Saturday, June 15, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -

ኪንና ባህል‹‹ቢስት ባር›› - የቤንች የተስፋና የበረከት ተምሳሌታዊ በዓል

‹‹ቢስት ባር›› – የቤንች የተስፋና የበረከት ተምሳሌታዊ በዓል

ቀን:

ቀደም ባሉት ስድስት አሠርታት ‹ሰርቲ መንዝስ ኦቭ ሰንሻይን› (አሥራ ሦስት የፀሐይ ወራት) በሚል መለያ ትታወቅ የነበረችው ኢትዮጵያ፣ ከቅርብ ዓመታት ወዲህ ደግሞ ‹ላንድ ኦቭ ኦሪጅንስ› (ምድረ ቀደምት) የሚል መለያ በቱሪዝም መሥሪያ ቤቷ አማካይነት ራስዋን እያስተዋወቀች ነው፡፡

‹‹ቢስት ባር›› - የቤንች የተስፋና የበረከት ተምሳሌታዊ በዓል | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

 ዘወትር እንደሚወሳው ለየት ያሉ መለያዎች አሏት ከሚያስብሉት መካከል የዘመን አቆጣጠሯ ይጠቀሳል፡፡ መስከረም ብቶ ጳጉሜን ከሚያበቃው ከመደበኛው የዘመን መቁጠሪያዋ በተጨማሪ፣ እንደየኅብረተሰቡ ባህልና ሃይማኖት የተለያዩ የዘመን መስፈሪያዎች አሏት፡፡

- Advertisement -

በአሥራ ሦስት ወራት ፀሐይ የማይለያት፣ 13 ወር ጸጋ የሚባልላት ከግማሽ ክፍለ ዘመን በላይ የቱሪስት ማስተዋወቂያ መለያዋ (ብራንድ) ሆኖ የዘለቀው የተቀዳው ከዚህ ልዩ አቆጣጠሯ ነው፡፡

በሕዝባዊው ካሌንደር መሠረት ከትናንት በስቲያ የተጀመረው ሰኔ፣10ኛው ወር ላይ ሲሆን፣ ዓምና በሐምሌ የባተው የበጀት (የሒሳብ) ዓመት ደግሞ 12ኛና የመጨረሻ ወር ላይ ደርሷል፡፡‹‹ቢስት ባር›› - የቤንች የተስፋና የበረከት ተምሳሌታዊ በዓል | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

‹‹ሠኔ የወር ስም ዐሥረኛ ወር በግብጽና በኢትዮጵያ፡፡ ሠናየ ዘርዕ [መልካም ዘር]፣ ወርኃ ዘርዕ [የዘር ወር] ሠናይ ማለት ነው፤››  በማለት በመዝገበ ቃላት ሐዲስ የፈቱት አለቃ ኪዳነ ወልድ ክፍሌ ናቸው፡፡  በኦሮምኛ ‹ሠኚ› ሲል ዘር ማለት እንደሆነም ያክላሉ፡፡  ‹‹ዐሥረኛ ወር ከመስከረም›› ብለው በዐዲስ ያማርኛ መዝገበ ቃላት ሥራቸው መግለጽ የጀመሩት አለቃ ደስታ ተክለ ወልድ፣ ትርጓሜውም ሠናዪ ሠናይ ማለት እንደሆነ፣ የርሻን መለስለስና የዘርን መዘራት እንደሚያሳይ ያብራራሉ፡፡

