Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ዓለምለፍልስጤም ዕውቅና መስጠት እስከ ምን?

ለፍልስጤም ዕውቅና መስጠት እስከ ምን?

ቀን:

በጋዛ እየተካሄደ ባለው ጦርነት የሕዝቡ ስቃይ ቀጥሏል፡፡ በዌስት ባንክ ያሉ ጥቃቶች እየባሱ ነው፡፡ ፍልስጤምና እስራኤል ቁርሿቸውንና የይዞታ ይገባኛል ጥያቄያቸውን በሰላማዊ መንገድ ፈትተው፣ ለቀጣናው ሰላም እንዲያሠፍኑ የተደረጉ ጥረቶች ውጤት አላመጡም፡፡ ይህም ንፁኃንን ጭምር ዋጋ እያስከፈለ ነው፡፡ በተለይ እ.ኤ.አ. በጥቅምት 2023 በሐማስ ቀስቃሽነት የተጀመረው ጦርነት የዓለም አገሮችንም አቋም ለሁለት እየከፈለ ነው፡፡

ለፍልስጤም ዕውቅና መስጠት እስከ ምን? | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ለፍልስጤም ሉዓላዊነት ዕውቅና መስጠት ሌሎችን ሊያበረታታ ይችላል (ሮይተርስ ፋይል)

ዓለምንም ‹‹ፍልስጤምን ሉዓላዊ አገር ማድረግ በቀጣናው የሁለትዮሽ መፍትሔ ለማምጣት ያስችላል›› በሚሉና ‹‹ፍልስጤምን ሉዓላዊ አገር ማድረግ ለሐማስ የሽብር ጥቃት ዕውቅና እንደመስጠት ነው›› በሚሉት ጎራ ከፍሏል፡፡  

እ.ኤ.አ. በ2012 በተባበሩት መንግሥታት ድርጅት (ተመድ) የታዛቢነት ወንበር የተቸራት ፍልስጤም፣ የድርጅቱ ሙሉ አባል እንድትሆን በግንቦት መጀመሪያ በቀረበ የውሳኔ ሐሳብ የ143 አባል አገሮችን ድጋፍ ማግኘቷም ይታወሳል፡፡

- Advertisement -

ይህ የውሳኔ ሐሳብ እንዲፀና የተባበሩት መንግሥታት ድርጅት ፀጥታው ምክር ቤት ማፅደቅ ይጠበቅበታል፡፡ እዚህ ላይ ደግሞ ከዚህ ቀደም ጥያቄውን ድምፅን በድምፅ ሽራ ውድቅ ያደረገችው አሜሪካ ውሳኔ ትልቁን ሥፍራ ይይዛል፡፡

ይህም ሆኖ ግን በርካታ የአውሮፓ አገሮች ለፍልስጤም አገርነት ዕውቅና እየሰጡ ነው፡፡ ይህ በፍልስጤምና በእስራኤል መካከል ያለውን የገዘፈ ችግር በመሠረታዊነት ለመፍታት ያስችላል ባይባልም፣ መንገድ ሊጠርግ እንደሚችል ቢቢሲ ይገልጻል፡፡

ሰሞኑን አየርላንድ፣ ስፔንና ኖርዌይ ለፍልስጤም ዕውቅና መስጠታቸውም እንግሊዝን፣ ፈረንሣይንና ጀርመንን ጨምሮ በሌሎች የአውሮፓ አገሮች ውስጥ ተፅዕኖ ይፈጥራል፡፡ ፍልስጤም የራሷን ዕድል በራሷ እንድትወስን ድጋፍ እንዲያደርጉም ያስችላል፡፡

ለፍልስጤም ዕውቅና መስጠት እስከ ምን? | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
የስፔን ጠቅላይ ሚኒስትር ለፍልስጤም ዕውቅና ሲሰጡ ከመንግሥት ተወካዮች አድናቆት ተችሯቸዋል (ኤኤፍፒ)

 ይህ ደግሞ የፍልስጤም ሉዓላዊነት በመላው ዓለም ዕውቅና እንዲያገኝ ለሚሠሩ የዓረብ አገሮች ዋና ጉዳይ ነው፡፡

እስራኤል ግን ለፍልስጤም ሉዓላዊነት ዕውቅና የመስጠቱን አጀንዳ ፍፁም አትቀበለውም፡፡ ይልቁንም ጋዛን ለሚያስተዳድረው ሐማስ እንዲሁም ሽብርተኝነት ዕውቅና መስጠት ነው ስትልም ትኮንናለች፡፡ አገሮች ለፍልስጤም ዕውቅና መስጠት ችግሩን በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል ቢሉም፣ እስራኤል የመደራደር መንገዶችን ያጠባል ትላለች፡፡  

ፍልስጤም የተመድ ሙሉ አባል ለመሆን ያቀረበችው ጥያቄ አገር ለመሆን በራሱ ባያስችልም፣ መንገድ ግን ይከፍታል፡፡ በዓረብ ሊግና በእስላማዊ ትብብር ድርጅት ዕውቅና ማግኘቷም አገር ተብላ ዕውቅና እንድታገኝ አንድ ግብዓት ነው፡፡

ሀንጋሪ፣ ፖላንድ፣ ሮማንያ፣ ቼክ ሪፐብሊክ፣ ስሎቫኪያ፣ ቡልጋሪያ፣ ስዊድን፣ ቆጵሮስና ማልታ ለፍልስጤም ሉዓላዊነት ዕውቅና ሲሰጡ፣ ሌሎች የአውሮፓ አገሮችና አሜሪካ የተለየ አቋም አላቸው፡፡

አሜሪካ ለፍልስጤም ሉዓላዊነት ዕውቅና የምትሰጠው ለመካከለኛው ምሥራቅ ዘላቂ የፖለቲካ መፍትሔ አካል እንዲሆን ነው፡፡ አሜሪካን ጨምሮ በኃያላን የአውሮፓ አገሮች የሚነሳው ‹‹የሁለት አገሮች መፍትሔ››ም የዚሁ አካል ነው፡፡ ይህ የሚሆነው ደግሞ እስራኤልና ፍልጤም የራሳቸው አገርና ድንበር ላይ ከስምምነት ሲደርሱ ነው፡፡

አገሮች ከዚህ ቀደም ለፍልስጤም ሉዓላዊነት ዕውቅና የሚሰጡት የሰላም ስምምነት ከተደረሰ በኋላ ነው የሚል አቋም ቢኖራቸውም፣ አሁን ሰላም ለማስፈን ቅድሚያ ፍልስጤም ሉዓላዊት መሆን አለባት ወደሚለው አቋም እየዞሩ ነው፡፡

ለዚህም ፍልስጤም የተመድ ሙሉ አባል እንድትሆን በቀረበ የውሳኔ ሐሳብ ላይ በርካታ የአውሮፓ አገሮች ይሁንታ መስጠታቸው እንደማሳያ ይነሳል፡፡

ሆኖም ለፍልስጤም አገርነት ዕውቅና መስጠት ብቻ በቂ አይደለም፡፡ በርካታ መፈታት ያለባቸው መሠረታዊ ጥያቄዎች መልስ ማግኘት አለባቸው፡፡

ለፍልስጤም ዕውቅና የሰጡ አገሮች የፍልስጤምና የእስራኤል ድንበር የት ነው? የፍልስጤም ዋና ከተማ የት መሆን አለበት? በሁለቱ አገሮች ሰላም ለማስፈን ከሁለቱም ወገን ምን መሠራት አለበት? ለሚለው፣ ለዓመታት መልስ ላላገኘውና ለጦርነትና ግጭት መንስዔ ሆኖ ለዘለቀው ጥያቄ መስጠት አለባቸው፡፡

ይህ ለአሠርታት መልስ ያላገኘ ጥያቄ እያለ፣ አንዳንድ የአውሮፓ አገሮች ለፍልስጤም ሉዓላዊነት ዕውቅና ቢሰጡም፣ ከመልካምነት የዘለለ ትርጉም አይኖረውም፡፡ በፍልስጤም ያለውን አሰቃቂ እውነታም አይለውጠውም፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...