Tuesday, May 28, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

 • በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር?
 • ጥሩ ወዲህ አምጪው… አዎ!
 • በል መርቅ…
 • ከዓመት ዓመት ያድርሰን…
 • ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው?
 • ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ …አልሰማሽም?
 • ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን ዋጋ አለው …በደንብ መርቅ እንጂ?
 • ሌላ ምን ብዬ ልመርቅ?
 • አገራችንን ሠላም ያድርግልን… ካለንበት ጦርነት ያውጣን በል እንጂ?
 • ተይ …ተይ …እሱ ይቅር!
 • እንዴ ለምን?
 • ሠላም ባንድ ወገን ፍላጎት ብቻ አይመጣም!
 • ኧረ ፖለቲካህን ተውና ዳቦውን መርቀህ ቁረስልን?
 • አንቺው እኮ ነሽ አላስቆርስ ያልሽው?
 • እኔ ደግሞ ምን አደረኩ …ከመቀመጫዬ አልተነሳሁ?
 • ካለሽበት ሆነሽ ጣልቃ እየገባሽ አይደለም እንዴ?
 • በል አሁን ጭቅጭቁን ተወውና ዳቦውን ቁረስንልን?
 • መቆረሱ የት ይቀራል ብለሽ ነው… ይኸው…?
 • ኧረ ተው… አታሳንሰው…?
 • አሳነስኩት እንዴ?
 • አደቀከው እንጂ?
 • ለሁሉም እንዲዳረስ ብዬ ነዋ?
 • ኤዲያ… ፈርፍረህ ጨረሰው እኮ።
 • ዛሬ ምን ነክቶሻል…?
 • ኤዲያ …ጨርሶ በቢላ የተቆረሰ አይመስልም እኮ?!
 • እና በምን የተቆረሰ መሰለ?
 • በድሮን!

[የቀረበላቸውን ሪፖርት ተመልክተው የተበሳጩት ክቡር ሚኒስትሩ ስልካቸውን አንስተው በቀጥታ ለክልሉ ርዕሰ መስተዳደር ደወሉ]

 • ሃሎ ክቡር ሚኒስትር፡፡
 • ሃሎ!
 • ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር።
 • ጤና ይንሳህ ብትለኝ አይሻልም?
 • እሱን ለጠላቶቻችን ያድርገው ክቡር ሚኒስትር።
 • አንዱ እኔ ሳልሆን የቀረሁ አልመሰለኝም።
 • አንዱ ምን?
 • አንዱ ጠላት።
 • እንዴ ክቡር ሚኒስትር ምን ተፈጥሮ ነው እንዲህ የሚሉት?
 • የሽግግር ፍትሕ በመጀመር ከምዕራባዊያኑ ጋር ግንኙነታችንን ለማደስ ጥረት እያደረግን መሆኑን አታውቅም?
 • በደንብ ነው እንጂ የማውቀው ክቡር ሚኒስትር።
 • ታዲያ ይህንን እያወቅክ ነው የምታዋክቡት?
 • ማንን?
 • የሰብዓዊ መብት ኮሚሽኑን።
 • ታዲያ ይኼ ለመጀመር ካቀድነው የሽግግግር ፍትሕ ጋር ምን አገናኘው?
 • እንዴት አይገናኝም? የኮሚሽኑን ሥራ እያደናቀፍክ ስለ ሽግግር ፍትሕ ብታወራ ማን ይሰማሃል። እስኪ ንገረኝ ማን ያምንሃል?
 • በዚያ መልኩ አላሰብኩትም ክቡር ሚኒስትር።
 • ዋና ችግር እኮ አርቃችሁ ማሰተዋል አለመቻላችሁ ነው።
 • በነገራችን ላይ ክቡር ሚኒስትር…?
 • እ…?
 • እኛ የኮሚሽኑን ሥራ ለማደናቀፍ ብለን አይደለም ያደረግነው ነገር የለም።
 • የኮሚሽኑን መርማሪዎች በፀጥታ ኃይሎች ማዋከብና ያነጋገሯቸውን ምስክሮች ማሰር ምን ማለት ነው፣ ማደናቀፍ አይደለም?
 • እንደዚያ ያደረግነው ለራሳቸው ሰንል ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • ለራሳቸው ማለት?
 • ኮሚሽኑ ለላካቸው መርማሪዎች ማለቴ ነው።
 • እነሱ ምን እንዳይሆኑ?
 • አደጋ እንዳይደርስባቸው።
 • እሺ አሁን የምታወራውን አቁምና የፈጠርከውን ስህተት እንዴት እንደምታርመው ንገረኝ።
 • ችግር የለም፣ ይታረማል ክቡር ሚኒስትር።
 • እኮ እንዴት እንደምታርመው ንገረኝ።
 • አንደኛው አማራጭ ኮሚሽኑ የእኛን ሪፖርት እንዲጠቀምበት ማድረግ ነው።
 • የቱን ሪፖርት?
 • የተቃዋሚ ፓርቲ አመራሩን ግድያ በተመለከተ ያደረግነውን የምርመራ ሪፖርት።
 • እናንተ ያደረጋችሁትን ምርመራ ኮሚሽኑ እንዲጠቀምበት?
 • አዎ ክቡር ሚኒስትር።
 • ይኼ እንዴት መፍትሔ ይሆናል። ኮሚሽኑ እንዴት የእናንተን የምርመራ ውጤት ይቀበላል?
 • የእኛን ምርመራ ሪፖርት ካልተቀበለ ደግሞ ሌላ አማራጭ እናቀርባለን።
 • ሌላው አማራጭ ምንድነው?
 • የተቃዋሚ አመራሩ ግድያ አንድ ላይ እንደሚታይ እንነግራቸዋለን።
 • አንድ ላይ ይታያል?
 • አዎ…
 • በምን?
 • በሽግግር ፍትሕ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