ይህን ብያኔ ደግሞ በአገሪቱ ባሉ የተለያዩ ማኅበረሰቦች ከእርሻ ጋር የሚያያዝ ብቻ ሳይሆን ከባህላቸውና ከትውፊታቸው የሚቀዱ ክብረ በዓላት አሉዋቸው፡፡ ለዚህ አንዱ ማሳያ ሰኔ 1 ቀን 2016 ዓ.ም. በደቡብ ምዕራብ ኢትዮጵያ ክልል የሚገኘው የቤንች ብሔረሰብ ያከበረው የዘመን መለወጫና የምስጋና በዓል ነው፡፡ በዓሉ በብሔረሰቡ ቋንቋ ቢስት ባር ይባላል፡፡ ‹‹ቢስት›› ማለት የመጀመሪያ ወይም የበኵር ሲሆን፣ ‹‹ባር›› ደግሞ በዓል የሚል ፍች አለው፡፡

‹‹ቢስት ባር›› - የቤንች የተስፋና የበረከት ተምሳሌታዊ በዓል | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር

የቤንች ሸኮ ዞን ኮሚዩኒኬሽን እንዳስታወቀው፣ የቤንች ብሔረሰብ የዘመን መለወጫ ቢስት ባር መከበር የጀመረው በዋዜማው ግንቦት 30 ቀን፣ የቤንች ብሔር መነሻ በሆነው በሼይ ቤንች ወረዳ ዣዥ ቀበሌ ነው፡፡ በበዓሉ መርሐ ግብር የብሔሩ ተወላጆች የፌዴራልና የክልል፣ የዞን እና የሁሉም ወረዳ አመራሮች፣ ባለአባቶችና የአካባቢው ‹ነገሥታት› ተገኝተዋል። በማግስቱ ቅዳሜ የተከበረው ደግሞ በሚዛን አማን ከተማ አማን ሜዳ ነው፡፡

የዞኑ ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች ጽሕፈት ቤት በማኅበራዊ ትስስር ገጹ እንደገለጸው፣ ቢስት ባር የአዲስ የዘመን መሻገሪያ፣ ብኩርናና ታላቅነት የሚወደስበት፣ ፈጣሪ በምስጋና የሚወደስበትና ሰዎች በአብሮነት የሚሰየሙበት ድንቅ ባህላዊ እሴት ነው።

የቤንች ብሔረሰብ በልዩ ዝግጅትና በድምቀት ከሚያከብራቸው ሦስት ትላልቅ በዓላት መካከል አንዱ የሆነው ቢስት ባር የጥጋብ፣ የተስፋና የበረከት ተምሳሌት እንዲሁም የዘመን መለወጫና የምስጋና ቀን እንደሆነ ያነጋገራቸው የአገሬው ባላባት ‹መር ቲያት› ሜርቴት ሻሽ ናቸው፡፡

የአገሬው ባላባት/ንጉሥ በመልዕክታቸው ቢስት ባርን ያብራሩት፣ ‹‹የእህል ወቅትን ተከትሎ በአካባቢው አባቶች የበኩር/ የመጀመሪያው እሸት የሚቀመስበት ረሃብና ድርቅ እንዲሁም በሽታ ከአካባቢው እንዲጠፋ አባቶች ተሰብስበው የሚመርቁበት፣ ለፈጣሪ ምስጋና የሚቸርበት ባህላዊ ሥርዓት ነው፤›› በማለት ነው፡፡

‹‹በዓሉም (ቢስት ባር) በቲያት/ በባላባቶች ምርቃት የሚመራ ሲሆን፣ በዕለቱም የዕርድ ሥርዓትን በማከናወን፣ ቦርዴ ተጠምቆ ከጎሳ መሪዎች በመጀመር የመብላትና የመጠጣት ሒደቱ ከተከናወነ በኋላ፣ ወጣት ሴቶችና ወንዶች በጨረቃ ብርሃን በደስታ ይጨፍራሉ።››

ቢስት ባር ከጥንት ጀምሮ ቤንቾች በድምቀት የሚያከብሩትና የማንነታቸው መገለጫና መድመቂያቸው ነው፡፡

 በዓሉ ለመጀመሪያ ጊዜ የአካባቢው ቲያቶች/ ባላባቶች እንዲሁም የአገር ሽማግሌዎችና ሌሎችም በአብሮነትና በታላቅ ድምቀት አክብረውት በማየታቸው ለአካባቢው አመራሮች ምስጋና አቅርበዋል፡፡

