Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምየኢራን ፕሬዚዳንት ድንገተኛ ሞት

የኢራን ፕሬዚዳንት ድንገተኛ ሞት

ቀን:

ኢራን የፕሬዚዳንቷን ወንበር በጥቁር ሻሽ አገልድማለች፡፡ ለአምስት ቀናትም የሐዘን ቀን አውጃለች፡፡ የኑክሌር ፕሮግራሟ ለጦር መሣሪያ ይውላል በሚል ከእስራኤልና ከምዕራባውያን በሚሰነዘርባት ውንጀላ አቪዬሽንን ጨምሮ በርካታ ማዕቀቦች የተጣሉባት ኢራን፣ በመካከለኛው ምሥራቅ  ካለባት ውጥረት ሳትወጣ፣ ዛሬ ሐዘን ላይ ተቀምጣለች፡፡

ኢራን ከአዘርባጃን ከምትዋሰንበት ድንበር የተገነባውን የሐይድሮ ኤሌክትሪክ ግድብ ከአዘርባጃን ፕሬዚዳንት ኢሃም አሊየቭ ጋር ለመመረቅ ያቀኑት ፕሬዚዳንት ኢብራሂም ሬሲ፣ ግድቡን ለመመረቅ ቢታደሉም፣ ከምርቃቱ በኋላ የነበራቸውን ፕሮግራም ለማሳካት አልቻሉም፡፡

የኢራን ፕሬዚዳንት ድንገተኛ ሞት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የኢራኑን ፕሬዚዳንትና ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ጨምሮ ዘጠኝ ሰዎችን ያሳፈረው ሄሊኮፍተር የተከሰከሰበት ሥፍራ
በድሮን የተቀረፀ ምስል (ኢሪን)

እሳቸውን፣ የኢራን ውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩን ሆሲን አሚር አብዱላሂንና ሌሎች ከፍተኛ ባለሥልጣናትን ይዛ በመመለስ ላይ የነበረችው ቤል 212 ሄሊኮፍተር፣ ከኩዊዝ ኳላሲ ግድብ በደቡብ 58 ኪሎ ሜትር ርቆ ከሚገኝ ተራራማ ሥፍራ በመከስከሷ ፕሬዚዳንቱን ጨምሮ ዘጠኝ  ባለሥልጣናትና ዘቦች በወጡበት ቀርተዋል፡፡

- Advertisement -

በኢራን የፕሬዚዳንቱንና ከፍተኛ ባለሥልጣናቱን ሞት ተከትሎ ዛሬ ለሦስተኛ ቀን የጎዳና ላይ ሐዘን እየተከናወነ ሲሆን፣ ከኢራን ውጭ ያሉ የሥርዓቱ ተቃዋሚዎች ደግሞ ደስታቸውን ሲገልጹ በዓለም አቀፍ መገናኛ ብዙኃን ታይተዋል፡፡

የፕሬዚዳንቱ መሞት በኢራን ፖሊሲ ላይ ለውጥ ያመጣል ተብሎ እንደማይታሰብ፣ በአገሪቱ የመጨረሻውን ውሳኔ የሚያሳልፉት የኢራን የበላይ መሪ አያቶላህ አሊ ሃሚኒ እንደሆኑ ያስታወሰው አልጀዚራ፣ የኢራን ምክትል ፕሬዚዳንት ሞሐመድ ሞኅበር የሽግግር ፕሬዚዳንት እንዲሁም ምክትል ውጭ ጉዳይ ሚኒስትርና የኢራን የኑክሌር ፕሮግራም ዋና ተደራዳሪ አሊ ባህሪ ካኒ ተጠባባቂ ውጭ ጉዳይ ሚኒስትር ሆነው መሾማቸውን ዘግቧል፡፡

በኢራን ሕገ መንግሥት መሠረት ሹመት በተሰጠ በ50 ቀናት ውስጥ የፕሬዚዳንት ምርጫ የሚካሄድና አዲስ ፕሬዚዳንት የሚመረጥ ይሆናል፡፡ ይህም በኢራን በ2025 እንዲካሄድ ዕቅድ ከተያዘለት መደበኛ ምርጫ በዓመት የቀደመ ነው፡፡

የኢራን ፕሬዚዳንት ድንገተኛ ሞት | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
ኢራናውያን ለፕሬዚዳንታቸው ደኅንነት በቴህራን ፀሎት ሲያደርሱ (አሶሽየትድ ፕሬስ)

