የፍትሕ ሚኒስትር ወ/ሮ ሃና አርዓያ ሥላሴ፣ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸሙ ጥቃቶችን መከላከልና ምላሽ አሰጣጥ ላይ የቅንጅትና ትብብር ሥራን ለማጠናከር ባለመ የምክክር መድረክ ላይ የተናገሩት። የሴቶችና ማኅበራዊ ጉዳይ ሚኒስቴርና የፍትሕ ሚኒስቴር በጋራ ባዘጋጁት መድረክ ላይ የፍትሕ ሚኒስትሯ እንዳብራሩት፣ ፆታን መሠረት ያደረጉ ጥቃቶች መንስኤዎቻቸው ሥር የሰደዱ የተዛቡ አመለካከቶችና ከአሉታዊ እሴቶችና ልማዶች የሚመነጩ ሊሆኑ ይችላሉ። የማኅበረሰቡን አመለካከት ለመለወጥ ሰፊ ሥራ የሚጠይቅ መሆኑንም አስገንዝበዋል። በመድረኩ በሴቶችና ሕፃናት ላይ የሚፈጸም ጥቃትን ለመከላከልና ምላሽ ለመስጠት የተቀረፀው ብሔራዊ ስትራቴጂ ሰነድ ቀርቦ በአተገባበሩ ላይ ተግባቦት መፈጠሩም ተጠቁሟል።