Sunday, June 16, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ንጉሥና ንጉሠ ነገሥት

ትኩስ ፅሁፎች

የታሪክ ተማሪዎችን ጽሑፎች ሳርም በተደጋጋሚ ከሚያጋጥሙኝ ነገሮች አንዱና እዚህ መናገር አለብኝ ካስባሉኝ ጉዳዮች መካከል ‹‹ንጉሥ››ን እና ‹‹ንጉሠ ነገሥት››ን አንድ አድርጎ የመቁጠር ጉዳይ ነው።

ንጉሥ ምኒልክና ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ምንም አንድ ሰው ቢሆኑም በማዕረጋቸው ይለያያሉ። ንጉሡ ምኒልክ ሽዋንና ሸዋ ዙሪያ ያሉ አንዳንድ ቦታዎችን ብቻ ነበር የሚያስተዳደሩት። ለንጉሠ ነገሥቱ ዮሐንስም ግብር መገበር ነበረባቸው። ንጉሠ ነገሥት ምኒልክ ግን ከሥራቸው የተለያዩ ንጉሦች የሚያስተዳድሯቸውን አገሮች አንድ ላይ ጠቅልለው የሚያዙበት ናቸው።

አፄ ኃይለ ሥላሴ ንጉሥ አይደሉም ሆነውም አያውቁም (ወደ አንቺም ጦርነት ያመራውን ዘውዲቱ የግድ ንጉሥ እንዲሏቸው ያደረጉትን ከቆጠርን እሺ)። ራስ ነበሩ ዘለው ንጉሠ ነገሥት ሆኑ። (መሃል ላይ ልዑል አልጋ ወራሽ) ሳስበው ደርግ ሆነ ብሎ ለማዋረድ ‹‹ንጉሡ›› ይላቸው ነበር መሰለኝ። ኢን ኮንክሉዥን በሁለቱ ቃላት መካከል ያለው ልዩነት በጠቅላይ ሚኒስትርና ሚኒስትር መካከል ያለውን ያህል ነው። ይህችን ልብ በሉማ።

  • ጦቢያን በታሪክ
- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች