Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹ሰው ሲታመም የምንጠይቀው ከቋጠሮ ሰሐን ጋር ነው››

ትኩስ ፅሁፎች

ሰው ሲታሰር ‹እግዚአብሔር ያውጣህ› የምንለው ከፍትፍት አገልግል ጋር ነው … አራስ የምትጠይቀው ከፔርሙዝ አጥሚት ጋር ነው… የክርስትና አባታችን ለፋሲካ አክፋዩን የሚጠብቀው ድፎ ዳቦና አረቄ ነው… እዝንተኛ የምናስተዛዝነው ሰባት እንጀራ ከአንድ ሰሐን ወጥ ጋር ነው… ሟች የምንሸኘው ከገንቦ ጠላና ከለምለም እንጀራ ጋር ነው… የቅዱሳንና የመልአክታት ተራዳዒነት የሚጎበኘን በስማቸው ከዘከርን ነው።

… ስዕለታችን በሬ ወይም በግ ነው… ሠርጋችን፣ ልደታችን፣ እርቃችን፣ ሹመታችን፣ አምልኳችን፣ የሚበላ ነገርን ሙጥኝ ያሉ ናቸው… ሌላው ቀርቶ አንድ ሰው ተምሮ ሲመረቅ ይዘን የምንሄደለት ስጦታ ብዕር ወይም መጽሐፍ አይደለም ኬክ፣ ብርቱካን፣ ሙዝ… ነው፡፡

በሽተኛ ስትጠይቅ ከብርቱካንና ከሙዝ ይልቅ መጽሐፍ መውሰድ እንደማላገጥ ይቆጠራል፡፡ ጊዜውን ይገፋበት ዘንድ መጽሐፍ ማበርከት በሽተኛው እንዳይድን ከመመኘት እኩል ነው። ለኛ ለኢትዮጵያውያን መጻሕፍት ከባዶ ገበታችን በስተዚያ የተቀመጡ ትርፍ ነገሮች ናቸው፡፡ መጻሕፍት የሚያስፈልጉት ገበታችን ሞልቶ ከገነፈለ በኃላ ነው ብለን በይነናል። ገበታችንም አይሞላ መጻሕፍቱም አይነሱም፡፡ ያልተረዳነው ቢኖር ለገበታ መትረፍረፍ ዙሪያ ጥምጥም ጉዞ መጻሕፍት አቋራጭ መንገድ መሆናቸውን ነው፡፡ እንዴት ታዲያ ማንበብ መብላትን ይቅደም? መቼ ይሆን ከምንኮራባቸው ባህሎቻችን በላይ ማንበብ ባህላችን ሆኖ የምንታወቅበት ናየምንኮራበት?.››.’

  • ዓለማየሁ ገላጋይ
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች