Saturday, May 18, 2024
- Advertisment -
- Advertisment -

[ክቡር ሚኒስትሩ የቢሮ ሥራቸውን አጠናቀው ከውጭ አገር የመጣ ወንድማቸውን ለመጠየቅ ያረፈበት ገስት ሀውስ ሲደርሱ ወንድማቸው በቴሌቪዥን የሚተላለፈውን ፕሮግራም በመገረም እየተከታተለ አገኙት]

 • ውይ መጣህ እንዴ? እስኪ አረፍ በል፡፡
 • ምንድነው እንዲህ ያስደነቀህ?
 • ተደንቄ ሳይሆን ግራ ግብት ብሎኝ ነው።
 • ምኑ ነው ግራ ያጋባህ?
 • የድልድይ ማስመረቅና የድልድይ ማፍረስ ነገር ነዋ።
 • አልገባኝም?
 • አለቃችሁ ድልድይ ሲያስመርቁ የተናገሩትን ሰምቼ ግራ ግብት ብሎኛል።
 • ምንድነው የተናገሩት?
 • ዛሬ ይህንን ድልድይ እንዳስመረቅነው ሁሉ የትርክት ድልድይ መገንባትም ያስፈልገናል አሉ።
 • የምን ድልድይ?
 • ቆይ የተናገሩትን ቃል በቃል ልንገርህ።
 • እሺ…
 • ‹‹በአማራና በኦሮሞ፣ በአማራና በትግራይና በሌሎችም ሕዝቦች መካከል በአልባሌ ትርክቶች ምክንያት እየላላ ያለውን ትስስር ሊያጠናክር የሚችል የትርክት ድልድይ መገንባትም እንፈልጋለን፤›› ነው ያሉት።
 • እና እንደዚያ ማለታቸው ግራ ያጋባል እንዴ?
 • ድልድይ መገንባት እንፈልጋለን ማለታቸውማ ጥሩ ነገር ነው።
 • ታዲያ ድልድይ እያስመረቁ ድልድይ ማፍረስ ያልከው ምኑን ነው?
 • ከቀናት በፊት ወደ ምዕራቡ አካባቢ ሄደው የተናገሩት ትዝ ብሎኝ ነዋ?
 • እዚያ ሄደው የተናገሩትን እንኳ አልሰማሁም፣ ምንድነው ያሉት?
 • ሕዝባችን በገዛ አገሩ ለመቶና ከዚያ በላይ ዓመታት እንደ ሁለተኛ ዜጋ ተቆጥሮ ቆይቷል፣ ዛሬ ግን ነፃ ወጥቷል።
 • ታዲያ ይህን ማለታቸው ምን ችግር አለው?
 • ኢትዮጵያ ውስጥ በመሪዎች የተጨቆነው አንድ ማኅበረሰብ ብቻ ነው እንዴ?
 • እሱስ ልክ ነህ ሁሉም ተጨቁኗል።
 • ዛሬ ደግሞ በአልባሌ ትርክቶች ምክንያት እየላላ ያለውን የሕዝቦች ትስስር ሊያጠናክር የሚችል የትርክት ድልድይ መገንባት አለብን ይላሉ፡፡
 • ይህንን ማለታቸው ትክክል አይዳለም እያልክ ነው?
 • ትክክል አይደለም!
 • ምኑ ነው ትክክል ያልሆነው?
 • ማኅበረሰባችን ቀደም ሲል የጨቆኑትን መሪዎች የብሔር ማንነት እየቆጠረ ዛሬ እርሱ በእርሱ ተካሮ ሳለ እንዲህ ያለ ንግግር ተገቢ አይደለም፡፡
 • በእርግጥ እንደዚያ ባይናገሩ ጥሩ ነበር።
 • ይኼን ብቻ መሰለህ እንዴ የተናገሩት?
 • እ… ሌላ ምን ብለዋል?
 • በታሪክም ቢሆን ሕዝባችን ለጠላት ጭቆና የተዳረገው የውስጥ አንድነት ስላልነበረው ነው፣ ዛሬ ከጠላት ጋር ውይይት ማድረግ ትልቅ ውርደት ነው፣ ስለዚህ ከዚህ ስህተት ተምረን በአንድነት በመቆም ጠላቶቻችንን እንመክት።
 • እንደዚያ ማለት አልነበረባቸውም፣ ግን ያው…
 • እ… ያው ምን?
 • አልፎ አልፎ የአፍ ወለምታ ሊያጋጥም ይችላል።
 • ከጭቆና ተነስተው ዛሬም ጠላቶቻችንን እንመክት እስከማለት የደረሱበትን ንግግር ነው የአፍ ወለምታ ነው የምትለኝ?
 • ለእኔ ወለምታ ነው የሚመስለኝ።
 • በጭራሽ! ይኼ የአፍ ወለምታ ሳይሆን አቅደው የተናገሩት ነው።
 • እንደዚያ አንኳን እርግጠኛ መሆን የሚቻል አይመስለኝም።
 • በደንብ ይቻላል፣ ከፈለግክ ንግግራቸውን ሲጀምሩ የተናገሩትን አድምጥ፣ ያኔ ጠላት ያሉት ማን እንደሆነ ጭምር ይገለጽልህ ይሆናል።
 • ንግግራቸውን ሲጀምሩ ምንድነው ያሉት?
 • ሕዝባችን ያሳለፈውን ጭቆና ለእናንተው መልሶ መናገር አልፈልግም፣ ነገር ግን አጠገቤ ላሉት እንግዶች እንዲገባቸው በደንብ እነግራቸዋለሁ።
 • እንግዶቹ እነማን ነበሩ?
 • በቦታው ላይ የተገኙ ናቸዋ!
 • በሕዝብ ፊት እንደዚያ መናገር አልነበረባቸውም ቢሆንም ግን…
 • እ… ቢሆንም ምን?
 • እኔ አሁንም የአፍ ወለምታ እንደሆነ ነው የሚሰማኝ።
 • በዝርዝር የተነገረ ሐሳብ እንዴት የአፍ ወለምታ ይሆናል?
 • እኔ በበኩሌ እሳቸው እንዲህ ዓይነት አስተሳሰብ አላቸው ብዬ አላምንም።
 • ምክንያት?
 • ምክንያቱም እኔ ለአገራቸው ያላቸውን ፍቅር በደንብ አውቃዋለሁ።
 • ምንድነው የምታወቀው?
 • በየትኛውም አጋጣሚ ስለኢትዮጵያ እያወሩ ከሆነ…
 • እ…?
 • በዓይናቸው ዕንባ ግጥም ይላል።
 • የምርህን ነው!?
 • የምሬን ነው።
 • ወንድሜን!
 • ምነው?
 • እንዲያው አንድ ወንድሜን!

