Wednesday, July 24, 2024
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

ጉዞው አጭር ነው

ትኩስ ፅሁፎች

አንዲት አዛውንት ሴት አውቶቡስ ውስጥ ገብተው ተቀመጡ በመሄድ ላይ ሳሉም አንዲት ወጣት ሴት አሮጊቷ ከጠቀመጡበት አጠገብ ለመቀመጥ ስትል በቦርሳዋ መታቻቸው። አሮጊቷም ምንም እንዳልተፈጠረ በዝምታ ጉዟቸውን ቀጠሉ። ወጣቷም ሴት በዝምታቸው በመደመም በቦርሳዋ ስትመታቸው ለምን እንዳላማረሩ ጠየቀቻቸው። አሮጊቷም በፈገግታ መለሱ፡፡

 ‹‹በሚቀጥለው ፌርማታ ስለምወርድ ንግግር አስፈላጊ ነው ብዬ አላመንኩበትም፣ ደግሞ ያለኝ ጉዞ እጅግ በጣም አጭር ስለሆነ መነጋገሩ መወያየት አያስፈልግም አሏት። ወጣቷም ይህ ንግግር በወርቅ ፊደላት መፃፍ አለበት አለች። አሮጊቷም በድጋሚ ‹‹ይህን ያህል ትርጉም ለሌለው ነገር መወያየት አያስፈልግም፣ ምክንያቱም የአብሮነታችን ጉዞ በጣም አጭር ነውና፣ እያንዳንዳችን ልንገነዘበው የሚገባን በዚህ ዓለም ላይ ያለን ጊዜ በጣም አጭር መሆኑን፣ በትግል መጨቃጨቅ፣ በከንቱ ክርክር፣ በቅናት፣ ሌሎችን ይቅር ባለማለት፣ በብስጭት ጊዜና ጉልበት ማባከን አይገባም፡፡

የሕይወት ጉዞ በጣም አጭር መሆኑን አስታውሰን ነገሮችን ችላ እንበለው። የዚያን ቆይታችንን ማንም አያውቅም። ጓደኞችንን፣ ቤተሰቦቻችንን እናድንቅ፣ እንከባበር፣ እንደምንወዳቸው እንግለጥ ደግሞም ትሁታን እንሁን፣ ይቅርም እንባባል፣ አመሥጋኝና በደስታ የተሞላን እንሁን ሁላችንም ጉዞአችን በጣም አጭር ነውና።

ሠናይ ቀን!

– ዓባይነህ አስፋው

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች