 ቀን 2016 ዓ.ም. ባካሄደው 25ኛ መደበኛ ስብሰባ የዘጠኝ ወራት የዕቅድ አፈጻጸሙን ሪፖርት ሲገመግም ነው፡፡

የኢኖቬሽንና ቴክኖሎጂ ሚኒስትሩ በለጠ ሞላ (ዶ/ር) ሪፖርቱን ባቀረቡበት ወቅት፣ ሚኒስቴሩ ከመደበኛ በጀት 81 በመቶ፣ እንዲሁም ከካፒታል በጀት 58 በመቶ ጥቅም ላይ ማዋሉን ገልጸው፣ በ2012 እና በ2013 በጀት ዓመት የቀድሞው የመገናኛና ኢንፎርሜሽን ቴክኖሎጂ ሚኒስቴር መከፈልና መሰብሰብ የነበረበት ሒሳብ ያለ ቢሆንም፣ ማስረጃ የሌለው ተከፋይና ተሰብሳቢ ሒሳብ በመሆኑ ምክንያት አስተያየት መስጠት አልተቻለም ብለዋል፡፡

- Advertisement -

አክለውም የ2012 ዓ.ም. የበጀት ግኝት ኮሚቴ በማቋቋም ሒሳባቸውን በማጥራት ሰነድ አልባ የሆኑ ተከፋይና ተሰብሳቢ ሒሳብ ከመዝገብ እንዲሰረዝ ለገንዘብ ሚኒስቴር ጥያቄ ማቅረባቸውን፣ ሒሳቡ ባለመሰረዙም በሚኒስቴሩ የበጀት አጠቃቀም ላይ ከምክር ቤቱ ጥያቄ እንዲነሳበት ሲያደርግ መቆየቱን ገልጸዋል፡፡ ሚኒስቴሩ በበኩሉ ሒሳቡን ለማጣራት ባደረገው ሒደት 237 ሚሊዮን ብር እንዲወራረድ ተደርጓል ብለዋል፡፡

በሌላ በኩል የኒውክሌር ሳይንስ ቴክኖሎጂ ምርምር ማዕከል ለመገንባት የሩሲያው ሮሳቶም ኩባንያ የአዋጭነት ጥናት እንዲያከናውን ድርድሮች እየተካሄዱ መሆናቸውን በለጠ (ዶ/ር) አስታውቀዋል፡፡ ለማዕከሉ ግንባታ የሚውል በጀት መፈቀዱንና በዘርፉ የሠለጠነ የሰው ሀብት ስለሚያስፈልግ፣ ሠራተኞችን ወደ ተለያዩ አገሮች በመላክ እንዲሠለጥኑ እየተደረገ መሆኑንም ገልጸዋል፡፡

በዘጠኝ ወራት ውስጥ ከተከናወኑ ተግባራት መካከል ሌላኛው፣ ከቻይና መንግሥት የተፈጥሮ ሀብት ሚኒስቴር፣ የኢትዮጵያን የቆዳ ስፋት በሙሉ የሚሸፍን የሳተላይት መረጃ የተገኘው ድጋፍ ነው፡፡ ‹‹ይህ የሳተላይት መረጃ አሁን ባለው የገበያ ዋጋ ሲሰላ እስከ 2.9 ሚሊዮን ዶላር ወጪ ያዳነ ወይም ያስገኘ ነው፤›› ብለዋል፡፡ 

በተጨማሪም እ.ኤ.አ. በ2020 ከቻይና መንግሥት ጋር በተፈጸመ ስምምነት ተጀምሮ የነበረው 12 ዲያሜትር ያለው የመሬት ምልከታ ሳተላይት መረጃ መቀበያ ጣቢያ ግንባታ በእንጦጦ ኮንስትራክሽን ሲካሄድ መቆየቱን፣ በዘጠኝ ወራት ውስጥ ለመሥራት የታቀደው ተጠናቆ በተያዘው በጀት ዓመት ግንባታው አልቆ አገልግሎት መስጠት መጀመሩን ገልጸዋል፡፡

ወደ ህዋ የተላኩ ሁለት ሳተላይቶችን አስመልክቶ ያስገኙት ጥቅም ላይ ማብራሪያ እንዲሰጥ ከሰው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ጥያቄ የቀረበላቸው በለጠ (ዶ/ር)፣ ሁለቱም ሳተላይቶች አገልግሎታቸውን መጨረሳቸውንና በሳተላይቶቹ አማካይነት 26.4 ቴራባይት መጠን ያለው የሳተላይት መረጃ ክምችት መፍጠር መቻሉን አብራርተዋል፡፡ ይህን መረጃ ከሁለቱ ሳተላይቶች ማግኘት ባይቻል ለከፍተኛ ወጪ ሊዳርግ የሚችል ነበር ብለዋል፡፡ 

ሚኒስቴሩ ለሚያከናውናቸው ተግባራት አዋጆችና ደንቦች በታቀደው ፍጥነት ልክ አለመፅደቃቸው፣ የከፍተኛ ባለሙያ እጥረት መኖርና ለቴክኖሎጂ ግዥ የውጭ ምንዛሪ እጥረት እንቅፋት እየሆኑብኝ ነው ብሏል፡፡

የሰው ሀብት ልማት ሥራ ሥምሪትና ቴክኖሎጂ ጉዳዮች ቋሚ ኮሚቴ ሰብሳቢ ነገሪ ሌንጮ (ዶ/ር)፣ አስፈላጊውን የሕግ ማዕቀፍ ማዘጋጀት እንደሚገባ፣ ወጣቶችን በዘርፉ በማሰማራት ከቴክኖሎጂ ጥገኝነት መውጣት እንደሚያስፈልግና ለዚህም ሚኒስቴሩ ትኩረት አድርጎ ሊሠራበት እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...