Sunday, June 4, 2023
- Advertisement -
- Advertisement -
- Advertisement -

ፌርማታ ፅሁፎች

‹‹በሮም በፖሊስና ስደተኞች መካከል በነበረው ግጭት የተጎዳ ኢትዮጵያዊ የለም፡፡››

ትኩስ ፅሁፎች

​የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር፣ በጣሊያን መዲና ሮም በፖሊስና ስደተኞች መካከል በተከሰተ ግጭት የተጎዳ ኢትዮጵያዊ አለመኖሩን ነሐሴ 23 ቀን 2009 ዓ.ም. በሰጠው መግለጫ የገለጸው፡፡ በመሃል ሮም ተርሚኒ ከተባለው ዋናው ባቡር ጣቢያ አቅራቢያ በሚገኝ ሕንፃ ከ2005 ዓ.ም. ጀምሮ ይኖሩ የነበሩትን የኢትዮጵያና የኤርትራ ስደተኞች ከአሥር ቀናት በፊት ጀምሮ አካባቢውን ለቀው እንዲወጡ የአገሪቱ ፖሊስ የኃይል ዕርምጃ መውሰዱና ግጭት መድረሱ ተቃውሞም ማስከተሉ 725 እንደሚሆኑ የተነገረ ኢትዮጵያውያና ኤርትራውያን ስደተኞች በጎዳና ላይ መበተናቸው ተዘግቧል፡፡ በጣሊያን የኢትዮጵያ ኤምባሲ ‹‹በቦታው ተገኝቼ ባደረግኩት ማጣራት አራት ኢትዮጵያውያን ከሕንፃው በመውጣት ያለምንም ጉዳት ወደ ሌላ ስፍራ የሄዱ መሆኑን ለማረጋገጥ ችያለሁ›› ማለቱን ተከትሎም የውጭ ጉዳይ ሚኒስቴር በኤፍቢሲ ባወጣው መግለጫ ‹‹የሌሎች አፍሪካ አገሮች እንጂ የጉዞ ሰነድ ያላቸው ኢትዮጵያውያን በቦታው አልነበሩም፤›› ብሏል፡፡

- Advertisement -
- Advertisement -

ተጨማሪ ለማንበብ

በብዛት የተነበቡ ፅሁፎች