Thursday, June 13, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ማኅበራዊድህነትን በጋራ የማጥፋት ውጥን

ድህነትን በጋራ የማጥፋት ውጥን

ቀን:

ገበሬውን ተጠቃሚ ለማድረግና ድህነትን ለመቅረፍ ከተፈለገ፣ ገበሬው አምርቶና ፕሮሰስ አድርጎ ወደውጭ እንዲልክ ማስቻል ወሳኝ ነው፡፡ ለዚህም በመንግሥት በኩል የተለያዩ ኢንሺየቲቮች እየተተገበሩ ሲሆን፣ የግሉ ዘርፍም ተሳታፊ እየሆነ ነው፡፡

በተለያዩ አገራዊ ጉዳዮች ላይ ለውጥ ማምጣት የሚቻለው በጋራ መሥራት ሲቻል በመሆኑ ‹‹ኑ አብረን እንሥራ›› የሚል መርህ አስቀምጠው እየሠሩ መሆኑን የሚገልጹት የፐርፐዝ ብላክ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ፍሰሐ እሸቱ (ዶ/ር)፣ ለዚህም ሕጉ ተስተካክሎ መውጣቱና ገበሬው በቀጥታ ለውጭ ገዥዎች ማቅረብ እንዲችል መመቻቸቱ መልካም እርምጃ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

ለዚህ ደግሞ ገበሬውን በሁሉም ዘርፍ መደገፍና ምርቱን ለውጭ ገበያ እንዲያቀርብ ማገዝ እንደሚያስፈልግ፣ የሚመሩት ተቋምም ይህንኑ ለማሳካት እየሰራ መሆኑን፣ በጋራ መሥራት ካልተቻለ ለውጥ እንደማይመጣ አስታውሰዋል፡፡

- Advertisement -

ፐርፐዝ ብላክ ግንቦት 19 ቀን 2016 ዓ.ም. ከግሪን ኬር ናቹራልስ ጋር በቡና ላይ በጋራ ለመሥራት የመግባቢያ ሰነድ በተፈራረመበት ወቅት ፍስሐ (ዶ/ር) እንዳሉት፣ ተቋማቸው በአፍሪ ቡና ፕሮጀክቱ የቡና አርሶአደሮችን በክላስተር በማደራጀት አብሮ መስራት ጀምሯል፡፡ 

ፐርፐዝ ብላክ ቡናን ይዞ የሚንቀሳቀስበት ዋና ምክንያትም የብዙ ሚሊዮኖችን ሕይወት ለመታደግና ከድህነት አዙሪት ለማውጣት እንደሆነ አክለዋል፡፡

በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵያውያን በቀጥታም ይሁን በተዘዋዋሪ ሕይወታቸው በቡና ላይ የተመረኮዘ ቢሆንም፣ የሚገባቸውን ያህል ጥቅም ስለማያገኙበት ይህንን መለወጥ ያስፈልጋል የሚሉት ፍስሐ (ዶ/ር)፣ የቡና ገበሬዎች ምርታማነታቸውን ከመጨመር አኳያ ገበሬዎችን በክላስተር እያደራጁ፣ ትራክተር ከማቅረብ ጀምሮ ድጋፍ እየሰጡ ምርት ለማሻሻል ጥረት እያደረጉ እንደሆነ አክለዋል፡፡

በተቋማቸው እምነት ቡና ለፍቶ እያመረተ ያለው ገበሬ ከቡናው ከሚገኘው ጥቅም እምብዛም እንደማያገኝ፣ ይህንን ለመቀየር ፐርፐዝ ብላክ ቀጥታ ከቡና ገበሬው ለተጠቃሚው ለማድረስ ጅማሮ ላይ መሆኑን፣ ገበሬዎችን በአንድ ላይ በክላስተር በማደራጀት ቡናቸውን አንድ ላይ አድርገው ፕሮሰስ አድርገው ወደ ውጭ የሚልኩበት ሁኔታ ላይ እየሰራ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ ፍሰሐ (ዶ/ር)፣ ያለቀበት የቡና ምርትን ለገበያ ለማቅረብ አፍሪ ቡናን ማቋቋማቸው ምርቱን በተለያዩ አገሮች ለማሠራጨት ያስችላል፡፡ ይህ የበለጠ ውጤታማ የሚሆነው በጋራ ሲሰራ በመሆኑ፣ ኅብረተሰቡ ተሳታፊ የሚሆንበት ኢንቨስት ኢን ፖቨርቲ ኢኒሺየቲቭን ባለፈው ሳምንት አስተዋውቋል፡፡

