Saturday, June 15, 2024

[ክቡር ሚኒስትር በኢትዮጵያ ታምርት ንቅናቄ እንዲሳተፉ ከተለዩ ባለሀብቶች መካከል እንዱ ጋ ስልክ ደውለው በንቅናቄው ላይ እንዲሳተፉ ግብዣቸውን እያቀረቡ ነው]

 • መቼም ኢትዮጵያ ታምርት በሚል የተጀመረውን አገር አቀፍ ንቅናቄ ሳትሰማ አትቀርም ብዬ ተስፋ አደርጋለሁ።
 • ልክ ነው፣ ሰምቻለሁ ክቡር ሚኒስትር።
 • አሁን ደግሞ ንቅናቄውን ለማጠናከር ኢትዮጵያ ታምርት የሚል የታላቁ የሩጫ ውድድር እንደገና እያዘጋጀን ነው።
 • አሁንም ሩጫ?
 • አዎ፣ ብዙ ሕዝብ የሚሳተፍበት የጎዳና ላይ የሩጫ ውድድር እንደገና ቢዘጋጅ ጥሩ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እርስዎ ሊፈጥሩ ለፈለጉት ጉዳይ የጎዳና ላይ ሩጫም የሚጠቅም አይመስለኝም።
 • ለምን?
 • ምክንያቱም እንዲህ ያሉ የጎዳና ላይ ዝግጅቶች የማኅበረሰብ ግንዛቤን ለመፍጠር ነው የሚረዱት፣ እኛ ደግሞ…
 • እ… ቀጥል?
 • እኛ አምራቾች ደግሞ ኢትዮጵያ ታምርት በሚለው ጉዳይ ላይ የግንዛቤ ችግር የለብንም።
 • የምን ችግር ነው ያለባችሁ?
 • የውጭ ምንዛሪና የምርት ግብዓት እጥረት፣ የገበያ ችግር…
 • እሺ…?
 • የፖሊሲ ድጋፍ ማጣት፣ የቅንጅት ችግርና የመሳሰሉት ናቸው፣ እነዚህ ደግሞ…
 • እ… እነዚህ ደግሞ ምን?
 • እነዚህ ደግሞ በሩጫ ውድድር የሚፈቱ አይደሉም።
 • ምን አባቴ ላድርግ ብለህ ነው?
 • እንዴት?
 • እኔም ይህንን ማድረግ ውጤት ያመጣል ብዬ አላምንም ስለሆነም አልፈለግኩትም ነበር።
 • እና ለምን አይተውትም?
 • ከላይ የወረደ ትዕዛዝ ሆኖብኝ ነው።
 • እንግዲያው ቀስ ብለው ከላይ ላሉት ይንገሩልኝ።
 • ምን?
 • አሁን የሚያስፈልገው ንቅናቄ ኢትዮጵያ ታምርት አይደለም ይበሉልኝ፡፡
 • እና ምንድነው የሚያስፈልገው?
 • የሚያስፈልገው?
 • እ…?
 • ኢትዮጵያ ታርም ነው።
 • ምኗን?
 • ችግርና ስህተቶቿን!

[ክቡር ሚኒስትሩ የሥራ አፈጻጸማቸውን ለተከበረው ምክር ቤት ካቀረቡ በኋላ ከምክር ቤቱ አባላት የሚነሱ ጥያቄዎችን እየተቀበሉ ማብራሪያ በመስጠት ላይ ናቸው]