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ መኖሪያ ቤታቸው ገብተው ከባለቤታቸው ጋር እየተጨዋወቱ ሳለ ባለቤታቸው ስለቴሌቶኑ ጥያቄ አነሱ]

 • እንዲያው ምን ስትሉ ነው ቴሌቶን ውስጥ የገባችሁት?
 • የምን ቴሌቶን?
 • ቴሌቶኑን ነዋ? በአንድ ጀንበር 50 ሚሊዮን ብር ያላችሁትን?
 • ኦ… እሱንማ ከዕቅዳችን በላይ አሳክተን አጠናቀቅነው እኮ፣ አልሰማሽም?
 • እሱንማ ሰምቻለሁ፣ የእኔ ጥያቄ ገንዘቡን ለምን ፈልጋችሁት ይሆን ብዬ ነው?
 • ዘመናዊ የሕዝብ መፀዳጃ ቤቶችን ለመገንባት ነዋ።
 • የት ነው የምትገነቡት?
 • አዲስ አበባ ከተማ ውስጥ።
 • አዲስ አበባ የት አካባቢ?
 • የኮሪደር ልማቱ በሚያልፋባቸው አካባቢዎች።
 • እኔም እኮ መጠየቅ የፈለግኩት እሱን ነው።
 • ምኑን?
 • በዚያ አካባቢ የሕዝብ መፀዳጃ ቤት ለምን ይገነባል?
 • እንዴት? ምን ማለትሽ ነው?
 • ሕዝብ በሌለበት?
 • ለምን የለም?
 • እንዲነሳ ተደርጓላ።
 • ለምንድነው የሚነሳው?
 • ለኮሪደር ልማቱ!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ለፖለቲካዊም ይሁን ኢኮኖሚያዊ ትግል መቀዛቀዝ ምክንያቱ የጠራ ርዕዮተ ዓለም አለመኖር ወይስ የምሁራን መዳከም?

