አስፈላጊ ግብዓቶች
1 ኪሎ ሥጋ
3 ኩባያ ቢራ
ግማሽ ኩባያ ማርጋሪን
2 የሻይ ማንኪያ ጨው
ሩብ የሻይ ማንኪያ ቁንዶ በርበሬ
አሠራር
በአንድ ወፍራም ድስት ውስጥ ማርጋሪን ጨምሮ ሥጋውን አጋም እስኪመስል እያገላበጡ ማብሰል፡፡
ጨውና ቁንዶ በርበሬ ጨምሮ እንደገና መጥበስ፡፡
አንድ ኩባያ ከሩብ ቢራ ጨምሮ የሙቀቱ ኃይል መጠነኛ በሆነ እሳት ላይ ለሦስት ሰዓት ማብሰል፡፡ እንደ አስፈላጊነቱ ቢራ ጠብ እያደረጉ ማበሰል፡፡
በስሱ እየቆረጡ በሰፊ ሳህን ማቅረብ፡፡
ስድስት ሰው ይመግባል፡፡
– ደብረወርቅ አባተ (ሱ ሼፍ) ‹‹ባህላዊ ምግቦች አዘገጃጀት›› (2003)