‹‹ቢስት ባር አንድ ጊዜ አክብረን የምንተወው ሳይሆን በዓሉን በቀጣይ በታላቅ ድምቀት ለማክበር ቃላችንን ዳግም የምናድስበት፣ ባህላችንና ታሪካችንን ለማሳደግ በአንድነት የምንቆምበት እንዲሆን እጠይቃለሁ፤›› ብለዋል ባላባቱ፡፡

‹‹ቢስት ባር በአብሮነት የመቆምና የደረሰን እህል በአንድ ላይ ተቋድሶ በጋራ የመብላት ባህል ማንፀባረቂያ በዓል ሲሆን፣ ከአሮጌው ዓመት ወደ አዲሱ ዓመት ሕዝቡን፣ ቤተሰቡን፣ ልጆቹን፣ እርሻውን፣ ከብቶቹንና ቀየውን በሰላም ጠብቆ ላቆየው ፈጣሪ ምስጋና የሚያቀርብበት በዓል ነው፤›› ያሉት በዓሉን አስመልክቶ የእንኳን አደረሳችሁ መልዕክት ያስተላለፉት የክልሉ ፓርቲ ጽሕፈት ቤት ኃላፊ አቶ ፀጋዬ ማሞ ናቸው፡፡

ከተፈጥሮ ጋር የጠበቀ ቁርኝት ያለው ቤንች የወቅት መፈራረቅን መሠረት ባደረገ ጥበብ ዓመትን ሲቀይር፣ ዘመንን ሲቀምር መቆየቱን ጠቅሰዋል።

በዚህም በዕድሜ የቀደመን ማስቀደም፣ የቤንች ብሔር አባላት ካሉት የሚያኮሩ እሴቶች አንዱ መሆኑን፣ የበኩር እህል ሲደርስ በዕድሜ ባለፀጋ የሆኑ አባትና እናቶች ቅድሚያ የሚሰጣቸው እንደሆነ መናገራቸው በማኅበራዊ ገጹ ተገልጿል።

የአገሬው ባላባት ‹መር ቲያት› ሜርቴት ሻሽ፣ ቢስት ባር የፍቅር የሰላምና የደስታ፣ የጥጋብና የበረከት፣ እንዲሁም ቸነፈርና በሽታ ከአካባቢው የሚጠፋበት ዘመን እንዲሆን በራሳቸውና በሕዝባቸው ስም ምኞታቸውን ገልጸዋል ተብሏል፡፡

በክብረ በዓሉ አጋጣሚ፣ የቤንች ብሔር ባህልና ቋንቋ ላይ ያተኮረ የፓናል ውይይት በሚዛን አማን ከተማ መካሄዱንም ዞኑ አስታውቋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

እኔ ምልህ? እ... ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው? ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም? የምን ንቅናቄ? በመንግሥት...

የመንግሥት የ2017 ዓ.ም በጀትና የሚነሱ ጥያቄዎች

የ2017 ዓመት የመንግሥት ረቂቅ በጀት ባለፈው ሳምንት መገባደጃ ለሚኒስትሮች...

ከፖለቲካ አባልነትና ከባንክ ድርሻ ነፃ የሆኑ ቦርድ ዳይሬክተሮችን ያካተተው ብሔራዊ ባንክ ያዘጋጃቸው ረቂቅ አዋጅና መመርያዎች

የኢትዮጵያ የብሔራዊ ባንክ የፋይናንስ ተቋማትን የተመለከቱት ድንጋጌዎችንና የባንክ ማቋቋሚያ...

የልምድ ልውውጥ!

እነሆ መንገድ ከቦሌ ሜክሲኮ። አንዱ እኮ ነው፣ ‹‹እንደ ሰሞኑ...