የአገሪቱ መንግሥት መገናኛ ብዙኃን እንደዘገቡትም፣ ምርጫው በሰኔ 21 ቀን 2016 ዓ.ም. የሚካሄድ ሲሆን፣ ከግንቦት 22 ጀምሮ ባሉት አምስት ተከታታይ ቀናትም የዕጩዎች ምዝገባ ይደረጋል፡፡

እ.ኤ.አ. ከ1989 ጀምሮ የኢራን የበላይ መሪነቱን ሥልጣን የያዙት የ85 ዓመቱ ሃሚኒ፣ ከቅርብ ጊዜ ወዲህ የጤና እክል እንደገጠማቸው ይነገራል፡፡ በመሆኑም እሳቸውን ማን ይተካል? የሚለው የኢራናውያን ቁልፍ ጥያቄ ነው፡፡ በአገሪቱ ሲናፈስ የከረመው ደግሞ ሬሲ ወይም የ55 ዓመቱ የሃሚኒ ልጅ ሞጃብ ሊተኳቸው ይችላሉ የሚል ነበር፡፡

ይህ በሚናፈስበት ወቅት የፕሬዚዳንቱ በሄሊኮፍተር አደጋ መሞት ጥያቄ ቢያጭርም፣ በአደጋው ዙሪያ የተጀመረው ምርመራ በሥውር የተሠራ ሸፍጥ ይኖራል የሚል ፍንጭ አልሰጠም፡፡

አስቸጋሪ የአየር ሁኔታ፣ መልክዓ ምድርና የቴክኒክ ብልሽት ላይ ትኩረት ተሰጥቶ ምርመራ እየተካሄደ ነው፡፡

ፕሬዚዳንቱና ሌሎች ባለሥልጣናት አርጅቷል በተባለው ቤል 212 ሄሊኮፍተር መጓዝ ነበረባቸው? የሚለው ሌላው በምርመራ ላይ የሚገኝ ሲሆን፣ የአየር ሁኔታው ጭጋጋማ እየሆነ ለምን ሄሊኮፍተሩ እንዲነሳ ተፈቀደ? የሚለውም ተነስቷል፡፡

ከሄሊኮፍተሩ መከስከስ ምርመራ ባሻገር የኢራኑ ፕሬዚዳንት መሞት የፖሊሲ ለውጥ ላይ  ጉልህ  ሚና ባይኖረውም፣ የሬሲ እና የውጭ ጉዳይ ሚኒስትሩ  አብዱላሂ  መሞት፣ በኢራን የውስጥ ፖለቲካ ውስጥ ለውጥ ሊያመጣ ይችላል፡፡ ሆኖም ኢራን በሊባኖስ ከሂዝቦላህ፣ በኢራቅ ከእስላማዊ ሬዚስታንስና በየመን ከሁቲ ጋር ያላትን ግንኙነት አያሳጣትም፡፡

አሁን ሥልጣን የተረከቡትም ሆነ በቀጣይ ምርጫ የሚመጡት፣ የኢራንን ገጽታ መገንባት፣ ለተለያዩ ታጣቂ ቡድኖች የሚደረግ ድጋፍ እንዲሁም ከአሜሪካና ከአውሮፓ ኅብረት ጋር ያለውን ተግባቦት አስቀጥሎ መሄድም ይጠበቅባቸዋል፡፡

ሬሲ አክራሪ፣ ሃይማኖተኛና ወግ አጥባቂ ፖለቲከኛ ነበሩ፡፡ ከሃይማኖት ምሁራንና ከሕግ አውጪዎች ጋር የጠበቀ ግንኙነትም ነበራቸው፡፡ በመንግሥታቸው ላይ ተቃውሞ በሚያነሱ፣ በምዕራባውያኑ ዓለም ሰብዓዊ መብት ናቸው ቢባሉም የኢራንን ሕግ፣ ባህልና ወግ በሚሸረሽሩ ተግባራት በተገኙት ዕርምጃ በመውሰድና የበላይ መሪውን ትዕዛዝ በታማኝነት በማስፈጸም ይታወቃሉ፡፡

የ63 ዓመቱ ሬሲ የኢራኑ የበላይ መሪ የአያቶላህ አል ሃሚኒ ተረካቢ ተብለው ይጠበቁ ነበር፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...