Friday, June 21, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ስፖርትፓሪስን የሚናፍቁት ኢትዮጵያውያን በዶሃ ዳይመንድ ሊግ ያሳዩት ብቃት

ፓሪስን የሚናፍቁት ኢትዮጵያውያን በዶሃ ዳይመንድ ሊግ ያሳዩት ብቃት

ቀን:

የኢትዮጵያ አትሌቲክስ በተለይም በኦሊምፒክ ተሳትፎው በረዥም ርቀትና ማራቶን ካልሆነ እስከ ቶኪዮ ኦሊምፒክ ድረስ ሊጠቀስ የሚችል ጠንካራ ውጤት አልነበረውም፡፡ በቶኪዮ ኦሊምፒክ ወቅት ግን ለሜቻ ግርማ ወደ ሥፍራው ያመራበት መንገድ ምንም እንኳ ሁለቱ ተቋማት በአትሌቱ ብቃት ሙሉ እምነት የነበራቸው አለመሆኑ እንደተጠበቀ፤ አትሌቱ ለአገሩና ለራሱ በ3,000 ሜትር መሰናል ያስመዘገበው የብር ሜዳሊያ ግን ትርጉም ያለው ውጤት ሆኖ ይጠቀሳል፡፡

በመጪው ሐምሌ በሚጀመረው ፓሪስ ኦሊምፒክ ላይ ግን የለሜቻ ግርማ እግር በመከተል በመካከለኛ ርቀት ትልቅ ተስፋን የሰነቁ ወጣቶች መታየት ጀምረዋል፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ የሚሆነው ደግሞ ባለፈው እሑድ በኳታር ዶሃ በተካሄደው ዳይመንድ ሊግ ውድድር ላይ በ3,000 ሜትር መሰናክል ውድድሩን በአሸናፊ ያጠናቀቀው ወጣቱ ፍሬው ሳሙኤል ይጠቀሳል፡፡ አትሌቱ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የፈጀበት ሰዓት 8፡07.25 መሆኑ እንደተጠበቀ በተለይም የኢትዮጵያውያኑ የምጊዜም ተቀናቃኝ ከሆኑት ኬንያውያን የገጠመውን እልህ አስጨራሽ ትግል ተቋቁሞ አሸናፊ መሆን አትሌቱን በፓሪስ ኦሊምፒክ እንዲጠበቅ ያደርገዋል፡፡

በሴቶች መካከል በተደረገው የ1,500 ሜትር ውድድር ፍሬወይኒ ኃይሉ ርቀቱን ለማጠናቀቅ የፈጀባት ሰዓት 4፡00.42 መሆኑ በትልቁ ሲጠቀስ፣ ከዚሁ ጎን ለጎን አትሌቷ በውድድሩ ያሳየችው ብቃት ለፓሪስ ኦሊምፒክ ያላትን ተስፋ በግልጽ ያመላከተ ስለመሆኑ ጭምር ዓለም አቀፍ ሚዲያዎች ሳይቀር ሽፋን የሰጡት ሆኖ ተመዝግቧል፡፡   

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የንብረት ማስመለስ ረቂቅ አዋጅና የሚስተጋቡ ሥጋቶች

ከሰሞኑ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት የቀረበው የንብረት ማስመለስ ረቂቅ...

የመጨረሻ የተባለው የንግድ ምክር ቤቱ ምርጫና የሚኒስቴሩ ውሳኔ

በአገር አቀፍ ደረጃ ደረጃ የንግድ ኅብረተሰቡን በመወከል የሚጠቀሰው የኢትዮጵያ...

ሚስጥሩ!

ጉዞ ከካዛንቺስ ወደ ስድስት ኪሎ፡፡ የጥንቶቹ አራዶች መናኸሪያ ወዘናዋ...