Wednesday, June 12, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዜናአቶ አብነት ገብረ መስቀል ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተፈቱ

አቶ አብነት ገብረ መስቀል ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተፈቱ

ቀን:

ላለፉት ሰባት ወራት በእስር ላይ የነበሩት አቶ አብነት ገብረ መስቀል፣ የተመሠረተባቸው የወንጀል ክስ ተቋርጦ ከእስር ተፈቱ፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር ከስምንት ወራት በፊት በመሠረተባቸው ከባድ የሙስናና ሕገወጥ ገንዘብን ሕጋዊ አስመስሎ ማቅረብ ወንጀሎች ክስ ሲከራከሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

አቶ አብነት ገብረ መስቀል ክሳቸው ተቋርጦ ከእስር ተፈቱ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
አቶ አብነት ገብረ መስቀል

በፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት፣ ዓቃቤ ሕግ በተከሳሹ ላይ የተመሠረተውን ክስ ከሰነድ ማስረጃና ከዓቃቤ ሕግ ምስክሮች የምስክርነት ቃል፣ እንዲሁም ከተገቢ የሕግ ድንጋጌ ጋር በመመርመር አቶ አብነት እንዲከላከሉ ውሳኔ ሰጥቶ ነበር፡፡

- Advertisement -

አቶ አብነት ባደረጉት ክርክር ከተመሠረተባቸው ክስ በነፃ እንደሚሰናበቱ የነበራቸው መተማመን ዕውን ሳይሆን ቀርቶ እንዲከላከሉ ብይን በመሰጠቱ፣ ወዲያውኑ በጠና ታመው ላንድማርክ ሆስፒታል ገብተው እንደነበር ሪፖርተር ከምንጮች አረጋግጧል፡፡

አቶ አብነት ሕመማቸው ስለጠናባቸው በሀሌሉያ ሆስፒታልና በላንድማርክ ሆስፒታል ጊዜያዊ ሕክምና እያደረጉ ቢቆዩም ሊሻላቸው ባለመቻሉ፣ ሕመማቸውን ጠቅሰው ለመንግሥት አቤቱታ ማቅረባቸውንም የሪፖርተር ምንጮች ተናግረዋል፡፡

በማረሚያ ቤት በኩል አቤቱታ የደረሰው የጠቅላይ ሚኒስትር ጽሕፈት ቤት ኮሚቴ በማቋቋም የአቶ አብነት ሕመም እውነት ስለመሆኑና አለመሆኑ ሲያጣራ፣ ተከሳሹ በፅኑ መታመማቸውን በማረጋገጡና ያከሟቸውም ሆስፒታሎች ከአገር ወጥተው ሕክምና ማግኘት እንዳለባቸው ምስክርነት በመስጠታቸው፣ ክሳቸው ሊቋረጥ መቻሉን ምንጮች አክለዋል፡፡

በመሆኑም ክሳቸው እንዲቋረጥላቸው ጥያቄ ያቀረቡት አቶ አብነት፣ ጉዳዩ በፍትሕ ሚኒስቴር ተቀባይነት ማግኘቱ ተረጋግጧል፡፡

የፍትሕ ሚኒስቴር የፌዴራል ጠቅላይ ዓቃቤ ሕግ በተቋቋመበት አዋጅ ቁጥር 943/2008 አንቀጽ 6(3ሠ) ድንጋጌ መሠረት፣ ለፌዴራል ከፍተኛ ፍርድ ቤት ልደታ ምድብ አንደኛ የፀረ ሙስና ወንጀል ችሎት ሰኞ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. በጻፈው ክስ የማቋረጥ ደብዳቤ፣ አቶ አብነት ባደረባቸው ከባድ ሕመም ምክንያት ክርክሩን ለመቀጠል አሥጊ ሁኔታ ላይ በመሆናቸው ክሳቸው እንዲቋረጥ ማመልከታቸውን ገልጿል፡፡

ሚኒስቴር መሥሪያ ቤቱም የተከሳሹን ማመልከቻ መርምሮ ግንቦት 15 ቀን 2016 ዓ.ም. ባስተላለፈው ውሳኔ አቶ አብነትና አብረዋቸው ክስ ተመሥርቶባቸው የነበሩት አቶ አበባው ታደሰ ደጀኔ፣ ወ/ሮ እስከዳር አሰፋ ወልደ ሰንበት፣ አቶ አየለ ዘለዓለም በላይና አቶ ወንድምአገኝ ዳኘው መንግሥቱ ክስ ከግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ጀምሮ የተቋረጠ መሆኑን አስታውቋል፡፡

ይኽንንም ተከትሎ አቶ አብነት ሰሞኑን ከአገር ወጥተው ሊታከሙ ይችላሉ ሲሉ የቅርብ ሰዎቻቸው ግምታቸውን ተናግረዋል፡፡

አቶ አብነት ከሼክ መሐመድ ሁሴን አል አሙዲ ጋር በጋራ ባቋቋሙትና 40 በመቶ ድርሻ የእሳቸው በሆነው ቦሌ ታወርስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር ጋር በተያያዘ በተመሠረተባቸው ክስ ሲከራከሩ ቆይተው፣ እሳቸው (አቶ አብነት) የተከሳሽ ከሳሽ ክስ ቢመሠርቱም ራሳቸው በከሰሱት ክስ ተረትተው እንደተፈረደባቸውና ሌሎች ከስድስት በላይ ክሶችን ሼክ አል አሙዲ በጠበቆቻቸው አማካይነት መሥርተውባቸው ሲከራከሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...