Wednesday, July 24, 2024
- ማስታወቂያ -
- ማስታወቂያ -

የጎህ ባንክ መሥራችና አደራጅ አቶ ጌታሁን ናና ከባንኩ የቦርድ አባልነት ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ

ተዛማጅ ፅሁፎች

በኢትዮጵያ የመጀመሪያው የግል የሞርጌጅ ባንክ በመሆን የተቋቋመውን ጎህ ቤቶች ባንክ በማደራጀትና በቦርድ ሊቀመንበርነት ሲመሩ የቆዩት አቶ ጌታሁን ናና ከኃላፊነታቸው ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ።

የጎህ ባንክ መሥራችና አደራጅ አቶ ጌታሁን ናና ከባንኩ የቦርድ አባልነት ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
አቶ ጌታሁን ናና

አቶ ጌታሁን ከጎህ ቤቶች የቦርድ ሊቀመንበርነት የለቀቁት በገዛ ፈቃዳቸው እንደሆነ የተጠቀሰ ሲሆን፣ እስካለፈው ሳምንት ድረስ እንደ አንድ የቦርድ አባል ሲሠሩ እንደነበር ታውቋል፡፡ ሆኖም ከቦርድ አባልነታቸው ለመሰናበት መልቀቂያ አቅርበው ጥያቄያቸው በቦርድ እየታየ ስለመሆኑ ለማወቅ ተችሏል፡፡

የጎህ ቤቶች ባንክ በቅርቡ ባካሄደው ምርጫ አቶ ጌታሁን ዳግም የተመረጡ ቢሆንም፣ በቦርድ ሊቀመንበርነታቸው መቀጠል እንደማይፈልጉ ገልጸው፣ አዲስ የቦርድ ሊቀመንበር እንዲመረጥ በማድረግ በቦርድ አባልነት ብቻ ለማገልገል የሚፈልጉ መሆኑን አስታውቀው፣ በዚሁ መሠረት ሥራ ላይ መቆየታቸው ታውቋል። በዚህ ሳምንት ግን ከቦርድ አባልነታቸውም በገዛ ፈቃዳቸው መልቀቅ እንደሚፈልጉ በመግለጽ ጥያቄያቸውን ለቦርዱ ማቅረባቸውንና ይህ ውሳኔያቸውም ያልተጠበቀ እንደሆነ የሪፖርተር ምንጮች ገልጸዋል፡፡ 

አቶ ጌታሁን ጎህ ቤቶች ባንክን ለማቋቋም በዋና አደራጅነት ከተሰባሰቡት ግለሰቦች መካከል በቀዳሚነት የሚጠቀሱ ሲሆን፣ ባንኩ አደራጅ ኮሚቴ ሰብሳቢ በመሆን እስከ ባንኩ ምሥረታ ድረስ ሲያገለግሉ ቆይተዋል፡፡ ከዚያም የባንኩ ምሥረታ ዕውን ሲሆን የመጀመሪያ የጎህ ቤቶች ባንክ ቦርድ ሊቀመንበር በመሆን ሠርተዋል፡፡ 

አቶ ጌታሁን ጎህ ቤቶች ባንክን በዋና አደራጅነት ከመግባታቸው በፊት የኢትዮጵያ ብሔራዊ ባንክ ምክትል ከዚያም የኢትዮጵያ ልማት ባንክን በፕሬዚዳንትነት መርተዋል፡፡ 

አቶ ጌታሁን በቅርቡ ወደ ሥራ የገባውን ካፒታል የፋይናንስ ልህቀት ማዕከል በዋና አደራጅነት የፋይናንስ ባለሙያዎች ከመሠረቱት መካከል አንዱ ሲሆኑ፣ ይህንኑ ተቋም በዋና ሥራ አስፈጻሚነት በመምራት ላይ ይገኛሉ፡፡

የጎህ ባንክ መሥራችና አደራጅ አቶ ጌታሁን ናና ከባንኩ የቦርድ አባልነት ለመልቀቅ ጥያቄ አቀረቡ | Ethiopian Reporter | ሪፖርተር
አቶ በላቸው ሁሪሶ

በአሁኑ ወቅት አቶ ጌታሁን ናናን ተክተው የጎህ ቤቶች ባንክ የቦርድ ሊቀመንበር በመሆን እየሠሩ ያሉት አቶ በላቸው ሁሪሶ ናቸው፡፡ አቶ በላቸው የጎህ ቤቶች ባንክ ከምሥረታው ጀምሮ በቦርድ አባልነት ሲያገለግሉ የነበሩ ናቸው፡፡ አቶ በላቸው በሙያቸው በተለያዩ የመንግሥት፣ የግልና የዓለም አቀፍ ተቋማት ላይ በተለያዩ ኃላፊነት ቦታዎች ላይ በማገልገል የረዥም ጊዜ ልምድ ያላቸው ናቸው፡፡ ከፋይናንስ ሥራ ጋር በተያያዘ በኦሮሚያ የኅብረት ሥራ ባንክ ውስጥ በቦርድ አባልነት፣ በምክትል ቦርድ ሊቀመንበርነትና በሊቀመንበርነት ያገለገሉ መሆኑ በዋናነት የሚጠቀስ ነው፡፡ 

በአሁኑ ወቅት በምክትል የቦርድ ሊቀመንበርነት በመሆን የተሰየሙት ወ/ሮ ፋሲካ ከበደ ሲሆኑ፣ ቀሪዎቹ የቦርድ አባላት አቶ ሽመልስ ገድለ ጊዮርጊስ፣ ውብሸት ዠቅ አለ (ዶ/ር/ኢንጂነር)፣ አቶ ሰለሞን ተስፋዬ፣ አቶ ዘመት ሥዩምና አቶ ሰመረ አሰፋ ናቸው፡፡

ጎህ ቤቶች ባንክ በዋናነት ለቤት ግዥ፣ ግንባታና ተያያዥ ሥራዎች ፋይናንስ ለማቅረብ የተቋቋመ ባንክ ሲሆን፣ በ2015 ዓ.ም. መጨረሻ ላይ አጠቃላይ የሀብት መጠኑ 2.6 ቢሊዮን ብር መድረሱ መግለጹ ይታወሳል፡፡ በአሁኑ ጊዜ ለስምንት ሺሕ በላይ ባለአክሲዮኖች አሉት፡፡ የመጀመሪያው የሞርጌጅ የግል ባንክ ነው፡፡ ባንኩ የተመሠረተው 1.05 ቢሊዮን ብር የተፈረመና 521.5 ሚሊዮን ብር በተከፈለ ካፒታል ነው፡፡ ባንኩ በ2015 የሒሳብ ዓመት መጨረሻ ላይ ባንኩ አጠቃላይ የተከፈለ ካፒታሉ  1.32 ቢሊዮን ብር መድረሱም መገለጹ አይዘነጋም፡፡ 

spot_img
- Advertisement -spot_img

የ ጋዜጠኛው ሌሎች ፅሁፎች

- ማስታወቂያ -

በብዛት ከተነበቡ ፅሁፎች