Wednesday, July 24, 2024

[ክቡር ሚኒስትሩ በመንግሥት የሚታወጁ ንቅናቄዎችን በተመለከተ ባለቤታቸው ለሚያነሱት ጥያቄ ምላሽ ለመስጠት እየሞከሩ ነው]

 • እኔ ምልህ?
 • እ… ዛሬ ደግሞ ምን ልትይ ነው?
 • ንቅናቄዎችን አላበዙባችሁም?
 • የምን ንቅናቄ?
 • በመንግሥት የሚታወጁ ሕዝባዊ ንቅናቄዎችን ማለቴ ነው።
 • ምን ታወጀ?
 • አንዴ ከዕዳ ወደ ምንዳ አላችሁ፡፡
 • እሺ?
 • የእሱን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ…
 • እ…?
 • ኢትዮጵያ ታምርት አላችሁ፡፡
 • እሺ?
 • የዚህን ውጤት እየጠበቅን ሳለ ደግሞ ሌላ ነገር አላችሁ።
 • አሁን ደግሞ ምን አልን?
 • ከተረጂነት ወደ ምርታማነት አላችሁ።
 • ታዲያ እንደዚያ ማለታችን ችግር አለው?
 • ችግር የለውም፣ ግን….
 • ግን ምን?
 • በመጀመሪያ ከዕዳ ወደ ምንዳ ብላችሁ የጀመራችሁት ንቅናቄ ምን ውጤት እንዳመጣ ግለጹልና?
 • እሱ እንኳ እንደታሰበው አልሄደም።
 • ለምን?
 • ምክንያቱ አይታወቅም፣ ግን የተጠበቀውን ውጤት አላመጣም።
 • እና ምን አሰባችሁ?
 • ምን እናስባለን?
 • ንቅናቄውን ውጤታማ ለማድረግ?
 • በግሌ ንቅናቄው ለምን ውጤት እንዳላመጣ መገምገም አለበት የሚል አቋም ነበረኝ።
 • መሆን የነበረበትም እንደዚያ ነው… መገምገም ነበረበት…
 • ግን እንደዚያ አልሆነም።
 • ለምን?
 • በድርጅት ደረጃ የተወሰነው ሌላ ንቅናቄ እንዲጀመር ነው።
 • አሁን የተጀመረውን ንቅናቄ ማለትህ ነው?
 • አዎ፣ “ከተረጂነት ወደ ምርታማነት” የሚለው ንቅናቄ እንዲጀመር ነው የተወሰነው።
 • በሁለቱ መካከል ልዩነቱ ምንድነው?
 • ከዕዳ ወደ ምንዳ የሚለው አገላለጽ ችግር እንዳለበት ነው የተገመገመው።

– ምን ችግር አለበት?

– ችግሩ ዕዳ የሚለው ቃል ላይ ነው።

– ዕዳ የሚለው ቃል ምን ችግር አለበት?

– ለእኔም ብዙ ግልጽ አልሆነልኝም ግን…

– ግን ምን?

– መንግሥት አልወደደውም።

– ለምን?

– ከፍተኛ ዕዳ ያለበት መንግሥት ስለሆነ፡፡

– ያው አይደለም እንዴ?

– ምኑ?

– ተረጂነት የሚለው ቃል፣ ከዕዳ ወደ ተረጂነት መቀየሩ ምን ለውጥ ያመጣል?

– ያው ነው ግን…

– ግን ምን?

– በቀጥታ መንግሥትን አያመለክትም።

– እንዴት ማለት?

– ዕዳ የሚለው ቃል ከመንግሥት ዕዳ ጋር ሊገናኝ ስለሚችል አልተወደደም።

  ዕርዳታ ግን ለመንግሥት አይደለም የሚቀርበው።

– እና ለማነው?

– ለተረጅዎች።

– ተረጅው ማነው?

– ሕዝብ፡፡

– እህ…. አሁን ገባኝ።

– ምንድን ነው የገባሽ?

– ከዕዳ ወደ ምንዳ የሚለው ንቅናቄ ምንን ታሳቢ አድርጎ እንደተጀመረና ለምን እንዳልተፈለገ ገባኝ።

– ምንን ታሳቢ ተደርጎ ነው የተጀመረው?

– ፓሪስ ክለብን።

– ከፓሪስ ክለብ ምን ታሳቢ ይደረጋል?

– ዕዳ ስረዛ፡፡

– እርግጥ ነው ዕዳ ስረዛ እንደሚኖር ታሳቢ ተደርጎ ነበር።

– ዕዳው ተሰርዞ ቢሆን ኖሮ በገባነው ቃል መሠረት ከዕዳ ወደ ምንዳ ተሸጋገርን  ሊባል ነበር ግን አልሆነም።

– አልሆነም ማለት?

– አልተሳካም ማለቴ ነው።

– እውነት ነው፣ ለጊዜው አልተሳካም።

– ስለዚህ ከራሳችሁ አወረዳችሁት።

– ምኑን?

– ንቅናቄውን ነዋ?

– ወዴት እናወርደዋለን?

– ወደ ሕዝብ ነዋ፡፡

– ምን ብለን? 

– ከተረጂነት ወደ ምርታማነት!

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች

- Advertisment -

ትኩስ ፅሁፎች

ለቀድሞ የሕግ ታራሚዎች የቆመው ሰው ለሰው

የደርግ መንግሥት ደጋፊዎችና የሥልጣን ተጋሪዎች፣ ከከፍተኛ የቀድሞ መንግሥት ባለሥልጣናት...

ባይደን ከምርጫ ራሳቸውን ካገለሉ በኋላ የዴሞክራቱን መድረክ የተቆጣጠሩት ካማላ ሃሪስ

የአሜሪካ ፕሬዚዳንት ጆ ባይደን ኮቪድ መያዛቸው በተነገረ ሳምንት ነበር...

‹‹በዶናልድ ትራምፕ ላይ የተቃጣው የግድያ ሙከራ የተቋማችን ውድቀት ማሳያ ነው››

የአሜሪካ ደኅንነት አገልግሎት (Secret Service) ዳይሬክተር ኪምበርሊ ቺትል ለኮንግረስ...

አደራውን ለመጠበቅ ዕድል ያላገኘው ቅርስ ባለአደራ

የኢትዮጵያ ቅርስ ባለአደራ ማኅበር ከተመሠረተ ሦስት አሥርት አስቆጥሯል፡፡ ማኅበሩ...

የአሸንዳ ጨዋታዎች ‹‹ዕቡነይ››

በነሐሴ በጉጉት የሚጠበቀውን የአሸንዳን በዓል ምክንያት በማድረግ፣ ሙዚቃዊ ከትግራይ...
spot_img

ተዛማጅ ፅሁፎች

[ክቡር ሚኒስትሩ የቅርብ ወዳጃቸው ከሆነች አንድ ባለሀብት የተደወለላቸውን ስልክ አንስተው በኮሪደር ልማቱ ላይ የምታቀርበውን ቅሬታ እየሰሙ ነው]

ክቡር ሚኒስትር እኔ የኮሪደር ልማቱ ላይ ተቃውሞም ሆነ ጥላቻ እንደሌለኝ የሚያውቁ ይመስለኛል? በዚህ እንኳን አትታሚም።  የእውነቴን ነው ክቡር ሚኒስትር። አውቃለሁ ስልሽ? ለኮሪደር ልማቱ አዋጡ ሲባልም ያለማመንታት አምስት ሚሊዮን...

[ክቡር ሚኒስትሩ በችግኝ ተከላ ፕሮግራም ላይ ሳይገኝ ከቀረው አንድ የተቋማቸው ባልደረባ የሆነ የተቃዋሚ ፓርቲ አባልን አስጠርተው እያናገሩ ነው]

ለምንድነው በዚህ አገራዊ ፋይዳ ባለው ፕሮግራም ላይ ያልተገኘኸው? ክቡር ሚኒስትር ህሊናዬ አልፈቀደልኝም። መቃወምና መተቸት ብቻ ውጤት የሚያመጣ መስልዎህ ከሆነ ተሳስተሃል። አልተሳሳትኩም ክቡር ሚኒስትር? ቆይ የመጀመሪያ ዓመት የችግኝ ተከላ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ከሚያከብሯቸው አንድ የቀድሞ ጉምቱ ፖለቲከኛ ስልክ ተደውሎላቸው እያወሩ ነው]

አንዳንድ ነገሮች ቢያሳስቡኝ ነው ቀጠሮ ሳልይዝ ላነጋግርህ የፈለኩት ክቡር ሚኒስትር፡፡ እርስዎማ ቀጠሮ መያዝ አያስፈልግዎትም፣ ምን ገጠመዎት? እኔማ ምን ይገጥመኛል አንተኑ ልጠይቅህ እንጂ? ምን? እውነት ለመናገር የማየው ነገር አሳስቦኛል፡፡ ይንገሩኝ...