Sunday, July 14, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
ማኅበራዊበከተሞች አካባቢ የቲቢ በሽታ ሥርጭት እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

በከተሞች አካባቢ የቲቢ በሽታ ሥርጭት እየጨመረ መሆኑ ተገለጸ

ቀን:

በከተሞችና በተለያዩ ተቋማት አካባቢዎች የቲቢ በሽታ እየጨመረ መሆኑን ጤና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡

ከተሞችን ጨምሮ በግጭት የተጎዱ አካባቢዎች ድርቅ በስፋት የተከሰተባቸው ቦታዎች፣ ማረሚያ ቤቶች፣ የጤና ተቋማትና ትልልቅ የልማት ተቋማት፣ እንዲሁም የኢንዱስትሪ ፓርኮችና በአጠቃላይ ሰዎች በርከት ብለው የሚሰባሰቡባቸው አካባቢዎች የቲቢ በሽታ ሥርጭት እየጨመረ መምጣቱን የጤና ሚኒስትር ደኤታ ደረጀ ድጉማ (ዶ/ር) ተናግረዋል፡፡

ሚኒስትር ዴኤታው ይህንን የተናገሩት ትናንት ማክሰኞ ሰኔ 4 ቀን 2016 ዓ.ም. የቲቢ በሽታን ለመከላከል የሚያስችል ፕሮጀክት የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጀት (ዩኤስኤአይዲ) ይፋ ሲያደርግ ነው፡፡

በተለይ በከተሞች አካባቢ ያለው የቲቢ በሽታ ሥርጭት በጣም ከፍተኛ መሆኑን የገለጹት ሚኒስትር ደኤታው፣ ኮቪድ-19 ወረርሽኝ ለበሽታው ሥርጭት መጨመር አሉዊ ተፅዕኖ እንደነበረው አስረድተዋል፡፡

ፕሮጀክቱ ለቀጣዮቹ አምስት ዓመታት የሚተገበር መሆኑን፣ እየጨመረ የመጣውን የቲቢ በሽታ ለመቆጣጠር ጉልህ አስተዋጽኦ እንደሚኖረው አብራርተዋል፡፡

በ7.5 ሚሊዮን ዶላር ይተገበራል የተባለው ፕሮጀክት ‹‹ሪች ኢትዮጵያ›› በተባለ አገር በቀል ድርጅት በኩል ተፈጻሚ እንደሚሆን የተናገሩት ደግሞ፣ በኢትዮጵያ የአሜሪካ ዓለም አቀፍ ተራድኦ ድርጀት የጤና ቢሮ ጊዜያዊ ዳይሬክተር ኮፕሪንስ ናቸው፡፡

ፕሮጀክቱ የቲቢ በሽታ ምርመራን ሕክምናና ልየታን በማሳደግ በተለያዩ ከተሞች ላይ ያለውን ሥርጭት ለመቀነስ ያለመ መሆኑን ጊዜያዊ ዳይሬክተሯ ገልጸዋል፡፡

አዲስ አበባን ጨምሮ በድሬዳዋ፣ በሐረርና ሸገር ከተሞች እንደሚተገበር ገልጸው፣ ከ5.5 ሚሊዮን በላይ ዜጎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርግ አክለዋል፡፡

‹‹አገር በቀል ድርጅቶች ትስስር ፕሮጀክት ሁለት›› የተሰኘው ይህ ፕሮጀክት በአገር በቀል ድርጅት ተፈጻሚ መሆኑ ተደራሽነቱን እንደሚያሰፋው ጠቁመዋል፡፡

የአሜሪካ መንግሥት የጤና ዘርፉን ለመደገፍ በዩኤስኤአይዲ በኩል በየዓመቱ ሁለት መቶ ሚሊዮን ዶላር ያወጣል ያሉት ጊዜያዊ ዳይሬክተሯ፣ ይህም የእናቶችና የሕፃናት ሞትን እንዲሁም ቲቢን ጨምሮ ሌሎች ተላላፊ በሽታዎችን ለመቀነስ እንደሚሠራበት ተናግረዋል፡፡

ዩኤስኤአይዲ ላለፉት 20 ዓመታት በቲቢ በሽታ ላይ ሰፋፊ ሥራዎችን እየሠራ መቆየቱን፣ ሕመምተኞችን በሰዓቱ አግኝቶ ማከምና ማዳን ትልቁ ሥራ ነው ብለዋል፡፡

ከዚህ ቀደም የቲቢ በሽታን ለመመርመር ብዙ ቀናት ይፈጅ እንደነበር አስታውሰው፣ በአሁኑ ወቅት ግን ድርጅቱ ጂን ኤክስፐርትና ትሩናት የተባሉ የቲቢ በሽታ መመርመሪያ መሣሪያዎችን ድጋፍ በማድረጉ በሽታውን በአጭር ጊዜ ለማውቅ እንደሚቻል አስታውቀዋል፡፡

ፕሮጀክቱ አገር በቀል ድርጅቶችን ማሳተፉ ሊበረታታ የሚገባ ነው ሲሉ የተናገሩት የጤና ሚኒስትር ደኤታው ደረጀ (ዶ/ር) ናቸው፡፡

እንደ ሪች ኢትዮጵያ የመሳሰሉ አገር በቀል ፕሮጀክቶች መሳተፋቸው ማኅበረሰቡን በማገልገል በኩል የተሻለ ውጤትን ያስመዘግባሉ ብለዋል፡፡

በከተሞች አካባቢ የቲቢ መድኃኒትን ጀምሮ የመጨረስ ምጣኔ አነስተኛ ነው ያሉት ደረጀ (ዶ/ር)፣ ፕሮጀክቱ የቤት ለቤት ምርመራና ክትትል በማድረግ መሰል ችግሮችን ለመፍታት እንደሚሠራ አብራርተዋል፡፡ ከዚህ ባሻገር ክትትሉን በአገር አቀፍ ደረጃ ለማስፋት መታቀዱን ጠቁመዋል፡፡

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

spot_img

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

ሚዲያው በሕዝብ የህሊና ችሎት ከተዳኘ በቂ ነው!

መሰንበቻውን ድንገት ሳይታሰብ ያለ ማስጠንቀቂያ ጠቅላይ ሚኒስትር ዓብይ አህመድ...

የባህር በር ጉዳይ

በታምሩ ወንድም አገኘሁ ድሮ ድሮ ገና ልጅ ሆኜ ፊደል እንደቆጠርኩ...

አገሩ ፖለቲካዊ ስክነትና መደማማጥ ያስፈልገዋል

በንጉሥ ወዳጀነው    ኢትዮጵያ የሁላችንም የጋራ ቤት ነች፡፡ ‹‹ጥያቄዬ ተመለሰልኝ››፣...

የመንግሥት የሰብዓዊ መብት ተቋም ለምን የመንግሥት ሚዲያን ማስተማር አቃተው

በገነት ዓለሙ የአገራችን የ2016 የበጀት ዓመት መሰናበቻና የአዲሱ የ2017 በጀት...