 • ክቡር ሚኒስትር መንግሥት ለሕዝብ ይፋ ያደረገው ነገር ከምን እንደደረሰ ቢያብራሩልን?
 • ምንድነው ይፋ ያደረገው? ጥያቄውን ትንሽ ቢያብራሩት?
 • ከአራት ዓመት በፊት በኦጋዴን አካባቢ ነዳጅ መገኘቱን ለሕዝብ በቴሌቪዥን አብስሮ ነበር።
 • እህ?
 • ነገር ግን ይህ ጉዳይ ምን ደረጃ እንደደረሰ የሚታወቅ ነገር የለም። በዚህም ምክንያት ሕዝባችን ለጥርጣሬና ለተዛቡ መረጃዎች ተጋልጧል።
 • እህ…
 • ክቡር ሚኒስትር እኛም እንደ ሕዝብ ተወካይ ማወቅ ይገባናል።
 • ትክልል ነው።
 • ስለዚህ ክቡር ሚኒስትር ነዳጁ ይመረታል ወይስ አይመረትም? የሚለውን ማብራሪያ ቢሰጡበት ለማለት ነው።
 • ጥሩ፣ እንደምታውቁት ወደ እዚህ ኃላፊነት ከተመደብኩ ገና አንድ ዓመት ተኩል ቢሆነኝ ነው።
 • አንድ ዓመት ተኩል ብዙ ሊመስል ይችላል፣ ነገር ግን ከዘርፉ ስፋት አንፃር ሁሉንም ጉዳዮች ለማወቅ በቂ አይደለም።
 • ክቡር ሚኒስትር ቅድም እኮ ስለኖራ ምርት ሲያብራሩልን ነበር፡፡
 • አዎ፣ ስለኖራ ጉዳይ አብራርቻለሁ።
 • ታዲያ ስለኖራ ሰፊ ማብራሪያ ሰጥተው እንዴት ስለ ነዳጅ መረጃ አይኖርዎትም?
 • እኔ ወደ እዚህ ኃላፊነት ከተመደብኩ ገና አጭር ጊዜ በመሆኑ በቂ መረጃ የለኝም፣ እንደዚያ ማለቴ ግን ባልደረቦቼ ምላሽ አይሰጡበትም ማለት አይደለም።
 • እንደዚያ ከሆነ ጥሩ፣ እኔ የሚያልፉት መስሎኝ ነው ክቡር ሚኒስትር።
 • አይደለም፣ የተከበረው ምክር ቤት ጥያቄማ ምላሽ ማግኘት አለበት፣ ስለዚህ ክቡር ሚኒስትር ደኤታው እዚሁ ስላሉ ዕድሉን ለእርሳቸው እሰጣለሁ።
 • ክቡር ሚኒስትር፣ እኔ እኮ እርስዎ ከተመደቡ በኋላ ነው ወደ እዚህ ኃላፊነት የመጣሁት፣
 • አንተን ማለቴ አይደለም፣ ተቀዳሚ ሚኒስትር ደኤታውን ማለቴ ነው፡፡
 • ክቡር ሚኒስትር እኔም መረጃው የለኝም።
 • እንዴት?
 • ክቡር ሚኒስትር እኔም እርስዎ ከመሾምዎ ስድስት ወራት አስቀድሞ ነው የተመደብኩት፡፡
 • ስለዚህ የምታወቀው ነገር የለም?
 • የለም ክቡር ሚኒስትር።
 • እንግዲህ በዚህ ጉዳይ ላይ ምላሽ መስጠት ባለመቻላችን የተከበረው ቋሚ ኮሚቴ ይቅርታ እንዲያደርግልን እጠይቃለሁ፣ ነገር ግን….
 • ክቡር ሚኒስትር በይቅርታ የሚታለፍ ነገር የለም፣ የቋሚ ኮሚቴው ጥያቄ የግድ ምላሽ ማግኘት አለበት።
 • እኛም የተከበረው ምክር ቤት ጥያቄ ምላሽ ማግኘት እንዳለበት እናምናለን።
 • ስለዚህ ምላሽ ስጡበት።
 • ለጊዜው ምላሽ መስጠት ስለማንችል የተከበረው ምክር ቤት ቀጥሎ የማቀርበውን ሐሳብ ቢፈቅድልን?
 • ሐሳቡን እንስማው… ይቀጥሉ…
 • ጥያቄውን እንደ ግብዓት ወስደን በቀጣይ ማብራሪያ ብንሰጥበት?
 • እንደምን ወስደን ነው ያሉት?
 • እንደ ግብዓት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...

የ‹‹ክብር ዶክትሬት›› ዲግሪ ጉዳይ

በንጉሥ ወዳጅነው ‹‹የክብር ዶክትሬት ዲግሪ ግልጽ የሆነ መመርያ እስኪወጣ ድረስ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው። ምን ታወጀ? አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡ እሺ? የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ... እ...? ኢትዮጵያ ታምርት...

[ክቡር ሚኒስትሩ ሰሞኑን በተጀመረው አገራዊ የምክክር መድረክ ላይ ስለተላለፉ መልዕክቶች በተመለከተ ከባለቤታቸው ጋር እያወጉ ነው] 

እኔ ምልህ? እ... አንቺ የምትይው? አለቃህ በምክክር መድረኩ ላይ ያስተላለፉትን መልዕክት አደመጥክ? አዎ፡፡ የሚገርም እኮ ነው አልተገረምክም? ምኑ ነው የሚያስገርመው? ለኢትዮጵያ የሚበጀውን ምከሩና አምጡ ብለው የምክክር መድረክ እንዲዘጋጅ ካደረጉ በኋላ...

[የክቡር ሚኒስትሩ ባለቤት የኬንያው ፕሬዚዳንት ያስተላለፉትን መልዕክት ተመልክተው ባለቤታቸውን በነገር ይዘዋቸዋል]

የኬንያው ፕሬዚዳንት ከሕዝባቸው ለቀረበባቸው ቅሬታ የሰጡትን ምላሽ ሰማህ? እንኳን ምላሻቸውን ቅሬታውንም አልሰማሁም። እንዴት? አልሰማሁማ? የምን ቅሬታ ቀርቦባቸው ነው? ሰሞኑን ወደ አሜሪካ ለመጓዝ ውድና ቅንጡ አውሮፕላን ተከራይተዋል የሚል ቅሬታ...