Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናየፀጥታና ኮንትሮባንድ መስፋፋት የውጭ ንግድ ገቢ እንዲቀንስ አድርጓል ተባለ

የፀጥታና ኮንትሮባንድ መስፋፋት የውጭ ንግድ ገቢ እንዲቀንስ አድርጓል ተባለ

ቀን:

የውጭ ምርቶች በሚመረትባቸው አካባቢዎች የፀጥታ ችግር በማጋጠሙና በኮንትሮባንድ ንግድ መስፋፋት ምክንያት የወጪ ንግድ ገቢ ግኝት ማነሱ ተገለጸ፡፡

በ2016 በጀት ዓመት የዘጠኝ ወር አፈጻጸም አጠቃላይ ከዕቃዎች፣ ከሸቀጦች ከውጭ ንግድ ገቢ 3.5 ቢሊዮን ዶላር ለማግኘት ታቅዶ፣ 2.5 ቢሊዮን ዶላር መገኘቱን ከንግድና ቀጣናዊ ትስስር ሚኒስቴር ሪፖርተር ያገኘው መረጃ ያመላክታል፡፡

የዕቃዎችና የሸቀጦች የውጭ ንግድ ገቢ የ2016 ዓ.ም. የስምንት ወር አፈጻጸም ከ2015 ዓ.ም. ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነጻጸር 122 (አንድ መቶ ሃያ ሁለት ሚሊዮን ዶላር) ወይም 4.6 በመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

- Advertisement -

ቀደም ሲል የጫት ምርት ኬላዎች መበራከትና ተደራራቢ የሆነ ታክስና ቀረጥ መኖር፣ ከጫት ምርት የሚገኘው ገቢ በከፍተኛ ሁኔታ መቀነሱንም መረጃው ያሳያል፡፡ በተለይ ከጫት ወጪ ንግድ 337 ሚሊዮን ዶላር ታቅዶ በዘጠኝ ወሩ 138 ሚሊዮን ዶላር ብቻ የተገኘ ሲሆን፣ ይኼም የ40 ከመቶ ክንውን መሆኑን መረጃው ያሳያል፡፡ ከባለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ክንውን ጋር ሲነፃፀር የጫት ገቢ የ32.6 ከመቶ ቅናሽ አሳይቷል፡፡

በዘጠኝ ወሩ ከተገኘው ገቢ የግብርና ምርቶች 73.6 በመቶ በማኑፋክቸሪንግ ዘርፉ 51.54 በመቶ በማዕድን 66.53 በመቶ እንዲሁም በኤሌክትሮኒክስና በሌሎች ምርቶች 71.25 በመቶ መሆኑ ታውቋል፡፡

በዋጋ ግሽበትና የኑሮ ውድነት ችግሮች ምክንያት ዝቅተኛ ገቢ ባለው የማኅበረሰብ ክፍል ላይ የተፈጠረውን የኑሮ ውድነት ጫና በሚፈለገው ደረጃ ማቃለል አለመቻሉ፣ ከፍተኛ የበጀት እጥረት መኖሩ ዘርፉ ላይ ከፍተኛ ችግር እንደፈጠረ መረጃው ያሳያል፡፡

ሚኒስቴሩም አዳዲስ የገበያ መዳረሻዎችን ከመፍጠር አንጻር በሀንጋሪ፣ በሆንዱራስ፣ በእስፔንና በሳዑዲ ዓረቢያ በበጀት መቱ ለወጪ ምርቶቹን አዲስ የገበያ መዳረሻ በመፍጠር ነጭ ቦሎቄ፣ ቀይ ቦሎቄና ኑግ መላክ ችሏል፡፡

በሌላ በኩል ገበያ ከማስፋትና ከማጠናከር አንጻር ወደ ሳዑዲ ዓረቢያ ላለፉት ሦስት ዓመታት ተቋርጦ የነበረውን የቁም እንስሳት በተለይም የበግ ገበያ በድጋሚ ማስጀመር ተችሏል፡፡

የውጭ ንግድ ማሳያ ማዕከል ማቋቋሚያ በመፍጠር 700 ካሬ ሜትር ቦታ ያረፈ የምርትና አገልግሎት ማሳያ ማዕከል ግንባታ ያከናወነ ሲሆን በማሳያ ማዕከሉም የአገሪቱን የንግድ ታሪክ የወጪ ንግድ አቅም እንዲሁም የኢንቨስትመንት አማራጮችን በማስተዋወቅ፣ የወጪ የገበያ ዕድል ለመፍጠርና ተፅዕኖ የሚፈጥር የማሳያ ማዕከል እንዲሆን ለማድረግ ከፍተኛ ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...