መሬት ላራሹ ብለው በተነሱ ተማሪዎችና ምሁራን ድምፅ የተቀጣጠለው የመጀመሪያው...

በአዲስ አበባ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች የሚሰጡ ድጋፎችንና መሥፈርቶችን ያካተተ አዲስ መመሪያ ወጣ

የአዲስ አበባ ከተማ አስተዳደር በከተማው ወስጥ ለሚገኙ አምራች ኢንዱስትሪዎች...

የዘንድሮ የወጭ ንግድ ገቢ ከዕቅዱም ሆነ ከባለፈው ዓመት ጋር ሲነፃፀር ዝቅተኛ መሆኑ ተገለጸ

የኢትዮጵያ የወጭ ንግድ ገቢ በተያዘው የበጀት ዓመትም የታቀደውን ያህል...

ሕይወትም እንዲህ ናት!

ከዊንጌት ወደ አየር ጤና ነው የዛሬው የጉዞ መስመራችን፡፡ አንዳንዴ...

ሙስና እያስፋፋው ያለው የጥገኝነት መንፈስ

በንጉሥ ወዳጅነው ሰሞኑን ዓለም አቀፍም ሆነ አገራዊ የሥነ ምግባርና የፀረ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ ከዘመዶቻቸውና ቤተሰቦቻቸው ጋር ሆነው በዓሉን በመኖሪያ ቤታቸው እያከበሩ ነው። ባለቤታቸውም ለበዓሉ የተዘጋጀውን ዳቦ ባርከው እንዲቆርሱ ለሚኒስትሩ እያቀረቡ ነው]

በል ዳቦውን ባርክና ቁረስልንና በዓሉን እናክብር? ጥሩ ወዲህ አምጪው... አዎ! በል መርቅ... ከዓመት ዓመት ያድርሰን... ኧረ በሥርዓት መርቅ ተው? ከዓመት ዓመት ያድርሰን አልኩኝ እኮ ...አልሰማሽም? ከዓመት ዓመት መድረሱ ብቻ ምን...

[ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ይፋ ያደረገውን ንቅናቄ አመራሮችና ቤተሰቦቻቸው በግንባር ቀደምትነት እንዲቀላቀሉ መታዘዙን ለባለቤታቸው እያጫወቱ በዚያውም ወደተከፈተው የባንክ ሒሳብ ገንዘብ እንዲያስተላልፉ እያግባቧቸው ነው]

በይ እስኪ ሞባይልሽን አውጪና ወደዚህ የባንክ ሒሳብ አንድ ሺሕ ብር አስተላልፊ? ለምን? መንግሥት ያስጀመረውን ንቅናቄ አመራሩ ከነቤተሰቡ ግንባር ቀደም ሆኖ እንዲደግፍ ታዟል። የምን ንቅናቄ ነው መንግሥት ያስጀመረው? ‹‹ፅዱ...

[ክቡር ሚኒስትሩ እየጠራ ያለውን የእጅ ስልካቸውን ተመለከቱና ደዋዩ አንድ ወዳጃቸው ባለሀብት መሆናቸውን ሲያውቁ አነሱት]

ጤና ይስጥልኝ ክቡር ሚኒስትር? እንዴት ነህ ወዳጄ? ሰሞኑን በተደጋጋሚ ብደውልም ስልኩ ከአገልግሎት መስጫ ክልል ውጪ ናቸው እያለ አስቸገረኝ። አዎ፣ ወጣ ብዬ ነበር። ከአገር ውጭ ነበሩ? አይ... እዚሁ ነው። ምነው በሰላም? በሰላም...