የፋይናንስ ኢንዱስትሪው ለውጭ ባንኮች መከፈት አገር በቀል ባንኮችን ለምን አስፈራቸው?

የማይረጥቡ ዓሳዎች የፋይናንስ ተቋማት መሪዎች ሙግት ሲሞገት! - በአመሐ...

የምርጫ 97 ትውስታ!

በበቀለ ሹሜ      መሰናዶ ኢሕአዴግ ተሰነጣጥቆ ከመወገድ ከተረፈ በኋላ፣ አገዛዙን ከማሻሻልና...

ሸማቾች የሚሰቃዩት በዋጋ ንረት ብቻ አይደለም!

የሸማች ችግር ብዙ ነው፡፡ ሸማቾች የሚፈተኑት ባልተገባ የዋጋ ጭማሪ...

መንግሥት ከለጋሽ አካላት ሀብት ለማግኘት የጀመረውን ድርድር አጠናክሮ እንዲቀጥል ፓርላማው አሳሰበ

የሦስት ዩኒቨርሲቲዎች ፕሬዚዳንቶች በኦዲት ግኝት ከኃላፊነታቸው መነሳታቸው ተገልጿል አዲስ አበባ...

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ስለሺ በቀለ ያቀረቡት መልቀቂያ ተቀባይነት ማግኘቱ ተሰማ

በአሜሪካ የኢትዮጵያ አምባሳደር ሆነው እያገለገሉ የሚገኙት የቀድሞው የውኃ ሀብት...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እንዲሳተፉ ከተለዩ ባለሀብቶች መካከል እንዱ ጋ ስልክ ደውለው በንቅናቄው ላይ እንዲሳተፉ ግብዣቸውን እያቀረቡ ነው]

መቼም ኢትዮጵያ ታምርት በሚል የተጀመረውን አገር አቀፍ ንቅናቄ ሳትሰማ አትቀርም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ። ልክ ነው፣ ሰምቻለሁ ክቡር ሚኒስትር። አሁን ደግሞ ንቅናቄውን ለማጠናከር ኢትዮጵያ ታምርት የሚል የታላቁ...

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡ ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ? ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው። ምኑ ነው ግራ ያጋባህ? የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ። አልገባኝም? አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን...

[ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ይፋ ያደረገውን ንቅናቄ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው በግንባር ቀደምትነት እንዲቀላቀሉ መታዘዙን ለባለቤታቸው እያጫወቱ በዚያውም ወደተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እያግባቧቸው ነው]

በይ እስኪ ሞባይልሽን አውጪና ወደዚህ የባንክ ሒሳብ አንድ ሺሕ ብር አስተላልፊ? ለምን? መንግሥት ያስጀመረውን ንቅናቄ አመራሩ ከነቤተሰቡ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲደግፍ ታዟል። የምን ንቅናቄ ነው መንግሥት ያስጀመረው? ‹‹ፅዱ...