Friday, March 21, 2025
- Advertisement -
- Advertisement -
ዜናበሕክምና መቶኛ ዓመቱንና በማስተማር ሰባኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው ጎንደር ዩንቨርስቲ ና ስፔሻላይዝድ...

በሕክምና መቶኛ ዓመቱንና በማስተማር ሰባኛ ዓመቱን እያከበረ ያለው ጎንደር ዩንቨርስቲ ና ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 40ኛ ዙር የሕክምና ተማሪዎቹን አስመረቀ

ቀን:

spot_img

ጎንደር ዩኒቨርሲቲው  ዛሬ የካቲት 8 ቀን 2017 ዓ.ም ፣ 254 ወንድ እና 112 ሴት   የሕክምና ተማሪዎቹን ያስመረቀው ለ40ኛ ጊዜ መሆኑንና ይኸም ዩኒቨርስቲው የተመሠረተበትን ምዕተዓመት እያከበረ ባለበት ጊዜ በመሆኑ ልዩ እንደሚያደርገው ተገልጿል።

ተቋሙ ህክምና ተማሪዎች 40ኛ ዙርና  21ኛ ዙር የፋርማሲ ተማሪዎችን ያስመረቀ ሲሆን፣  በሁለተኛ ዲግሪ፣ በሦስተኛ ዲግሪ፣ በስፔሻሊቲና ሰብ ስፔሻሊቲ የትምህርት ዘርፎችን ሲከታተሉ የቆዩ መሆናቸው ታውቋል።

በመርሃ ግብሩ  የጤና ሚኒስቴር ሚኒስትር  ዴዔታ ደረጄ ድጉማ (ዶ/ር ) ፣ የዩንቨርስቲው ፕሬዚዳንት አስራት አጸደወይን (ዶ/ር) ፣ የጎንደር ከተማ ከንቲባና  ሌሎች አካላት ተገኝተዋል።

በመድረኩ ንግግር ያደረጉት የዩንቨርስቲው ፕሬዝዳንት  አስራት አጸደወይን_ዶ/ር)፣   በቅድመ ምረቃና በድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ትምህርታቸውን ያጠናቀቁ ተማሪዎች፣ በኮሌጅ የትምህርት ጉባዔ ተመስክሮና በዩንቨርስቲው ሴኔት ጸድቆ ለምርቃት ቀን በቅተዋል ብለዋል፡፡

“ተመራቂ ተማሪዎች ኢትዮጵያ እናንተን በጥብቅ ትፈልጋችኋለችና ይህ ደስታ የእናት አገራችሁ ጭምር ነው” ያሉት ፕሬዝዳንቱ፣ የሰለጠኑበት ሙያ  ፈታኝና የተከበረ  ቢሆንም ውጤቱ ግን ፈዋሽ መሆኑን እንደሚገነዘቡ ጠቅሰዋል፡፡

በርካታ  “እንቅልፍ አልባ ለሊቶች፣ ስንፍናና ድካም የሻረ ትጋት በብዙ ተግዳሮቶች የተፈተነ ግን ያልተሸነፈ ጥንካሬያችሁ ለዛሬው ቀን አብቅቷችኋልና እንኳን ደስ አላችሁ” ሲሉ ለተመራቂ ተማሪዎች መልዕክታቸውን አስተላልፈዋል፡፡

የጤና ሚኒስትር ዴዔታው  ዶ/ር ደረጄ ድጉማ በበኩላቸው፤ “ተመራቂዎች አድካሚውን የትምህርት ጉዞ በስኬት አጠናቃችሁ በጉጉት ስትጠብቁት ለነበረው የምርቃት ቀናችሁ እንኳን አደረሳችሁ” ያሉ ሲሆን፤ “ቀጣይ የአገራችን ጉዞ ዛሬ የምትመረቁት ተማሪዎች እጅ ላይ የሚወድቅ ነው” ብለዋል፡፡