ይህ ኢንሺየቲቭ ኅብረተሰቡ በወር 100 ብርና ከዚህ በላይ በኅብረት ባንክ እየቆጠበ 10 በመቶ ወለድ የሚያገኝበትና ገንዘቡን በፈለገ ሰዓት የሚያወጣበት ሲሆን፣ ፐርፐዝ ብላክም ከኅብረት ባንክ ጋር በገባው ውል መሠረት አንድ ቢሊዮን ብር ማስቀመጡን ተናግረዋል፡፡

ከባንኩ ጋር በተደረገ ስምምነት መሠረት፣ 19 በመቶ ወለድ እንዳለው፣ ከወለዱ በየወሩ 100 ብርና ከዚህ በላይ ለሚቆጥቡት ከመደበኛው ሰባት በመቶ ወለድ በተሻለ የ10 በመቶ ወለድ ተከፋይ እንደሚያደርግ፣ ቀሪው ዘጠኝ በመቶ ወለድ ፐርፐዝ ብላክ በሚሊዮን የሚቆጠሩ ኢትዮጵውያንን ሕይወት ለመለወጥ የሚሰራበት እንደሚሆንም ገልጸዋል፡፡

ከዚሁ ጎን ለጎን ቡና ተፈልቶ ከመጠጣት ባለፈ ለተለያዩ ጥቅሞች ስለሚውል፣ በቡና ዘይት ዘርፍ ከተሰማራው ግሪን ኬር ናቹራልስ ጋር አብረው እንደሚሰሩ አስታውቀዋል፡፡

ግዛው በቀለ (ዶ/ር)፣ የግሪን ኬር ናቹራልስ ኃላፊነቱ የተወሰነ የግል ማኅበር መሥራችና ዋና ሥራ አስኪያጅ ናቸው፡፡ በኢትዮጵያ የዕፅዋት ዝርያና አጠቃቀም ዙሪያ ለ15 ዓመታት ጥናት ያደረጉት ግዛው (ዶ/ር) ፣ በተለይ ከቡና ዘይት ለቆዳ ሕክምና የሚውሉ መድኃኒቶች በማምረትና ውጭ በመላክ ላይ ይሠራሉ፡፡

ግዛው (ዶ/ር)፣ ከፐርፐዝ ብላክ ጋር አብረው ለመሥራት በድርጅታቸው በኩል የተፈራረሙት የመግባቢያ ሰነድ፣ የኢትዮጵያን የውጭ ምንዛሪና የገበሬውን ገቢ ለማሳደግ ዕገዛ እንደሚያደርግ ተናግረዋል፡፡

በኢትዮጵያ ከቡና ዘይት በማምረት ዙሪያ ጥናት በማድረግና ከሌሎች አገሮች የተሸለ ውጤት በማስመዝገብ ላይ መሆናቸውም፣ ለቡና ገበሬዎችና ለአገር ትልቅ እሴት እንደሚሆን ጠቁመዋል፡፡

ሁለቱ ተቋማት ባደረጉት የመግባቢያ ስምምነት መሠረት፣ ግሪን ኬር ናቹራልስ ምርት ሲያመርት፣ ፐርፐዝ ብላክ በዘረጋቸው የማሠራጫ ማዕከላት ምርቶቹን የሚያቀርብ ይሆናል፡፡

ሕዝቡ ተፈጥሮን እንዲጠቀም ግንዛቤ በመፍጠሩ ዙሪያ አብረው የሚሠሩ በመሆኑም፣ የገበሬዎችን የአቅራቢነት ድርሻ ከፍ በማድረግ ገበሬዎች ተጠቃሚ የሚሆኑበትን ሁኔታ ይፈጥራሉ፡፡

ገበሬው በቀጥታ ተጠቃሚ እንዲሆን ጥረት እንደሚደረግና ትልቁ ገቢ የገበሬው እንዲሆን አብረው እንደሚሠሩ ስምምነቱን ባደረጉበት ወቅት አስታውቀዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...