ተመራቂ ተማሪዎች የተጣለባቸውን ኃላፊነት በብቃት ለመወጣት እራሳቸውን ማዘጋጀት እንደሚገባቸው ያሳሰቡት ዶ/ር ደረጄ፣ በቀጣይ ወደ ሥራ ሲገቡ በሙያቸው  አገራቸውንና ወገኖቻቸውን  ያለ ስስት እንዲያገለግሉ ጠይቀዋል፡፡

በተመረቁበት ሙያ ማህበረሰቡን ያለ ምንም አድሎ ሙያው የሚጠይቀውን ስነ ምግባር አክብረው  ሀላፊነታቸውን እንሚወጡ ቃል ገብተዋል።

ከ2010 ዓ/ም ጀምረው ሌሊትና ቀን ክረምትና በጋ ሳይሉ  ላለፉት 7 ዓመታት በአስቸጋሪና ፈታኝ ሁኔታ ማለፋቸውን ተመራቂ ተማሪዎች በተለይ ለሪፖርተር ተናግረዋል።

በኮሮና ቫይረስ ወቅት ለአንድ ዓመት  አቋርጠው  እንደነበር ያስታወሱት ተማሪዎቹ፣ በዚያም አንድ ዓመትን ጨምረው 7 ዓመት ቆይታ ማድረጋቸውን ተናግረዋል 

በመርሃ ግብሩ ላይም በቅርቡ ሕይወቱ ያለፈውና በባህር ዳር ዩኒቨርሲቲ ሕክምናና ጤና ሳይንስ ኮሌጅ በጠቅላላ ቀዶ ሕክምና ስፔሻሊስት እና የጉበት፣ የቆሽትና የሃሞት መስመር ሰብ ስፔሻሊስት ሃኪም የነበረውን ዶ/ር አንዱዓለም ዳኜን በማሰብ የህሊና ጸሎት ተደርጓል፡፡

ጎንደር ዩኒቨርስቲ 70ኛ ዓመትና አጠቃላይ ስፔሻላይዝድ ሆስፒታል 100ኛ ዓመት የምሥረታ በዓል  በማክበር ላይ ሲሆን በስፖርታዊ ውድድር፣ አዳዲስ መሠረተ ልማቶችን በማስጀመር በነፃ ለማኅበረሰቡ አገልግሎት በመስጠት በዓሉን እንደሚያከብር መናገሩ ይታወሳ።

ዩኒቨርሲቲው  በ11 ኮሌጆች በ87 የቅድመ ምረቃ ፕሮግራሞች ዛሬ የተመረቁትን ጨምሮ  ከ300 በላይ በሁለተኛ ሦስተኛ ዲግሪና ስፔሻላይዜሽን ፕሮግራሞች ከ40 ሺሕ በላይ ያስተናግዳል። ።

spot_img
- Advertisement -

ይመዝገቡ

ተዛማጅ ጽሑፎች
ተዛማጅ

የብሔርተኝነት ፖለቲካ ጡዘትና በአገር ላይ የሚደቅነው አደጋ

በነገደ ዓብይ ከአንድ ዓመት በፊት በሪፖርተር ዕትም “እኔ እምለው” ዓምድ...

[ክቡር ሚኒስትሩ ወደ ቢሯቸው ሲገቡ አማካሪያቸው ማኅበራዊ ሚዲያ ላይ በተመለከተው አንድ ጉዳይ ተገርሞ አገኙት] 

ምነው? ደህና አይደለህም? ኧረ ደህና ነኝ ክቡር ሚኒስትር። ፊትህ ላይ የማየው...

ተንቀሳቅሶ የመሥራት መብት ጉዳይ በአዲሱ የጎዳና ንግድ ደንብ መነጽር

በየቦታው ገመድ ወጥረው ‹‹ወዲህ በሉ›› እያሉ ገንዘብ የሚቀበሏቸው ሰዎች...

ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የብድር ወለድ ማሻሻያ በፋይናንስ ዘርፍ ላይ የሚያሳርፈው ተሻጋሪ ተፅዕኖ

የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ በቅርቡ የብድር ወለድ ምጣኔው ላይ ያደረገው...
error: